1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በቦስተን ድል ቀንቷዋል፤ የአፍሪካ ዋንጫም ወደ ፍጻሜው እየተቃረበ ነው

ሰኞ፣ ጥር 27 2016

ከአትሌቲክስ ፤ አሜሪካ ቦስተን በተካሄደ የኒው ባላንስ የቤት ውስጥ የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያውያኑ ለሜቻ ግርማ እና ጉዳፍ ጸጋይ አሸናፊ መሆናቸው፤ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች የዓለም ዋንጫ ማጣርያ በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስቴዲየም የደቡብ አፍሪካ አቻውን ያስተናገደው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሸንፏል።

https://p.dw.com/p/4c3ve
Olympische Spiele Tokio | Gudaf Tsegay Äthiopien
ምስል INA FASSBENDER/AFP

የጥር 27 ቀን 2016 ዓ/ም የስፖርት ዝግጅት

 አሜሪካ ቦስተን በተካሄደ የኒው ባላንስ የቤት ውስጥ የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያውያኑ ለሜቻ ግርማ እና ጉዳፍ ጸጋይ አሸናፊ መሆናቸው፤ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች የዓለም ዋንጫ ማጣርያ በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስቴዲየም የደቡብ አፍሪካ አቻውን ያስተናገደው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ማሸነፉ ፤ በድራማዊ ክስተቶች ታጅቦ የቀጠለው የአፍሪቃ ዋንጫ አስተናጋጇ አይቮሪኮስትን ጨምሮ ግማሽ ፍጻሜውን የተቀላቀሉ አራት ሃገራት መለየታቸው ፤ በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የመሪዎቹ የአንገት ለአንገት ትንቅንቅ ፤ የቡንደስሊጋው ኃያል ባየር ሙንሽን ከመሪው የነበረበትን የነጥብ ልዩነት ያጠበበትን ድል ማስመዝገቡን ጨምረን የሌሎች የአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች ውጤቶች  ይዳሰሳሉ።  ። 
አሜሪካ ቦስተን ኒው ባላንስ የቤት ውስጥ የሩጫ ውድድር እንደተጠበቀው ኢትዮጵያውያኑ ለሜቻ ግርማ እና ጉዳፍ ጸጋይ አሸናፊ ሆነዋል። በ1,500 ሜትር ርቀት የተወዳደረችው አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ ርቀቱን በ3 ደቂቃ 58 ሰከንድ ከ11 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመግባት የወርቅ ሜዳሊያውን ስታሸንፍ ሌላዋ ኢትዮጵያዊት ብርቄ ኃየሎም 3 ደቂቃ 58 ሰከንድ ከ43 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት 2ኛ ሆናለች ። ጉዳፍ ጸጋይ የገባችበት ሰዓት የስፍራው ክብረ ወሰን ሆኖ ተመዝግቧል። በማይክሮ ሰከንዶች ብቻ ተቀድማ 2ኛ የወጣችው ብርቄ ኃየሎም ያሳየችው እልህ አስጨራሽ ብቃት ለወደፊት እጅጉን ተስፋ የሚጣልባት አትሌት መሆኗን አሳይታለች ። በርቀቱ አሜሪካዊቷ ኤምሊ ማካይ ሶስተኛ ወጥታለች ። በወንዶች የኒው ባላንስ የ3 ሺ ሜትር የሩጫ ውድድር ለሜቻ ግርማ የስፍራውን ክብረ ወሰን በማሻሻል ጭምር አሸናፊ ሆኗል። ለሜቻ ውድድሩን ለማሸነፍ 7 ደቂቃ ከ29 ሰከንድ ከ09 ማይክሮ ሰከንድ ወስዶበታል። በውድድሩ ኬንያዊው ኤድዊን ኩርጋት ሁለተኛ ሲወጣ አየላንዳዊው ብርያን  ፋይ ሶስተኛ ሆኖ አጠናቋል። 
እግር ኳስ 
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች የሴት ብሄራዊ ቡድን ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የደቡብ አፍሪቃ አቻውን ትናንት እሁድ በአበበ ቢቂላ ስቴድየም አስተናግዶ 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል። የብሄራዊ ቡድኑ በደቡብ አፍሪቃ አቻው ላይ በፍጹም የበላይነት ማሸነፉ ለቀጣይ ውድድሮች ተስፋ እንዲጣልበት ከማድረግ ባሻገር ለዋናው ብሔራዊ ቡድን መጠናከር ከወዲሁ ተስፋ እንዲጣልበት አድርጓል። የጥር 20 ቀን፣ 2016 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ
በ1,500 ሜትር ርቀት የተወዳደረችው አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ ርቀቱን በ3 ደቂቃ 58 ሰከንድ ከ11 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመግባት የወርቅ ሜዳሊያውን ስታሸንፍ ሌላዋ ኢትዮጵያዊት ብርቄ ኃየሎም 3 ደቂቃ 58 ሰከንድ ከ43 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት 2ኛ ሆናለች ።ምስል JEWEL SAMAD/AFP

በድራማዊ ክስተቶች ታጅቦ፤ የስፖርት ተንታኞች እና ተመልካቾችን የቅድመ ግምት እያፋለሰ የቀጠለው 34ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ ደርሷል።  የምድብ ድልድሉን ተንጠላጥላ ያለፈችው የውድድሩ አስተናጋጅ አይቮሪኮስት በሩብ ፍጻሜ የተሻለ ግምት ተሰጥቷት የነበረውን ማሊን በተጨማሪ ሰዓት ባስቆጠረችው ጎል 2 ለ 1 በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን ስትቀላቀል ፤ ማሊ የማይገባትን ነገር ግን መራሩን ሽንፈት ተከናንባ ከውድድሩ ለመሰናበት ግድ ብሏታል። ናይጄሪያ ፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ደቡብ አፍሪቃም ግማሽ ፍጻሜውን የተቀላቀሉ ሃገራት ናቸው ። በሩብ ፍጻሜ ፍልሚያ አሳዛኝ ተሸናፊ ከነበሩት ውስጥ ትንሿ ኬፕ ቨርዴ ተጠቃሽ ናት ። ከ500 ሺ ብዙም የማይበልጥ የህብ ቁጥር የያዘችው የምዕራብ አፍሪቃውቷ ደሴት ሀገር ከደቡብ አፍሪቃ ጋር የነበራት የሩብ ፍጻሜ ውድድር ቁጭ ብድግ ያስደረጉ ትዕይንቶችን ቢያሳይም የማታ ማታ ደቡብ አፍሪቃ በመለያ ምት አሸንፋ ወደ ዋንጫ አንድ እርምጃ የሚያስጠጋትን ውጤት አስመዝግባለች። 
የግማሽ ፍጻሜ ተፋላሚ ሀገራት ከነገ በስትያ ረቡዕ ምሽት በሚያደርጓቸው ሁለት ጫወታዎች የዋንጫ ተፋላሚ ሀገራትን ይለያሉ ። በዚሁ መሰረተት ምሽት 2 ሰዓት ላይ ናይጄሪያ ከደቡብ አፍሪቃ ሲጫወቱ ምሽት አምስት ሰዓት ላይ ደግሞ አዘጋጇ አይቮሪኮስትን ከ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ያገናኛል ። 34ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ የፊታችን ቅዳሜ ለ 3ኛነት እንዲሁም እሁድ የግማሽ ፍጻሙ አሸናፊ ሃገራት  የዋንጫ ፍልሚያ አድርገው ውድድሩም በይፋ ይጠናቀቃል። 
በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት ወደ ተከናወኑ የአውሮጳ ዋንኛ ሊጎች የእግር ኳስ ውድድሮች ስንሸጋገር ፤ ቀዳሚ የምናደርገው የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግን ነው ። ትናንት እሁድ በበርካቶች ዘንድ ሲጠበቅ የቆየው  እና በአርሴናል እና ሊቨርፑል መካከል በኤሜሬትስ የተከናወነው ጫወታ በአርሴናል የ 3 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቋል። ለአርሴናል ጎሎቹን ሳካ ፣ ማርቲኔሊ እና ተቀርሮ የገባው ትሮሳርድ ሲያስቆጥሩ ፤ ሊቨርፑልን ከሽንፈት ያልታደገችው ጎል ደግሞ የአርሴናሉ ተከላካዩ ጋብሬል ማጋሌሽ በራሱ ላይ አስቆጥሯል።

የደቡብ አፍሪካው በረኛ አራት የመለያ ምቶችን ማዳን ችሏል።
የግማሽ ፍጻሜ ተፋላሚ ሀገራት ከነገ በስትያ ረቡዕ ምሽት በሚያደርጓቸው ሁለት ጫወታዎች የዋንጫ ተፋላሚ ሀገራትን ይለያሉ ። በዚሁ መሰረተት ምሽት 2 ሰዓት ላይ ናይጄሪያ ከደቡብ አፍሪቃ ሲጫወቱ ምሽት አምስት ሰዓት ላይ ደግሞ አዘጋጇ አይቮሪኮስትን ከ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ያገናኛል ። ምስል Samuel Shivambu/ BackpagePix/empics/picture alliance
የአይቮሪኮስት ብሄራዊ ቡድን ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል።
በድራማዊ ክስተቶች ታጅቦ፤ የስፖርት ተንታኞች እና ተመልካቾችን የቅድመ ግምት እያፋለሰ የቀጠለው 34ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ ደርሷል።  የምድብ ድልድሉን ተንጠላጥላ ያለፈችው የውድድሩ አስተናጋጅ አይቮሪኮስት በሩብ ፍጻሜ የተሻለ ግምት ተሰጥቷት የነበረውን ማሊን በተጨማሪ ሰዓት ባስቆጠረችው ጎል 2 ለ 1 በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅላለች።ምስል Siphiwe Sibeko/REUTERS

የታኅሣሥ 29 ቀን፣ 2016 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

ሊጉን እየመራ በነበረው ሊቨርፑል እና በአርሴናል መካከል የነበረው የነጥብ ልዩነትም ከ 5 ወደ 2 ዝቅ ማለቱ ለዋንጫው የሚደረገውን ትንቅንቅ የበለጠ አጓጊ አድርጎታል። ትናንት እሁድ በተደረጉ ሌሎች ጫወታዎች ወደ ወጥ አቋም እየተመለሰ ያለው ማንችስተር ዩናይትድ በሜዳው ኦልትራፍርድ ዌስት ሃም ዩናትድን አስተናግዶ 3 ለ 0 በሆነ ሰፊ ጎል ማሸነፍ ችሏል። አሰልጣኝ አልረጋ ያለው እና ሽንፈትን የተለማመደው ቼልሲ ደግሞ በሜዳው እና በደጋፊው ፊት ዎልቨር አምፕትንን አስተናግዶ የ4 ለ 2 ሽንፈት ተከናንቧል። በርን ማውዝ ከኖቲንግሃም 1 ለ 1 አጠናቀዋል።  ዛሬ ቀጥሎ በሚደረግ አንድ ጫወታ ብሬንት ፎርድ ማንችስተር ሲቲን ያስተናግዳል። ሊጉን ሊቨርፑል በ51 ነጥቦች ሲመራ አርሴናል በ49 ይከተላል ። ቀሪ ጫወታዎች ያሉት ማንችስተር ሲቲ በ46 ሶስተኛ አስቶን ቪላም በተመሳሳይ ነጥብ በጎል ተበልጦ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። 
በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት በጀርመን ቡንደስሊጋ ተጠባቂ ጫወታዎች ተከናውነዋል። በሊጉ አብዛኞቹ ጫወታዎች የተከናወኑት ባለፈው ቅዳሜ ሲሆን ትናንት እሁድ ሁለት ቻወታዎች ተስተናግደዋል። ኡንየን በርሊንን ያስተናገደው አር ቢ ላይፕሲች 2 ለ0 አሸንፏል። በቮልስቡርግ እና ሆፈንሃይም መካከል የተደረገው ግጥሚያ ሁለት አቻ ተጠናቋል። ቅዳሜ ዕለት ከተደረጉ ግጥሚያዎች ባየር ሙንሽን ቦሩሽያ ሞንቼግላድባህን 3 ለ 1 ያሸነፈበት ጫወታ ተጠቃሽ ነው።የጥር 13 ቀን፣ 2016 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

የአርሴናሉ አጥቂ ካይ ሃቬርስ
ትናንት እሁድ በበርካቶች ዘንድ ሲጠበቅ የቆየው  እና በአርሴናል እና ሊቨርፑል መካከል በኤሜሬትስ የተከናወነው ጫወታ በአርሴናል የ 3 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቋል። ምስል John Walton/empics/picture alliance

ባየር ሙኒክ ጫወታውን ማሸነፉን ተከትሎም ከመሪው ባየር ሊቨርኩሰን ያነበረውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሁለት ማጥበብ ችሏል። በሌሎች ጫወታዎች አይትራ ፍራንክፈርትን ያስተናገደው ኮለን 2 ለ 0 ሲያሸንፍ ፤ ወደ ፍራይቡርግ የተጓዘው ሽቱት ጋርት 3 ለ 1 አሸንፎ መመለስ ችሏል። ሃይድንሃይም የተጓዘው ቦሩሽያ ዶርትሙንድ ደግሞ ያለምንም ጎል ነጥብ ጥሎ ተመልሷል። ሊጉን ሊቨርኩሰን በ52 ነጥቦች ሲመራ ፤ ባየር ሙኒክ በ50 ይከተላል። ሽቱት ጋርት እና ዶርቱሙንድ በ40 እና 37 ነጥቦች ሶስተኛ እና አራተኛ ናቸው ። 
በስፔን ላሊጋ ትናንት እሁድ በሪያል ማድሪድ እና አትሌቲኮ ማድሪድ መካከል ይጠበቅ የነበረው ግጥሚያ አንድ አቻ ተጠናቋል። አወዛጋቢ በነበረው ጫወታ አትሌቲኮዎች በ93ኛው ደቂቃ ባስቆጠሩት ጎል ከሜዳቸው ውጭ ነጥብ ተጋርተው መመለስ ችለዋል። በሌሎች ጫወታዎች ሴልታ ቪጎ ከሜዳው ውች ኦሳሱናን ገጥሞ 3 ለ 0 አሸንፎ የተመለሰ ሲሆን ሪያል ቤትስ ከጌታፌ 1, አቻ ፤ ቪያ ሪያል እና ካዲስ ያደረጉት ጫወታ ደግሞ ያለምንም ጎል ተጠናቋል። ሊጉን ሪያል ማድሪድ በ58 ነጥቦች ሲመራ ጊሮና በ56 ነጥብ ይከተላል። ባርሴሎና እና እና አትሌቲኮ ማድሪድ ደግሞ በ50 እና 48 ነጥቦች ሶስተኛ እና አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። 
 
ታምራት ዲንሳ 
ሸዋዬ ለገሰ

የባየር ሙኒኩ አጥቂ ሃሪ ኬን
ዳሜ ዕለት ከተደረጉ ግጥሚያዎች ባየር ሙንሽን ቦሩሽያ ሞንቼግላድባህን 3 ለ 1 ያሸነፈበት ጫወታ ተጠቃሽ ነው። ባየር ሙኒክ ጫወታውን ማሸነፉን ተከትሎም ከመሪው ባየር ሊቨርኩሰን ያነበረውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሁለት ማጥበብ ችሏል።ምስል Sven Hoppe/dpa/picture alliance