1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሜሪካን ማሳሰቢያ እና ተቃውሞው

ሰኞ፣ የካቲት 23 2012

ኢትዮጵያ ስለ ህዳሴው ግድብ ስምምነት ላይ ሳይደረስ የመጨረሻ ሙከራ እንዳታደርግና የውኃ ሙሌት እንዳትጀምር ከአሜሪካን የተሰጠው ማሳሰቢያ የሀገሪቱን ሉዓላዊነት የሚጎዳ ነው ሲሉ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁራን እና ፖለቲከኞች ተቃወሙ።ምሁራኑ ኢትዮጵያ በታችኛዎቹ የተፋሰሱ ሃገራት ላይ ጉዳት ሳታደርስ አባይን የመጠቀም መብቷን ልትከለከል አይገባምም ብለዋል።

https://p.dw.com/p/3YloD
Grand Ethiopian Renaissance Dam
ምስል picture-alliance/dpa/G. Forster

የዩናይትድ ስቴትስ ግምጃ ቤት ባለፈው ቅዳሜ ስለ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ያወጣው መግለጫ በርካታ ኢትዮጵያውያንን አስቆጥቷል። ኢትዮጵያ ስለ ህዳሴው ግድብ ስምምነት ላይ ሳይደረስ የመጨረሻ ሙከራ እንዳታደርግ እና የውኃ ሙሌትም እንዳትጀምር ከአሜሪካ መንግሥት የተሰጠው ማሳሰቢያ የሀገሪቱን ሉዓላዊነት የሚጎዳ ነው ሲሉ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁራን እና ፖለቲከኞችም ተቃውመውታል።ምሁራኑ ኢትዮጵያ የአባይ ተፋሰስ የታችኛዎቹ ሃገራት ላይ የከፋ ጉዳት ሳታደርስ በተፈጥሮ ሀብቷ የመጠቀም መብቷን ማንም ሊከለለላት አይገባምም ብለዋል። የአሜሪካን ግምጃ ቤት ኢትዮጵያ ካልተካፈለችበት ስብሰባ በኋላ «የህዳሴ ግድብን የመጀመሪያ የውኃ ሙሌት እና የውኃ አለቃቀቅ እና ደንብ ለማዘጋጀት የሚደረገው ድርድር ተጠናቋል» ሲል ያወጣውን መግለጫ ኢትዮጵያ ውድቅ አድርጋለች።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ