1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካሰሜን አሜሪካ

ትራምፕ ላይ የተፈጸመው የግድያ ሙከራ

እሑድ፣ ሐምሌ 7 2016

ግሬግ የተባለና በቦታው የነበረ የዓይን እማኝ፣ዶናልድ ትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ በሚያደርጉበት ስፍራ የቅርብ ርቀት ላይ በሚገኝ ህንጻ ላይ መሳሪያ የታጠቀ ግለሰብ ማየቱን ለፖሊስ ተናግሯል። የዐይን እማኙ፣ትራምፕ ላይ የግድያ ሙከራ የፈጸመውን ግለሰብ ለፖሊስ መጠቆሙንም አስታውቋል።

https://p.dw.com/p/4iHDd
የአሜሪካ አልሞ ተኳሾች የግድያ ሙከራ ያደረገውን ወጣት ገድለውታል
የአሜሪካ አልሞ ተኳሾች የግድያ ሙከራ ያደረገውን ወጣት ገድለውታልምስል Gene J. Puskar/AP Photo/picture alliance

የፔንሲልቫንያ የምርጫ ዘመቻ

ተጋግሎ በቀጠለውና የወራት ዕድሜ በቀሩት የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ፣ የሪፐብሊካን ፓርቲው ዕጩ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ፔንሲልቫንያ በተባለችው ግዛት እንደተለመደው ከደጋፊዎቻችው ፊት ቆመው ንግግር በማድረግ ላይ ነበሩ። ፔንሲልቫኒያ፣የአሜሪካ ኘሬዚዳንት ውጤትን ይወስናሉ ከሚባሉ ቁልፍ ግዛቶች አንደኛዋ ናት። በፔንሲልቫኒያ የምርጫ ቅስቀሳ ላይ የነበሩት ትራምፕ  ከተተኮሱባቸው በርካታ ጥይቶች አንደኛው የቀኝ ጆሯቸውን በስታ አቁስላቸዋለች።በዚሁ መኻል፣ የአሜሪካ የደህንነት ሰራተኞች ተሯሩጠው  ወደ መድረክ በመውጣት የቀድሞውን ፕሬዝዳንት ዝቅ አድርገው ከተኩስ እሩምታው ለመከላከላል ችለዋል።

ቀኝ እጃቸው እና ፊታቸው በደም የተሸፈነው ትራምፕ፣ጥቃቱ ከተፈጸመባቸው መድረክ በደህንነት ሰዎች ተከልለው፣ ወደ ተዘጋጀላቸው መኪና ሲወሰዱም የቅኝ እጃቸውን በማንሳት ለደጋፊዎቻቸው መልዕክት አስተላልፈዋል፤ ደጋፊዎቻቸውም ድጋፋቸውን ገልጸውላቸዋል።

 የቀድሞ ፕሬዝዳንት መልዕክት

የቀድሞው ፕሬዚዳንት ወደ አካባቢው የሚገኝ ሆስፒታል ከተወሰዱ በኋላ"ትሩዝ ሶሻል" በተባለው የማኀበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት፣ በጥይት ተመትቻለሁ ሲሉ የግድያ ሙከራ እንደተፈጸመባቸው አስታውቀዋል።

የተኩስ ድምጽ በመስማቴና ጥይቱ ቆዳዬን ሲነካኝ ስለተሰማኝ፣ የሆነ ችግር እንዳለ አውቅ ነበር ያሉት ትራምፕ፣ ብዙ ደም እንደፈሰሳቸው ጽፈዋል።

ዶናልድ ትራምፕ ከግድያ ሙከራው በኋላ
ዶናልድ ትራምፕ ከግድያ ሙከራው በኋላምስል REUTERS

የዐይን እማኝ ምስክርነት

ግሬግ የተባለና በቦታው የነበረ የዓይን እማኝ፣ዶናልድ ትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ በሚያደርጉበት ስፍራ የቅርብ ርቀት ላይ በሚገኝ ህንጻ ላይ መሳሪያ የታጠቀ ግለሰብ ማየቱን ለፖሊስ ተናግሯል። የዐይን እማኙ፣ትራምፕ ላይ የግድያ ሙከራ የፈጸመውን ግለሰብ ለፖሊስ መጠቆሙንም አስታውቋል።

 "የጦር መሳሪያ እንደያዘ በግል ማየት ይቻላል። ወደ እርሱ እያመለከትን፣ በቦታው ለነበሩት ፖሊሶች ሰውዬው የጦር መሣሪያ መያዙን እየነገርናቸው ነበር።ግራ ገብቷቸው ምን እንደተፈጠረ አያውቁም ነበር። እዚህ ጣሪያው ላይ ምን ይሰራል እያየነው ነው ብለን እየነገርናችው ነበር።ቀጥሎ ያሰብኩት ነገር ትራምፕ እስካሁን ንግግር እያደረጉ ለምን ቆዩ?ለምን ከመድረኩ ላይ አያወርዷቸውም የሚለው ነው።"

ጆሴፍ ባይደን ስለጥቃቱ ምን አሉ?

ጥቃቱም ተከትሎ ፕሬዝደንት ጆሴፍ ባይደን ለአሜሪካ ሕዝብ በቴሌቪዥን ባስተላለፉት መልዕክታቸው፣የግድያ ሙከራውን በጥብቅ አውግዘው፣እንደዚህ ዐይነት ሁከት በአሜሪካ ተቀባይነት እንደሌለው አመልክተዋል።

" አሜሪካ ውስጥ ለዚህ አይነት ጥቃት ቦታ የለም፤ እንደዚህ መሆን አንችልም ይህንን ልንቀብለው አንችልም።"

ፕሬዚደንት ባይደን ከጥቃቱ በኋላ ከትራምፕ ጋር በስልክ መነጋገራቸው ተመልክቷል።

USA Butler Wahlkampf Trump Zwischenfall
ምስል Evan Vucci/AP Photos/picture alliance

ምርመራው ለወራት ይቀጥላል

ትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ  ከሚያደርጉበት መድረክ በመቶ ሜትሮች ርቀት ላይ ሆኖ የተኮሰው ግለሰብ በአልሞ ተኳሾች ከተገደለ በኋላ፣ የአሜሪካ የምርመራ ቢሮ ሰፊ ምርመራ እያካሄደ ነው። የምርመራ ቢሮው፣ ትራምፕ ላይ የተፈጸመውን ድርጊት የግድያ ሙከራ አድርጎ እንደሚመለከተው ነው ያስታወቀው።

ኤፍ ቢ አይ፣እንዳመለከተው፣በምርጫ ዘመቻው ላይ ትራምፕን ያቆሰላቸው፣ቶማስ ማቲው ክሩክስ ይባላል፣የ20 ዓመት ወጣት ነው።

 ክሩክስ በወቅቱ መታወቂያ ባለመያዙ ማንነቱን ለማወቅ፣መርማሪዎች የዘረመል ናሙና መጠቀማቸው ተገልጿል።

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ማጠናቀቁ የተገለጸው ክሩክስ በሪፐብሊካን ፖርቲ መራጭነት የተመዘገበ እንደሆነ፣እንዲሁም እንደ ጎርጎሮሳዊው ጊዜ አቆጣጠር 2021 ለሊበራል የዘመቻ ቡድን ገንዘብ መለገሱ ታውቋል።

ክሩክስ ጥቃቱን ለምን ዓላማ እንደፈጸመውና ከእርሱ ጋር ሌሎች ተባባሪ ሰዎች እንዳሉ ለማወቅ እንዲቻል፣ምርመራው ለወራት የሚቀጥል እንደሆነ የፌዴራሉ ምርመራ ቢሮ ሃላፊዎች አስታውቀዋል።

የግድያ ሙከራውን ፈጽሟል የተባለው ግለሰብ በአሜሪካ የደህንነት አባላት የተገደለ ሲሆን፣ ሌሎች ሁለት ሰዎች በተኩስ ልውውጡ ተገድለዋል፣ሁለት ሰዎች በጽኑ ቆስለዋል።

ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ባይደን፣ ጥቃቱን ተከትሎ ለአሜሪካ ሕዝብ በቴሌቪዥን ባስተላለፉት መልዕክት የግድያ ሙከራውን በጥብቅ

 አውግዘዋል።

" አሜሪካ ውስጥ ለዚህ አይነት ጥቃት ቦታ የለም፤ እንደዚህ መሆን አንችልም ይህንን ልንቀብለው አንችልም።"

ፕሬዚደንት ባይደን ከጥቃቱ በኋላ ከትራምፕ ጋር በስልክ መነጋገራቸው ተመልክቷል።

ትራምፕ ከግድያ ሙከራው በኋላ
ትራምፕ ከግድያ ሙከራው በኋላምስል Evan Vucci/AP Photo/picture alliance

ምርመራው ለወራት ይቀጥላል

ትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ  ከሚያደርጉበት መድረክ በመቶ ሜትሮች ርቀት ላይ ሆኖ የተኮሰው ግለሰብ በአልሞ ተኳሾች ከተገደለ በኋላ፣ የአሜሪካ የምርመራ ቢሮ ሰፊ ምርመራ እያካሄደ ነው።

የምርመራ ቢሮው፣ ትራምፕ ላይ የተፈጸመውን ድርጊት የግድያ ሙከራ አድርጎ እንደሚመለከተው ነው ያስታወቀው። ኤፍ ቢ አይ፣እንዳመለከተው፣በምርጫ ዘመቻው ላይ ትራምፕን ያቆሰላቸው፣ቶማስ ማቲው ክሩክስ ይባላል፣የ20 ዓመት ወጣት ነው።  ክሩክስ በወቅቱ መታወቂያ ባለመያዙ ማንነቱን ለማወቅ፣መርማሪዎች የዘረመል ናሙና መጠቀማቸው ተገልጿል።

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ማጠናቀቁ የተገለጸው ክሩክስ በሪፐብሊካን ፖርቲ መራጭነት የተመዘገበ እንደሆነ፣እንዲሁም እንደ ጎርጎሮሳዊው ጊዜ አቆጣጠር 2021 ለሊበራል የዘመቻ ቡድን ገንዘብ መለገሱ ታውቋል።

ክሩክስ ጥቃቱን ለምን ዓላማ እንደፈጸመውና ከእርሱ ጋር ሌሎች ተባባሪ ሰዎች እንዳሉ ለማወቅ እንዲቻል፣ምርመራው ለወራት የሚቀጥል እንደሆነ የፌዴራሉ ምርመራ ቢሮ ሃላፊዎች አስታውቀዋል።

ታሪኩ ሃይሉ

ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር