1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በጀርመን ለበርካቶች የስራ እድል የፈጠሩ ኢትዮጵያዊ

ረቡዕ፣ ኅዳር 28 2015

በጀርመን የስራ ፈቃድ ሲያገኙ ስራ የጀመሩት በዲኤች ኤል ውስጥ በሹፌርነት ስራ ነበር። ታዲያ ኮንትራታቸው ሲያልቅ ተቀጥረው ሲሰሩበት ከነበረው መስሪያቤት ከአለቆች ጋር በነበራቸው ጥሩ ግንኙነት በራሳቸው አንድ መኪና እራሳቸው ሹፌር ሆነው ስራ ጀመሩ። ከ 26 ዓመት በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ በፍትህ ስራ ላይ ተሰማርተው ይሰሩ ነበር።

https://p.dw.com/p/4KYVc
Assefa Solomon Logistik Deutschland
አቶ አሰፋ ሰለሞን ምስል privat

ቋንቋ የሁሉ ነገር መክፈቻ መሳርያ ነው

ለ26 አመታት በጀርመን አገር የኖሩት አቶ አሰፋ ሰለሞን የከለን ከተማ ነዋሪ ናቸው። የራሳቸው የሎጂስቲክ  ኩባንያ ባለቤት ሲሆኑ ለ60 ሰዎች የስራ እድል ፈጥረዋል። አቶ አሰፋ ባለትዳር እና የአንድልጅ  አባት ናቸው ስላሳለፉት የስደት ህይወት አጋርተውናል።

 የዛሬ 26 አመት  ጀርመን  ከመምጣታቸው በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ የፍትህ ስራ ላይ ተሰማርተው ይሰሩ ነበር። በወቅቱ በነበሩ የሁኔታዎች አለመመቻቸት  በስራቸው ላይ መቀጠል ስላልቻሉ ወደ አውሮፓ ተሰደው  በጀርመን ሀገር መኖር ጀመሩ።

« ጀርመን አገር መጀመሪያ ስገባ ከጠበኩት በላይ ነው እንደጠበኩት ያገኘውት  የከተማው ውበት እና ፅዳቱ ነው። የመጀመሪያው እና ትልቁ ችግር ደግሞ ቋንቋው ነው »ይላሉ። አቶ አሰፋ ጀርመን በገቡበት ወቅት አንድም የጀርመን ቋንቋን መናገር አይችሉም ነበር። ታዲያ በጀርመን የመጀመሪያ ከባዱ ነገር ቋንቋን ነው «እኔ ወደ ጀርመን በመጣሁበት ግዜ ብዙ ሰው እንግሊዘኛ አይናገርም ነበር።እና ነገሮች ከባድ ነበሩ። በባህሪዬ አስቸጋሪ እና ፈታኝ  ነገሮች ሲገጥሙኝ በድል መወጣትን  እንጂ ወደውኃላ ለመመለስ አስቤ  አላውቅም የሚሉት አቶ አሰፋ። «እንደመጣሁ ሁሉም ነገር ግራ ሲያጋባኝ የሁሉ ነገር መክፈቻ ቁልፉ ቋንቋ መሆኑ ገባኝ። ያገኘሁትን እድል ተጠቅሜ ቋንቋ ትምህርት ቤት ገባው» በወቅቱ አብረዋቸው የመጡ ስደተኞች ምንያደርጋል ቢሏቸውም አቶ አሰፋ ግን የቋንቋ ትምህርቱን ቀጠበት። «ትንሽ ከሰዎች ጋር መግባባት ስጀምር ነገሮች እየቀለሉልኝ መጡ»ይላሉ ። 

ዛሬ የራሳቸው የግል ኩባንያ ባለቤት የሆኑት አቶ አሰፋ መጀመሪያ ስራ ሲጀምሩ የተቀጠሩት ኩሽና ውስጥ ሰሀን ማጠብ እና እረዳት ሆነው በማገዝ ነበረ ። አሁን ላይ በራሳቸው ኩባንያ ለ60 ሰዎች  የስራ እድል ፈጥረዋል።ለመሆኑ ስራዎት ምንድነው ስንል ጠየቅናቸው «ከዲኤች ኤል (DHL)ካንትራት ወስጄ  በዲኤች ኤል የሚመጡ መልክቶችን ኮለን ከተማ ውስጥ በ55 መኪናዎች እና በ6o ሰዎች  መልክቶችን አደርሳለሁ» ብለዋል። እርሳቸው ከአመታት በፊት በጀርመን የስራ ፈቃድ ሲያገኙ ስራ የጀመሩት በዲኤች ኤል ውስጥ በሹፌርነት ስራ ነበር። ታዲያ ኮንትራታቸው ሲያልቅ ተቀጥረው ሲሰሩበት ከነበረው መስሪያቤት ከአለቆች ጋር በነበራቸው ጥሩ ግንኙነት በራሳቸው አንድ መኪና እራሳቸው ሹፌር ሆነው ስራ ጀመሩ።  «ሁሉንም ስራ አንድ ሰው መስራት አይችልም ህግ አለ የታስክ ጉዳይ አለ የተለያዩ ማክበር የሚገባ ህጎች አሉ ስለዚ እነዚህን ጉዳዩች ለባለሙያ ነው ምሰጠው»። ሁሉን ነገር መስራት ከባድ ነው ለሚያውቁ ወይም ስራቸው ለሆኑ ሰዎች ስራውን መስጠት ያስፈልጋል ይላሉ።

ኢትዮጵያ ውስጥ አንዳንድ ኢንቨስትመንቶች ላይ ከሰዎች ጋር ለመስራት እጃቸውን እያስገቡ እንደሆነ  አቶ አሰፋ ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል።

አቶ አሰፋ ለወጣቶች ሚያስተላልፉት መልዕክት ካለ ብለናቸው ይህንን ብለዋል «የሰው ልጅ አቅሙ እና እድሉ ካለው አገር ላይ መስራትን የሚያክል ትልቅ ነገር የለም  ከሚያገኘው ገቢ  በተለየ ውስጣዊ ደስታን ይሰጣል» ይላሉ በተለያየ ምክንያት ተሰደው ለሚገኙ ሰዎች መጀመሪያ የሚኖሩበትን አገር ቋንቋ ለማወቅ ጥረት ማድረግ አለባቸው። ቋንቋ የሁሉ ነገር መክፈቻ ነው።ቀጥሎ ህጎችን አኗኗሩን ዘዴዎችን ሁሉን ለማወቅ ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል» ብለዋል ። ከምንም በላይ በስራ ላይ ስርነ ስርአት  አስፈላጊ እና የመጀመሪያው መርህ መሆን አለበት ይላሉ።

ማኅሌት ፋሲል

አዜብ ታደሰ