በምዕራብ ኢትዮጵያ የፀጥታ ችግር ተጽእኖ በእርዳታ አቅርቦት ላይ
ሐሙስ፣ ጥር 26 2014ማስታወቂያ
የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ እርዳታዎች ማስተባበሪያ ቢሮ በእንግሊዘኛ ምህጻሩ (ኦቻ) የምዕራብ ኢትዮጵያ የፀጥታ ችግር ሰብአዊ እርዳታ ለማቀበል እንቅፋት እንደሆነበት አስታወቀ፡፡ ቢሮው ባለፈው ሳምንት ባወጣው ሪፖርት ድጋፍ የሚሹ ዜጎች ቁጥርም እየጨመረ መሆኑን ገልጿል። በምስራቅ፣ምዕራብ እና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት ዜጎች እየተፈናቀሉ መሆኑን የጠቀሰው ቢሮው፣ በምስራቅና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች ከ250,000 በላይ ዜጎች ሰብአዊ እርዳታ እንደሚያሻቸው በሪፖርቱ ጠቁሟል፡፡ በቤኒሻንጉል መተከል የነበረው አለመረጋጋት ወደ ካማሺና አሶሳ ዞን መዛመቱንና በቅርብ ደግሞ በማኦ-ኮሞ ልዩ ወረዳ የስደተኛ መጠለያ ሰፈር በታጠቁ ኃይሎች መዘረፉንም ገልጸዋል።
ነጋሳ ደሳለኝ
ነጋሽ መሐመድ
ኂሩት መለሰ