የዳያስፖራ ኤጀንሲ
ዓርብ፣ ታኅሣሥ 26 2011ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዳያስፖራ ኤጀንሲን የማዋቀር ሥራ መጠናቀቁን አስታወቀ። የኤጀንሲው ዋና ሃላፊ ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት እንዳሉት ከኤጀንሲው ዋና ዋና ተግባራት መካከል በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን መብት እና ጥቅሞቻቸውን ለማስጠበቅ የሚረዱ ሥራዎችን ማከናወን ይገኝበታል። ከዚሁ ጋር ከዳያስፖራው የሚገኝ የዕውቀት የክህሎት እና የቴክኖሎጂ ሽግግርም ትኩረት የሚሰጣቸው ጉዳዮች ናቸው። ከውጭ የሚመጡ ኢትዮጵያውያንን የፖለቲካ መብት ማስከበር እና የፖለቲካ ተሳትፎአቸውንም ማሳደግ በኤጀንሲው ተልዕኮዎች መካተቱ ተገልጿል። ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ከአዲስ አበባ ዝርዝሩን ልኮልናል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ