ማስታወቂያ
የሚያዝያ 13 ቀን 2016 ዓ/ም አርዕስተ ዜና
በማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ የተሳፈሩበት የእንጨት ጀልባ በመስመጧ ወንዝ ውስጥ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ቢያንስ 58 ደረሰ። የጀልባዋ መስመጥ መንስኤ ከአቅም በላይ ሰዎችን ማሳፈሯ ነበር።
እስራኤል በደቡባዊ ጋዛ በምትገኘው ራፋህ ከተማ ሌሊቱን በሰነዘረችው ጥቃት 18 ሰዎች ተገደሉ ። በጥቃቱ ከሞቱት መካከል 14ቱ ህጻናት መሆናቸውን የጤና ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።
ዩክሬንን ለመርዳት ትናንት የዩናይትድ ስቴትስ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተስማማበትን የርዳታ ጥቅል የውሳኔ ረቂቅ የጀርመን መንግሥት አወደሰ።
ዛሬ በተካሄደው 41ኛው የቪየና ከተማ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊው ጫላ ረጋሳ አንደኛ በመሆን አሸነፈ። በ 44ኛው የለንደን ማራቶን ውድድርም ኢትዮጵያዊያኑ አትሌቶች በወንዶች ቀነኒሳ በቀለ ፤ በሴቶች ደግሞ ትዕግስት አሰፋ ተጠባቂውን ውድድር ሁለተኛ በመሆን አጠናቀዋል።