ሐንጋሪ በስተመጨረሻ የአውሮጳ ኅብረት ለዩክሬን ገንዘብ እንዲሰጥ ፈቀደች
ሐሙስ፣ ጥር 23 2016የአውሮጳ ኅብረት አባል ሀገራት መሪዎች ዛሬ ብራሰልስ ውስጥ ባካሄዱት ጉባኤ ለዩክሬን ተጨማሪ የ50 ቢሊዮን ዩሮ እርዳታ ለመስጠት ተስማሙ። የኅብረቱ የመሪዎች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ቻርል ሚሼል በትዊተር እንዳስታወቁት ሀያ ሰባቱም የኅብረቱ አባል ሀገራት በሙሉ ከኅብረቱ በጀት ለዩክሬን ተጨማሪ 50 ቢሊዮን ዩሮ የእርዳታ ማዕቀፍ ለመስጠት ተስማምተዋል።
ሚሼል ስምምነቱ ለዩክሬን በፍጥነት የተሰጠ ዘላቂ ድጋፍ መሆኑን ገልጸው የአውሮጳ ኅብረትም በዩክሬን ጉዳይ የመሪነቱን ቦታና ሃላፊነቱንም እየወሰደ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
የዩክሬን ፕሬዝዳን ት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ ስምምነቱን በደስታ ተቀብለዋል። ዜልንስኪ እርዳታው የሀገራቸውን የምጣኔ ሀብትና ፋይናንስ መረጋጋት በዘላቂነት ያጠናክራል ብለዋል።ለዩክሬን ሊሰጥ በቃቀደው በዚህ እርዳታ ላይ ባለፈው ታህሳስ የአባል ሀገራት መሪዎች ሲነጋገሩ እቅዱን የሀንጋሪው ፕሬዝዳንት ቪክቶር ኦርባን ውድቅ አድርገውት ነበር።
የኅብረቱ አባል ሀገራት ለሳምንታት ከኦርባን ጋር ሲወዛገቡ ከቆዩ በኋላ ነበር ዛሬ የተስማሙት። ጉባኤው ከመጀመሩ አስቀድሞ የኅብረቱ አባል ሀገራት መሪዎች ኦርባን ጫናውን በማንሳት ድጋፋቸውን እንዲሰጡ ግፊት ካደረጉባቸው በኋላ ለዩክሬን ርዳታ እንዲሰጥ ሐንጋሪ ተስማምታለች። የሐንጋሪ ጠቅላይ ሚንስትር ቪክቶር ኦርባን የአውሮጳ ኅብረት ለዩክሬን ሊሰጥ ያቀደውን የ50 ቢሊዮን ዩር የገንዘብ ድጋፍ ሀገራቸው ስታከላክል የቆየችው ስለገንዘቡ ዋስትና ባለማግኘቷ መሆኑን ተናግረዋል ። ሐንጋሪ የተጨነቀችውም ለሐንጋሪ የሚገባው ገንዘብ ወደ ዩክሬን ይሄዳል ብላ ነበር ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትሯ ። በእርግጥ በአውሮጳ ኅብረት እና የኅብረቱ አባል በሆነችው ሐንጋሪ መካከል ዩክሬንን በተመለከተ የውዝግቡ ምክንያት ምንድን ነበር?
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ