1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አርጀንቲና የደቡብ አሜሪካ (ኮፓ አሜሪካ) ዋንጫን አሸነፈች

ሰኞ፣ ሐምሌ 8 2016

አርጀንቲና የደቡብ አሜሪካ (ኮፓ አሜሪካ) ዋንጫን ለ16ኛ ጊዜ አሸንፋ በማንሳት ክብረ ወሰን ሰበረች ። አርጀንቲና እሁድ ዕለት በፍጻሜው 1 ለ0 ያሸነፈችው ኮሎምቢያን ነው ። ለአርጀንቲና በሦስት ያለፈውን የዓለም ዋንጫ እና የማሸነፊያዋን ብቸኛ ግብ ያስቆጠረው ላውታሮ ማርቲኔዝ ነው ።

https://p.dw.com/p/4iIj7
USA Copa America 2024 l Argentinien gewinnt, Nationalmannschaft feiert
ምስል Charly Triballeau/AFP via Getty Images

አርጀንቲና የደቡብ አሜሪካ (ኮፓ አሜሪካ) ዋንጫን ለ16ኛ ጊዜ አሸንፋ በማንሳት ክብረ ወሰን ሰበረች ። አርጀንቲና እሁድ ዕለት በፍጻሜው 1 ለ0 ያሸነፈችው ኮሎምቢያን ነው ። ለአርጀንቲና  የማሸነፊያዋን ብቸኛ ግብ 112ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠረው ላውታሮ ማርቲኔዝ ነው ። በሺህዎች የሚቆጠሩ ቲኬት የሌላቸው ደጋፊዎች ወደ ስታዲየሙ ካልገባን በማለታቸው፦ ጨዋታው ለአንድ ሰአት ግድም ዘግይቶ ነበር የጀመረው ።

የ37 ዓመቱ ሊዮኔል ሜሲ ከኮሎምቢያ ጋ በነበረው የፍጻሜ ግጥሚያ 36ኛው ደቂቃ ላይ ነበር ጉልበቱ ላይ ጉዳት የደረሰበት ። 65ኛው ደቂቃ ላይ እያነባ ከሜዳ ለመውጣት ተገድዷል
የ37 ዓመቱ ሊዮኔል ሜሲ ከኮሎምቢያ ጋ በነበረው የፍጻሜ ግጥሚያ 36ኛው ደቂቃ ላይ ነበር ጉልበቱ ላይ ጉዳት የደረሰበት ። 65ኛው ደቂቃ ላይ እያነባ ከሜዳ ለመውጣት ተገድዷል ። ፎቶ ከማኅደር፦ ቦነስ አይረስ አርጀንቲና የሚገኝ ሕንጻ ምስል Roberto Tuero/Zuma/IMAGO

የዓለማችን ምርጡ የእግር ኳስ ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ የመጨረሻው ይሆናል የተባለለት የትናንቱ የፍጻሜ ግጥሚያ ላይ በጉዳት እስከ መጨረሺያው ባለመጫወቱ በእንባ ተውጦ ታይቷል ። የስምንት ጊዜ የዓለማችን ምርጥ የእግር ኳስ ተጨዋች ተብሎ በባሎን ዲዮር የተመረጠው የ37 ዓመቱ ሊዮኔል ሜሲ ከኮሎምቢያ ጋ በነበረው ግጥሚያ 36ኛው ደቂቃ ላይ ነበር ጉልበቱ ላይ ጉዳት የደረሰበት ። 65ኛው ደቂቃ ላይ ግን ኳሷን ተክትሎ አንድም ተጨዋች ሳይነካው ከኮሎምቢያው አጥቂ ሉዊስ ዲያዝ አጠገብ ወድቋል ።  ወዲያውም እያነከሰ፤ በእንባ ተውጦ ከሜዳ ወጥቷል ። ተቀያሪ ወንበር ላይ ሆኖም ፊቱን በሁለት እጆቹ መዳፍ ከልሎ እየተንሰቀሰቀ ሲያለቅስ ነበር ። ምናልባትም ይህ ለብሔራዊ ቡድኑ የመጨረሻው ጨዋታ ሊሆን ይችላል ተብሏል ። ለሌላኛው አርጀንቲናዊ የ36 ዓመቱ አንኼል ዲ ማሪያ ግን የትናንቱ የፍጻሜ ግጥሚያ የመጨረሻው ነበር ።

አርጀንቲና ኮሎምቢያን በኮፓ አሜካ ዋንጫ 2 ለ1 ያሸነፈችበት ግጥሚያ ለአርጀንቲናዊ የ36 ዓመቱ አንኼል ዲ ማሪያ ግየመጨረሻው ነበር
አርጀንቲና ኮሎምቢያን በኮፓ አሜካ ዋንጫ 2 ለ1 ያሸነፈችበት ግጥሚያ ለአርጀንቲናዊ የ36 ዓመቱ አንኼል ዲ ማሪያ ግየመጨረሻው ነበር ። ፎቶ፦ ከማኅደርምስል Matthias Koch/picture alliance

ባ,ርጀንቲና ሽንፈት የገጠማት ኮሎምቢያ ለሁለተኛ ጊዜ የኮፓ አሜሪካ ዋንጫን ለማንሳት የነበራት ሕልም በእነ ሊዮኔል ሜሲ መክኗል ።  የኮሎምቢያ የትናንቱ ሽንፈት ከሁለት ዓመት ከመንፈቅ ግድም ወዲህ የመጀመሪያው ሆኖ ተመዝግቧል ። ኮሎምቢያ ሽንፈት የገጠማት እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር በየካቲት 2022 በአርጀንቲና ነበር ። ቀጣይ የማጣሪያ ጨዋታ በመስከረም ወር የሚጠብቃት ኮሎምቢያ በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያም ከምድቧ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች ።  #DWSports 

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ታምራት ዲንሳ