ማስታወቂያ
ውህደቱን በተመለከተ በቅርቡ ይፋ የተደረገ ዘገባ ግን አሁንም በምዕራብና በምሥራቅ ጀርመን ልዩነቶች መኖራቸውን ያመለክታል። ዘገባው ምሥራቅና ምዕራብ ጀርመንን አንድ ከሚያደርጓቸው ይልቅ የሚለያይዋቸው ያመዝናሉ ይላል። የጀርመን መንግሥት ደግሞ ውህደቱ ባለፉት 33 ዓመታት ብዙ አጥጋቢ ውጤቶችን ማስገኘቱን ይናገራል። ሆኖም የምሥራቁም የምዕራብ ጀርመንም የእድገት ደረጃ የተስተካከለ እንዲሆን መሰራት እንዳለበት ያምናል። በዚህ ጉዳይ ላይ ዶቼቬለ ያነጋገራቸው የፌደራል መንግሥቱ የምሥራቅ ጀርመን ኮሚሽነር ካርስተን ሽናይደር በአሁኑ ጊዜ በምሥራቅ ጀርመን የተመዘገበውን የኤኮኖሚ እምርታ አወድሰዋል። ኮሚሽነሩ በጀርመን ፖለቲካዊው ውህደት መሳካቱን ገልጸው አሁንም ምዕራብና ምሥራቅ ጀርመንን የሚለዩ መስመሮች መኖራቸውን ግን አልሸሸጉም