1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዳሎል ጨዉ አምራቾችና ነጋዴዎች ቅሬታ

ማክሰኞ፣ ጥር 26 2012

በዳሎል አካባቢ በባሕላዊ መንገድ ጨዉ የሚያመርቱና የሚነግዱት ሰዎች እንደሚሉት ለገበያ ለማቅረብ መኪና ላይ የጫኑት የጨዉ ምርት  በራሕሌ ዉስጥ  ታግዶባቸዋል።

https://p.dw.com/p/3XG4S
Äthiopien l Keine Weiterreise für Salzhändler nach Tigrai
ምስል DW/M. Haileselassie Brhane

የዳሎል ጨዉ አምራቾችና ነጋዴዎች ቅሬታ

በአፋር ክልል ዳሉል ወረዳ የሚገኙ ጨው አምራቾችና ነጋዴዎች  ምርታቸዉን እንዳይሸጡ የክልሉ መንግስት «ከለከለን» አሉ። በዳሎል አካባቢ በባሕላዊ መንገድ ጨዉ የሚያመርቱና የሚነግዱት ሰዎች እንደሚሉት ለገበያ ለማቅረብ መኪና ላይ የጫኑት የጨዉ ምርት  በራሕሌ ዉስጥ  ታግዶባቸዋል።የጨዉ ምርቱን የጫኑ ተሽከርካሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ከታገዱ ሶስት ቀናት ማለፉንም ቅሬታ አቅራቢዎቹ ተናግረዋል።የአካባቢው  ባለስልጣናት  ግን ጨዉ አምራቾቹና ነጋዴዎቹ በመግሥት ሕጋዊ ፈቃድና እዉቅና አልተሰጣቸዉም ይላሉ።የታገዱትም መኪኖች መለቀቃቸዉን አስታዉቀዋል።በዳሎል ወረዳ በጨዉ ማምረት፣ ማዘጋጀትና መነገድ ሥራ ከ10 ሺሕ በላይ ህዝብ ይተዳደራል።

ሚሊዮን ኃይለ ስላሴ 

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ