1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመን የካናቢስ ዕጽ በውስን ሁኔታ ጥቅም ላይ እንዲውል መፍቀዷ

ማክሰኞ፣ መጋቢት 24 2016

የጀርመን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወይም ቡንደስታግ ካናቢስ የተሰኘውን አደንዛዥ ዕዝ ፤በውስን ሁኔታ በግል መጠቀም የሚያስችል ህግ ትናንት ሰኞ አጽድቋል። ህጉ ለጀርመናውያን ካናቢስ የተሰኘውን አደንዛዥ ዕዝ በውስን መጠን የማምረት ፣ የመያዝ እና የመጠቀም መብት እንደሚያጎናጽፍ ተገልጿል።

https://p.dw.com/p/4eLsW
Deutschland | Freude über Teillegalisierung von Cannabis in Berlin
ምስል Fabian Sommer/dpa/picture alliance

የጀርመን ቡንደስታግ ካናቢስ የተሰኘውን አደንዛዥ ዕዝ መጠቀም የሚያስችል ህግ አጸደቀ

የጀርመን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወይም ቡንደስታግ ካናቢስ የተሰኘውን አደንዛዥ ዕዝ ፤በውስን ሁኔታ በግል መጠቀም የሚያስችል ህግ ትናንት ሰኞ አጽድቋል። ህጉ ለጀርመናውያን ካናቢስ የተሰኘውን አደንዛዥ ዕዝ በውስን መጠን የማምረት ፣ የመያዝ እና የመጠቀም መብት እንደሚያጎናጽፍ ተገልጿል። ህጉ መጽደቁን ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ የዕጹ ተጠቃሚዎች በእሁለ ሌሊት በርሊን ብራደንበርግ አደባባይ ወጥተው ደስታቸውን ሲገልጹ ታይተዋል። በአሜሪካ ማሪዋናን እንደመድኃኒት
የህጉ መጽደቅ  በመራሄ መንግስት  ኦላፍ ሾልስ ጥምረት ውስጥ ያለውን ሌላ መሰናክል ያስወግዳል የሚል እምነት ተጥሎበታል።
 ተቃዋሚው የክርስትያን ዴሞክራቶች ህብረት ግን የህጉን መጽደቅ አጥብቆ ኮንኗል፤ በቀጣዩ ምርጫ ስልጣን ከያዘ ወዲያው ከህጉ እንደሚፍቅ ግልጽ አድርጓል። ምንም እንኳ አንዴ ከተፈቀደ መመለሱ አስቸጋሪ ሳይሆን እንደማይቀር ግን አስቀድሞ ተጠቁሟል ።  
ይልማ ኃይለሚካኤል
ታምራት ዲንሳ
እሸቴ በቀለ