“ህዝብን የሚገድል ጠላት ነዉ” የጉጂ አባገዳዎች ህብረት
ዓርብ፣ መስከረም 7 2014ማስታወቂያ
የጉጂ ኦሮሞ አባገዳዎች ህብረት በደቡባዊ የኦሮሚያ ዞኖች የኦሮሞ ህዝብን አሰቃቂ በሆነ መንገድ ይገድላል ያለዉን የትኛውንም ቡድን በጠላትነት ፈረጀ፡፡ በአከባቢው በተደጋጋሚ በሚስተዋለው የፀጥታ መድፈረስ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያለፈ የመጣው የሰው ህይወት እያሳሰበን ነው ያለዉ የአባገዳዎቹ ህብረት በምዕራብ ጉጂ ዞን ሰሞኑን ባካሄደዉ የሰላም ጉባኤ ነው ውሳኔውን ያስተላለፈዉ፡፡ የኦሮሞ አባገዳዎች ህብረት ሰብሳቢ እና የጉጂ አባገዳ ጅሎ ማንኦ በተለይም ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት ከእንግዲህ በአከባቢው የሰው ሕይወትን በሚያጠፉት ላይ በገዳ ስርዓት ውሳኔ ውግዘት ታውጇል ነው ያሉት፡፡
ስዩም ጌቱ
አዜብ ታደሰ
እሸቴ በቀለ