1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቻይና እና የአፍሪቃ የንግድ ግንኙነት

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 29 2006

የቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ የቻይና እና የአፍሪቃ የንግድ ግንኙነት ይበልጥ በእኩልነት ላይ የተመረኮዘ እንደሚሆን ተናግረዋል። የቻይናእና የአፍሪቃ ፤ በተለይም የቻይናና የኢትዮጵያ የንግድ ግንኙነት እንዴት ይገመገማል?

https://p.dw.com/p/1BujL
China Einfluss in Afrika Baustelle in Addis Abeba Äthiopien
ምስል Getty Images

አፍሪቃን በንግድ አጋርነት ሙሉ በሙሉ ከጎኗ ያሰለፈችው ቻይና በበኩሏ ይበልጥ ግንኙነቷን አስፋፍታ እና አጠናቅራ ለመቀጠል ወስናለች። የአፍሪቃ ሀገራትስ? ቢያንስ ኢትዮጵያ በርካታ ቀጣይ የንግድ ስምምነቶችን መፈራረሟ ተሰምቷል። ሊ ኬኪያንግ የአፍሪቃ ህብረትን በጎብኙበትም ጊዜ ሀገራቸው በፈጣኑ ባቡር ረገድ ያለውን ዘመናዊ ሥነ ቴክኒክ ለአፍሪቃውያን ለማካፈል ዝግጁ መሆንዋን እና እስካሁን 20 ቢሊዮን ዶላር የነበረው የብድር መጠን በ10 ቢሊዮን ከፍ እንደሚል ሊ መናገራቸውን የቻይና ዜና ወኪል ሺንዋ ገልጸዋል። ሊ ኢትዮጵያን በመጀመሪያ የጎበኙበት በርካታ ምክንያቶች አሉ ይላሉ አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ።አቶ ዘመዴነህ ዓለም አቀፍ በሆነው የኤርንስት ኤንድ ያንግ የቢዝነዝ አማካሪ ድርጅት የኢትዮጵያው ቅርንጫፍ ኃላፊ ናቸው። እንደ እሳቸው አመለካከት የቻይና እና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ምን ያህል ጠንካራ እንደሆነ ለማየት ከሌሎች የአፍሪቃ አገራት ጋ አነፃፅሮ መመልከት ያስፈልጋል።

የቻይና በአፍሪቃ በተለይም በማዕድን እና በድፍድፍ ነዳጅ ዘይት በታደሉ ሀገራት ላይ ማተኮር፤ቻይናን በከፍተኛ ሁኔታ በተለይም በምዕራቡ ሀገራት እያስተቻት ይገኛል። ቻይና በአፍሪቃ ሀገራት የማዕድን ብዝበዛ እንደምታካሂድ እና የሰራተኞች መብትን እንደማትጠብቅ ከሚሠነዘሩ ወቀሳዎች ጥቂቶቹ ናቸው። በቦን ዮንቨርሲቲ ስለ ቻይና እና ኢትዮጵያ ግንኙነት ዶክትሬቱን የሚሰራው አሌክሳንደር ደምሴ ደብረዘይት መንገድ ላይ የሚገኘውን የቻይና ትልቁን የሴቶች ጫማ አምራች ሁዣን ፋብሪካን ጎብኝቷል። የሰራተኞቹ ይዞታ ምን እንደሚመስል የተመለከተውን ገልፆልናል። አሌክሳንደር እንደገለፀው ለሰሪውም ይሁን ለአሰሪው አንዳንድ ያልተሟሉ ነገሮች እንዳሉ ለመረዳት ችለናል።ስራው ግን እንደቀጠለ ነው። በሁለቱም ሀገራት መካከል ጥብቅ ግንኙነት አለ። በበርካታ የአፍሪቃ ሀገራት ከአፍሪቃ ጋር ስላላቸው ግንኙነት ለታዘቡት አቶ ዘመዴነህ ቻይና በኢትዮጵያ ባላት እንቅስቃሴ ጠንካራ ጎኑ ብቻ ነው የሚታያቸው።

Chinesisches Restaurant in Maputo
የቻይና ሬስቶራንት በሞዛምቢክ፤ ማፑቶምስል DW/J. Beck

ሊ ኬኪያንግ በአዲስ አበባ የአፍሪቃ ህብረት ባሰሙት ንግግር ከሀገራቸው ጋር ያለው የንግድ መጠንን እኢአ በ2020 አሁን ካለው 200 ቢልዮን በጥፉ እንደሚጨምር ተናግረዋል። የአፍሪቃ ሀገራት የቻይናን መውዓለ ንዋይ ሲያወድሱ አንዳንድ ምዕራባዊያን ሀገራት ግን ቻይናን ይተቻሉ።

Li Keqiang Präsident China Besuch in Äthiopien mit Hailemariam Desalegn
ምስል Reuters

እርግጥ ነው። ለምሳሌ ኢትዮጵያ ውስጥ ቻይና የምታመርታቸው ጫማዎች እንደ ዮናይትድ ስቴትስ ላሉ ጥብቅ የጥራት ቁጥጥር ላላቸው ለውጭ ገበያ ይቀርባሉ።በአንፃሩ ከቻይና ሌሎች እንደ አልባሳት እና ጫማ የመሳሰሉ እቃዎች ወደ ኢትዮጵያ በብዛት ይገባሉ። ባንድ በኩል ተጠቃሚዎች ሲያማርሩ በሌላ በኩል አምራቾች ቻይና ገበያ እንደተሻማቻቸው ይናገራሉ። አሌክሳንደር ግን ይህ ጥሩ አጋጣሚ ይዞ ሊመጣ ሁሉ ይችላል ይላል። እንዴት? ማብራሪያ አለው። ከዚህም በተረፈ ከቻይና ጋር ያለውን የእውቀት ሽግግር በተመለከተ በዛሬው የከኢኮኖሚው ዓለም ርዕሳችን አንስተናል። ሁሉንም ከድምፅ ዘገባው ያገኛሉ።

ልደት አበበ

ሂሩት መለሰ