ሞሮኮ ጥሎ ማለፉን ተቀላቀለች ፤ ጀርመንስ ?
ሐሙስ፣ ኅዳር 22 2015ቀጠር ውስጥ ዛሬም በተደረገው የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ጨዋታ ሞሮኮ ካናዳን 2 ለ1 አሸንፋ ከምድቡ 7 ነጥብ በመያዝ በ1ኛነት አለፈች። በተመሳሳይ ሰዓት በነበረው ጨዋታ ቤልጂየም ከክሮሺያ ጋር ያለምንም ግብ በመለያየቷ ከምድቡ 3ኛ ደረጃ ይዛ ተሰናብታለች። ክሮሺያ በ5 ነጥብ ሞሮኮን ተከትላ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፋለች። በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ምሽት 4 ሰዓት ላይ ደግሞ በተመሳሳይ ጊዜ ጃፓን ከስፔን እንዲሁም ጀርመን ከኮስታሪካ ጋር ይጫወታሉ።
ከምድብ «ረ» ክሮሺያ እና ሞሮኮ 4 ነጥብ ቤልጂየም 3 ነጥብ ይዘው ነበር ዛሬ ወደ ግጥሚያ የገቡት። ካናዳ ሦስተኛ እና የመጨረሻ ጨዋታዋን ዛሬ ለማካሄድ ወደ ሜዳ የገባችው በ0 ነጥብ ነበር 0 ይዛ ተሰናብታለች። ከእየ ምድቡ 1ኛ እና 2ኛ የሚወጡ ሁለት ቡድኖች ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ይችላልሉ። ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ዛሬ ማታ በሚከናወነው የምድብ «ሠ» ውስጥ የሚገኙት አራቱም ቡድኖች የማለፍ ዕድል አላቸው።
አፍሪቃዊቷ ሴኔጋል ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን አረጋገጠች
ምድቡን ስፔን በ4 ነጥብ ትመራለች። ጃፓን እና ኮስታሪካ 3 ነጥብ ይዘው በግብ ክፍያ ነው የሚበላለጡት። ጀርመን 1 ነጥብ ብቻ አለው፤ አንድ የግብ እዳም አለበት። በፊፋ የዓለም ዋንጫ ታሪክ እንደ ጣሊያን 4 ዋንጫዎችን በመውሰድ በስኬት ሁለተኛው የሆነው የጀርመን ቡድን ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፍ ይጠበቅበታል። ያም ብቻ አይደለም፤ በተመሳሳይ ሰዓት የሚደረገውን ሌላ ግጥሚያ ውጤት መጠበቅ ይኖርበታል።
ስፔን ኮስታሪካን 7 ለ0 ድባቅ መታ
ባለፈው የዓለም ዋንጫ የጀርመን ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ወደ ቀጣዩ የጥሎ ማለፍ ውድድር ማለፍ ሳይችል በምድብ ማጣሪያው መሰናበቱ ይታወሳል። በዓለም ዋንጫ ታሪክ ብራዚል እስካሁን 5 ዋንጫዎችን በመሰብሰብ የሚስተካከላት አልተገኘም። በሁሉም የዓለም ዋንጫ ውድድሮች ላይ በመሳተፍም ብቸኛዋ ሀገር ናት። ከምድቧ 1ኛ ሆና ማለፏን ብታረጋግጥም ነገ ማታ ካሜሩንን ትገጥማለች።
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ታምራት ዲንሳ
እሸቴ በቀለ