አውሮጳ ሕብረት እና የቻይና ጉባኤ
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 2 2011ማስታወቂያ
የአውሮጳ ሕብረት እና ቻይና በኢኮኖሚያዊ ግንኙነታቸው ላይ የመከሩበት የጋራ ጉባኤ ትናንት ተካሂዶ መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል። የአውሮጳ ሕብረት በሕብረቱ የመሪዎች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ቱስክ እና በህብረቱ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ዦን ክሎድ ዩንከር፣ቻይና ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትሯ በሊ ኬክያን በተመራ ልዑካን የተወከሉበት ድርድር አስቸጋሪ እንደነበረ ቢገልጽም ውጤቱ ግን የሰመረ እንደሆነ ተነግሯል። ከጉባኤው በፊት ዩንከር በአውሮጳ የሚሰሩ የቻይና ኩባንያዎች የተሰጣቸው መብት ቻይና ውስጥ ለሚንቀሳቀሱ የአውሮጳ ኩባንያዎችም ሊሰጣቸው ይገባል ሲሉ አሳስበው ነበር። ቻይና በበኩልዋ በሯን ይበልጥ ክፍት በማድረግ ከአውሮጳ ሕብረት ጋር ያላትን የኤኮኖሚ ትስስር እንደምታጠብቅ አስታውቃለች። ገበያው ንጉሤ ከብራሰልስ ዝርዝሩን ልኮልናል።
ገበያው ንጉሴ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ