ሜርክልን ለመተካት የሚወዳደሩት እጩዎች የውጭ ፖሊሲ
ማክሰኞ፣ ሰኔ 22 2013የፊታችን መስከረም 16 ቀን2014 ዓም በጎርጎሮሳዊው መስከረም 26፣2021 ዓም የሚካሄደው የጀርመን አጠቃላይ ምርጫ እስካሁን በሥልጣን ለቆዩት ለመራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል የመጨረሻው ነው።በመስከረሙ አጠቃላይ ምርጫ የሚያሸንፈው ፓርቲ አዲስ መራኄ መንግሥት ይሰይማል።በዚህ አጠቃላይ ምርጫ፣መራኄ መንግሥት አንጌላ ሜርክልን ሊተኩ ይችላሉ ተብለው የሚገመቱት፣ የሜርክል ፓርቲ ፣ የክርስቲያን ዴሞክራት ኅብረት በምህጻሩ CDU እጩ አርሚን ላሼት፣ የጥምር መንግሥቱ አካል የሶሻል ዴሞክራቶች ፓርቲ በጀርመንኛው ምህጻር SPD እጩ ኦላፍ ሾልትዝ እንዲሁም የአረንጓዴዎቹ ፓርቲ እጩ አናሌና ቤርቦክ ናቸው።እነዚህ ሦስት እጩ ተወዳዳሪዎች ባለፈው ሰሞን በተካሄደ መድረክ ላይ በተነሱላቸው ጥያቄዎች የሚያራምዱትን የጀርመን የውጭ የፖለቲካ መርሃቸውን ይፋ አድርገዋል። ሰፊ ተቀባይነት ያላቸው የሦስቱ ፓርቲዎች እጩዎች በዚሁ መድረክ ጀርመን በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ሚናዋ ምን እንደሆነ ተጠይቀው ነበር። ባለፈው አርብ በአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት ማሊ ከዘመቱ የጀርመን ወታደሮች አስራ ሁለቱ ቆስለዋል።የጀርመን ወታደሮች ማሊ የተሰማሩት በተባበሩት መንግሥታት የማሊ ተልዕኮ እና በአውሮጳ ኅብረት የስልጠና መርሃ ግብር ስር ነው።ለእጩ ተወዳዳሪዎቹ ከቀረበላቸው ጥያቄዎች አንዱ በቅርቡ ማሊ እንደደረሰው ፣ሁኔታዎች አደገኛ ሲሆኑ ከዚህን መሰሉ ተልዕኮ መራቅ አይሻልም የሚል ነበር።የSPDው እጩ ኦላፍ ሾልትዝ የለም ሲሉ ነበር የመለሱት።ሾልትዝ የጀርመን ወታደሮች በውጭ ሃገራት ተልዕኮዎች ውስጥ መሰማራታቸውን ይደግፋሉ ።
በዚህ አጠቃላይ ምርጫ፣መራኄ መንግሥት አንጌላ ሜርክልን ሊተኩ ይችላሉ ተብለው የሚገመቱት፣ የሜርክል ፓርቲ ፣ የክርስቲያን ዴሞክራት ኅብረት በምህጻሩ CDU እጩ አርሚን ላሼት፣ የጥምር መንግሥቱ አካል የሶሻል ዴሞክራቶች ፓርቲ በጀርመንኛው ምህጻር SPD እጩ ኦላፍ ሾልትዝ እንዲሁም የአረንጓዴዎቹ ፓርቲ እጩ አናሌና ቤርቦክ ናቸው።እነዚህ ሦስት እጩ ተወዳዳሪዎች ባለፈው ሰሞን በተካሄደ መድረክ ላይ በተነሱላቸው ጥያቄዎች የሚያራምዱትን የጀርመን የውጭ የፖለቲካ መርሃቸውን ይፋ አድርገዋል። ሰፊ ተቀባይነት ያላቸው የሦስቱ ፓርቲዎች እጩዎች በዚሁ መድረክ ጀርመን በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ሚናዋ ምን እንደሆነ ተጠይቀው ነበር። ባለፈው አርብ በአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት ማሊ ከዘመቱ የጀርመን ወታደሮች አስራ ሁለቱ ቆስለዋል።የጀርመን ወታደሮች ማሊ የተሰማሩት በተባበሩት መንግሥታት የማሊ ተልዕኮ እና በአውሮጳ ኅብረት የስልጠና መርሃ ግብር ስር ነው።ለእጩ ተወዳዳሪዎቹ ከቀረበላቸው ጥያቄዎች አንዱ በቅርቡ ማሊ እንደደረሰው ፣ሁኔታዎች አደገኛ ሲሆኑ ከዚህን መሰሉ ተልዕኮ መራቅ አይሻልም የሚል ነበር።የSPDው እጩ ኦላፍ ሾልትዝ የለም ሲሉ ነበር የመለሱት።ሾልትዝ የጀርመን ወታደሮች በውጭ ሃገራት ተልዕኮዎች ውስጥ መሰማራታቸውን ይደግፋሉ ።
«ይህ ወደፊትም ልንወጣው የሚገባ ትልቅ ተግባር ነው። ለዚህ ዝግጁ ነን።ለዚህም አስፈላጊው ክህሎት አለን»
የCDU እና የአረንጓዴዎቹ እጩዎች ላሼትና ቤርቦክም ይህን አይቃወሙም።ግን ቤርቦክ ቢያንስ የጀርመን ወታደሮች ለማሊ ወታደሮች ስልጠና መስጠታቸው እንዲቆም ይፈልጋሉ።ያም ሆኖ ሜርክልን ሊተኩ ይቻላሉ ተብለው የሚታሰቡት የሦስቱ እጩዎች አብዛኛዎቹ የውጭ ፖሊሲዎቻቸው ተቀራራቢ ናቸው።ሦስቱም በዓለም አቀፍ ስምምነቶችና ድርጅቶች ያምናሉ።ጀርመንም በዓለም መድረክ ከአሁኑ የተሻለ ንቁ ተሳትፎና ሚና እንዲኖራት ይፈልጋሉ።ሦስቱም ጀርመንን ለ16 ዓመታት የመሩት አንጌላ ሜርክል ይከተሉ ከነበሩት የጀርመን የውጭ የፖለቲካ መርህ እምብዛም ርቀው አልተገኙም የዶቼቬለው ፔተር ሄለ እንደዘገበው።ለምሳሌ የአውሮጳ ኅብረትን ማጠናከርን በሚመለከተው ጉዳይ ወደፊት አባል ሃገራት በተናጠል የውጭ የፖለቲካ መርኅ ውሳኔዎችን እንዲያግዱ አይፈልጉም።
የአውሮጳ ኅብረት አባል ሀገር ሃንጋሪ በቅርቡም ሆነ በቀደሙት ጊዜያት ቻይና በሆንግኮንግ የዴሞክራሲ መርሆች እንዲጠፉ ስታደርግ ኅብረቱ ቻይናን እንዳያወግዝ ሃንጋሪ ስትከላከል ቆይታለች።ሦስቱ እጩዎች ማለትም ላሼት፣ባርቦክና ሾልትስ ለኅብረቱ አባል ሃገራት የተሰጠው እንዲህ ዓይነቱ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብት እስከ ጎርጎሮሳዊው 2025 ዓም ድረስ እንዲነሳ ይፈልጋሉ። ሆኖም ይህ የጀርመን ፖለቲከኞች ፍላጎት ይህ የነበረ ቢሆንም ላለፉት አሥርት ዓመታት እውን መሆን አልቻለም።ከኅብረቱ አባል ሃገራት መሪዎች አስቸጋሪ ከሚባሉት ከሃንጋሪው ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኡርባን ጋር ታዲያ ግንኙነቱ እንዴት ቢሆን ነው የምትመርጡት? ለሦስቱም የቀረበ ጥያቄ ነበር። የሶሻል ዴሞክራቶቹ እጩ ሾልትስና የክርስቲያን ዴሞክራት ኅብረት ፓርቲ እጩ ላሼት የተለሳለሰ መልስ ሲሰጡ የአረንጓዴዎቹ ፓርቲ እጩ ቤርቦክ ግን ከሁለቱ በተለየ ቆንጠጥ የሚያደርግ እርምጃ እንዲወሰድ እንደሚሹ ነው ያሳሰቡት።በተለይ በሰዎች የጾታዊ መስተጋብር ዝናባሌ ላይ አድሎዎ ያደርጋሉ የሚባሉ የሃንጋሪ ሕጎችን በመቃወም ባርቦክ የአውሮጳ ኅብረት ለሃንጋሪ የሚሰጠውን ድጋፍ በተቻለ ፍጥነት እንዲያቆም እንደሚፈልጉ ነው ያስረዱት።
« እንደዚህ ሊቀጥል አይችልም። መርሆቻችንን በገዛ እግራችን ልንረግጣቸው አይገባም።»ሲሉ
ባርቦክ ከሁለቱ ተፎካካሪዎቻቸው በተለየ በህዝብ ዘንድ ያላቸው ተቀባይነት ጥያቄ ውስጥ ይገባል።ከርበር የተባለ የጥናት ተቋም ባካሄደው የዳሰሳ ጥናት ጀርመናውያን በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ከቤርቦክ ይልቅ በላሼትና በሾልትስ ይበልጥ ይተማመናሉ። የተቋሙ የበርሊን ቢሮ ሃላፊ ኖራ ምዩለር ፣ ምክንያቱን ለዶቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ አስረድተዋል።
« ቤርቦክ ቀላል የማይባል የውጭ የፖለቲካ መርህ ብቃትም ይሁን ልምዳቸውን ያካፍላሉት።ሆኖም እርሳቸው በመንግሥት መስሪያ ቤቶች በሃላፊነት አልሰሩም።በተቃራኒው ኦላፍ ሹልትዝ በገንዘብ ሚኒስትርነት በርከት ያሉ ዓለም አቀፍ ልምዶች አሏቸው። አርሚን ላሼትም ከጀርመን ትላልቅ ክፍለ ግዛቶች የአንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር እንደመሆናቸው ከአውሮጳውያን ጋር ግንኑነታቸው የሰፋ ነው።ይህ ምናልባትም እንደጥናቱ ቤርቦክ የሚቀጡበት ነጥብ ነው የሚሆነው።»
ቤርቦክ ከፈላጭ ቆራጮች ግልጽ መስመር አስምረው መለየት ይፈልጋሉ።በቻይና ህዳጣኖች በኃይል ተገደው የሚሰሯቸው የቻይና ምርቶች ላይ እገዳ እንዲጣል ይሻሉ።ሾልትስ እና ላሼትደግሞ በተቃራኒው ከቻይና ጋር በመቀራረብ ለውጥ ማምጣት ነው የሚፈልጉት።ይህም ጀርመንን በመራሄ መንግሥትነት የመሩት ቪየሊ ብራንት በ1960ዎቹና በ1970ዎቹ በሶቭየት ኅብረትና ምሥራቅ አውሮጳ ሃገራት ያራምዱት የነበረው የፖለቲካ መርህ ነው።የፍራንክፈርት ነዋሪ ፣የፖለቲካ ሳይንቲስ ምሁር ጉንተር ሄልማን ቤአነሌና ቤርቦክርቦክ በፈላጭ ቆራጮች ላይ የያዙትን አቋም ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አቋም ጋር ያመሳስሉታል።በተለይ ከሩስያ ወደ አውሮጳ ጋዝ የሚተላለፍበት ፕሮጀክት ላይ የያዙትን አቋም።
«አረንጓዴዎቹ፣ከሩስያ ወደ አውሮጳ ጋዝ የሚተላለፍበት Nord Stream ሁለት በሚባለው ፕሮጀክት ላይ በግልጽ ተቃራኒ አቋም ይዘዋል።ሆኖም የኛ ጥናት እንደሚያመለክተው የአብዛኛው ጀርመናዊ ድጋፍ የላቸውም።የጀርመን ዜጎች ይህን ፕሮጀክት በንጽጽር በአዎንታዊነት እና በእርግጠኝነት ይቀበሉታል። እናም «ኖርድ ስትሪም ሁለት» በጥቅሉ ከሩስያ ጋር በተለያየ መንገድ የሚያገናኝ መለያ ነው። »
የአሜሪካን ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የባልቲክ ባህር ላይ ከሩስያ ወደ አውሮጳ ጋዝ ለማስተላለፍ የሚዘረጋው መስመር ግንባታ እንዲቆም ነው የሚፈልጉት።አሜሪካን ይህን አውሮጳን ከሩስያ ጋር የሚያቀራርብ ፕሮጀክት ቀልብዋ አልፈቀደውም።ቤርቦክም ከባይደን ጋር ተመሳሳይ አቋም ነው ያላቸው። በቅርቡ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ የሩስያ ጋዝ ወደ ጀርመን መተላለፍ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል ። የባርኮክ ስጋት የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እስካሁን ጋዙ የሚያልፍባትን ዩክሬንን ተጨማሪ ጫና ውስጥ ይከቷቷል የሚል ነው።አዲሱ መስመር ሲዘረጋ ፑቲን እስካሁን ጋዝ በሚተላለፍባት ዩክሬን ላይ ጫና ሊያሳድሩ ይችላሉ የሚል ስጋት አለ ።የዚህ ጋዝ ማስተላለፊያ ግንባታ በዘሁኑ ጊዜ በርሊንና ዋሽንግተን የሚያጋጭ ጉዳይ ሆኗል።ከባርኮክ በተቃራኒ የCDU ና የSPD እጩ ተወዳዳሪዎች የጋዝ ማስተላለፊያው ሥራ እንዲጀምር ይፈልጋሉ።ሆኖም የጀርመን ክርስቲያን ዴሞክራት ኅብረት ፓርቲ እጩ አርሚን ላሼት በዚህ ሰበብ ዩክሬን ችግር ውስጥ እንድትወድቅ አይፈልጉም ።
«ይህ ዩክሬን እየተጎዳች መሆን የለበትም።ፕሬዝዳንት ፑቲን ይህን ካደረጉ ና ዩክሬንን ለመጉዳት ከተጠቀሙበት የጋዝ ማስተላለፊያ መስመሩ ስራ ከጀመረ በኋላ በማንኛውም ጊዜ ማስቆም ይቻላል።»
በርሊንና ዋሽንግተን በኖርድ ስትሪም 2 ጉዳይ አንድ መግባቢያ ላይ ለመድረስ በአሁኑ ጊዜ እየተደራደሩ ነው።ይህም የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩ ሄልማን እንደሚሉት ሜርክል በሚቀጥለው ወር መጀመሪያ ላይ ባይደንን ሲጎበኙ የሚካሄድ ሳይሆን አይቀርም።ጀርመን ከአጠቃላይየሀገር ውስጥ ዓመታዊ ገቢዋ 1.56 በመቶውን ለመከላከያ ወጭ ታደርጋለች።ላሼትና ሾልትስ። ይህን ወደ 2 በመቶ ማሳደግ ይፈልጋሉ።ቤርቦክ ግን ይህን ያህል በመቶውን ለመከላከያ አውላለሁ የሚል ቃል መግባት አልፈለጉም ።ያም ሆኖ የመከላከያው ብቃት ከፍ እንዲል እንደሚፈልጉ አሳውቀዋል።የሦስቱም እጩዎች የውጭ ፖሊሲ በአብዛኛው ይመሳሰላል ይላሉ የውጭ ፖሊሲ ጉዳዮች አዋቂ ሄልማን ።
« የውጭ የፖለቲካ መርሃቸው በግልጽ የሚመሳሰል ሦስት እጩዎች አሉ። ከዚህ ሌላ ግን ዓለም አቀፍ ንግድን በሚመለከት እንደ ዶናልድ ትራምፕ ልምድ የሌላቸው አይደሉም።»
ስለዚህ የጀርመን አጋሮች ስለ መስከረሙ ምርጫ ሊሰጉ አይገባም ይላል የዶቼቬለው ፒተር ሄለ ዘገባ ።
ፔተር ሄለ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ