ከሜጀር ጄነራል ክንፈ ጋር 7 ተጠርጣሪዎች ችሎት ቀርበዋል
ረቡዕ፣ ኅዳር 5 2011ማስታወቂያ
በሁመራ በኩል ከሀገር ሊወጡ ሲሉ በቁጥጥር ስር እንደዋሉ የተነገረላቸው እና ትላንት ወደ አዲስ አበባ እንዲመጡ የተደረጉት የብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄነራል ክንፈ ዳኘው ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። ከእርሳቸው ጋር የኢትዮ ቴሌኮም የስራ ኃላፊ የነበሩት ወንድማቸው ኢሳይያስ ዳኘው እና የቀድሞ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ፍጹም የሺጥላን ጨምሮ በድምሩ ስምንት ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀርበዋል።
ዘገባውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።
ዩሃንስ ገብረ እግዚያብሔር
ነጋሽ መሐመድ