የተባባሰው የሴቶች ጥቃት
ማክሰኞ፣ ጥቅምት 1 2015
የ17 ዓመትዋ አዳጊ ወጣት ከሳምንት በፊት በጎረቤትዋ ወይም እንደሚባለው በእናትዋ ፍቅረኛ በስለት ተወግታ ህይወትዋን ማጣትዋ የተነገረው «አዳናዊት» ወላጅ አባት የሆኑት አቶ ይሄይስ ሸዋዬ «ሕጉ ይታወቃል ትልቁ ቅጣት ዕድሜ ይፍታህ ነው እስር ቤት ቁጭ ብለህ ተቀለብ ነው ይህ ደሞ ከልጃችን ህይወት አንፃር ካሳለፈችው ነገር አንፃር ማሾፍ ነው የሚሆነው» ያሉት
የ12 ተኛ ክፍል ተማሪ የነበረችውን «አዳናዊት»ን በስለት ወግቶ ለህልፈተ ህይወት ዳርጓል ተብሎ በመጠርጠሩ በፖሊስ ቁጥጥር እንዳለ የሚገለጸው ግለሰብ አቶ ሚካኤል ሽመልስ ይባላል። አዳጊ ወጣትዋን ከ10 ዓመት ዕድሜዋ ጀምሮ በተለያዩ ጊዜያት አስገድዶ ይደፍራት እንደነበር፤ የጥቃቱ ሰለባ የሆነችው ሟችም ከወላጅ እና ትዋ ጋር በመሆን ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሄዳ ፍትህ ለማግኘት ቃልዋን መስጠቷ ተሰምቷል። ፖሊስ ቃልዋን ተቀብሎ የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ በማውጣት ተጠርጣሪውን ያፈላልጋል። ሆኖም ግን ተጠርጣሪው ከሳሽ ላይ ጉዳት ያደርስባታል በሚል ጥበቃ ወይንም ከለላ እንዳላደረገላት ነው የተነገረው። በዚህ መሀልም በፖሊስ እየተፈለገ እንደሆነ ያወቀው ተጠርጣሪ መስከረም 19 ቀን 2015 ከቀኑ ስድስት ሰዓት ላይ የጥቃቱ ሰለባ አገር ሰላም ብላ ከእናትዋ ጋር በመኖሪያ ቤቷ በተቀመጠችበት ደርሶ በስለት ሰባት ቦታ ወግቶ ለማምለጥ ሲሞክር በፖሊስ ቁጥጥር ስር ይውላል።
ወላጅ አባት የ12ተኛ ክፍል ተማሪ የነበረችውን ልጃቸው ሲገልፁ ወላጅ አባት «አዳናዊት ምንብዬ ልንገርሽ የዋህ ቆንጆ ልጅ ታዛዥ ሰው አክባሪ እግዚአብሔርን የምትፈራ ነበረች» ይላሉ።
አባት በሟች ልጃቸውአዳናዊት ላይ ይደርስ ስለነበረው አካላዊም ሆነ ስነልቡናዊ ጉዳት ከመሞትዋ በፊት ምንም እንደማያውቁ ሁሉንም የሰሙት ልጃቸው ከሞተች በኋላ እንደሆነ ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል
«እኔ የሰማሁት የሞተች ዕለት ነው። የእናትዋ የፍቅር ጓደኛም ስለነበረ ምንም አላውቅም ፤ፖሊስ ጣቢያ ሄደው ስለማመልከታቸው እራሱ ምንም አላውቅም»። ይላሉ
አዶናይን እንደ ምሳሌ አነሳን እንጂ በየግዜው በቁጥር በርካታ እህቶቻችን ዛሬም በቅርብ ቤተሰብ ፣በጎረቤት እንዲሁም በማይታወቅ ሰው ጥቃት እንደሚደርስባቸው የተለያዩ መረጃዎችን ያሰባሰቡ አካላት ይናገራሉ። ነገር ግን ሁሉም ደፍረው ጉዳያቸውን በመያዝ ወደ ሕግ አይሄዱም። ለዚህም የተለያዩ ምክንያቶች በዋናነት ይጠቀሳሉ፤ አንድም ያሉበትን ማኅበረሰብ ፍራቻ፣ መገለል ብሎም የጣት መጠቋቆሚያ እንዳይሆኑ በመስጋት፤ አንድም ሕጉን ባለመተማመን የጥቃት ሰለባዎች ጉዳያቸው አደባባይ እንዲወጣ አለመፈለጋቸው ነው የሚነገረው። ህይወት አበበ በሴቶች ጥቃት ላይ ትኩረት አርጎ የሚሠራው ሴታዊት የተባለ ፆታን መሰረት ያደረገው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት አባል እንዲሁም ለሴቶች የመብት እኩልነት የምትሟገት ወጣት ናት። የሴቶች መብት መከበር ጉዳይ የሕግን ጨምሮ ብዙ ችግር አለ ትላለች።
«የሕግ ችግር አለ እንዲሁም ፖሊስ የፀጥታ ኃይሎች ላይም ላይ ፍተኛ ችግር ሊከሱ ሄደው ምስክር አምጡ ይባላል ምስክር በሌለው ጉዳይ ላይ ፤ይህ የአሰራር ችግር ነው። ሌላው ተጠቂዎችም ሆኑቤተሰቦች ይፈራልሉ እንደዚ የሚባል ሰው ነው ጥቃት ያደረሰብኝ ብሎ ለማውራት ፍርሀት አለባቸው ስትል ሌላዋ የሴቶች መብት እና እኩልነት የምትከራከረው ቤተልሄም አካለወርቅም በሀሳዋ ትስማማለች መርማሪዎች ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸው ሰዎችን እንዴት አድርገው ነው ቃል መውሰድ ያለባቸው ለሚለው ስልጠናዎች ቢኖሩም በቂ አይደለም አሁንም ተገደሽ ተደፍረሽ ስትሄጂ ምን ለብሰሽ ነበር ድንግል ነበርሽ ወይ ጠጥተሽ ነበር ወይ ለምን እዛ ሄድሽ ተብሎ ተበዳይ ላይ ነው ፖሊስ ምርመራ የሚያደርገው ትላለች።
በሴቶች እና በሕጻናት ላይ ለሚደርስ እንዲህ ላለው ጾታዊ ጥቃት እና ጉዳት በዋናነት የሕጉ መላላት እና ተፈፃሚነቱ እንደመነሻ ተደርጎ ይወሰዳል። ሕጉ ድርጊቱ እንዲቆም ወይንም እንዲቀንስ አለማድረጉ ብዙዎችንም ያስማማል። የሕግ አፈጻጸሙ ላይ ችግር እንዳለ ይሰማኛል የምትለው ህይወት
ድምፅ ሂወት አበበ ለሴቶች መብት እኩልነት የምትከራከር ። «የሕግ ፍፃሜ ላይ ችግር አለ» ነገር ግን ቅድም እንዳልኩት « ከፖሊስ ጀምሮ አካሄዱ ላይ ፍርድ ቤት እስከሚኬድበት ድረስ ችግሮች አሉ ስለዚህ ለበዳዩች በቂ ከለላ ይኖራቸዋል ማለት በጣም ከባድ ነው»። ብላለች
የሴቶች መብትእና እኩልነት ተሟጋች ቤተልሄም መንግሥት በሴቶች እና በሕጻናት ላይ ለሚደርስ ጥቃት ከባድ ከሆኑት ነገሮች ውስጥ አንድ ሕጉን ማስፈፀም ነው ትላለች።
«በየቀኑ የሚገደሉ ሴቶች እንደምትሰሚው ነው ብዛታችን ህዝቡ አንድ ላይ ተንቀሳቅሶ መንግሥት በሴቶች እና በሕጻናት ላይ ያለውን የህግ ስርአቶች እንዲፈትሽልና እንዲከልስልን አሁን እየተንቀሳቀስን ነው ያለነው ምክንያቱም ከባድ የሆነው ሕጉን ማስፈፀም የተፃፉትን እንኩዋን መተግበር በጣም ከባድ የሆነበት ሁኔታ ነው ያለው »
አንዲት ሴት ጥቃት ደርሶብኛል ብላ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ስትሄድ ለተበዳይዋ በቂ የሕግ ከለላ ማድረግ የፖሊስ ድርሻ እንደሆነ ይታመናል። ምክንያቱ ተጠርጣሪው በሕግ ቁጥጥር ስር ባለመዋሉ ጥቃት ያደርሳል ተብሎ ስለሚታሰብ።
በl17 አመትዋ ህይወትዋን ያጣችው የ«አዳናዊት» ወላጅ አባትም አቶ ይሄይስ ሕጉ ክፍተት አለበት ከሚያምኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ውስጥ ናቸው ። ልጃቸው ፖሊስ ጣቢያ ሄዳ ብታመለክትም ከለላ ሳይደረግላት ቀናት ቆይታ ፖሊስ ተጠርጣሪውን ለመያዝ በመጣበት ቀን በሰአታት ልዩነት ልጃቸው እንደተገደለች ይናገራሉ ልጄ ካሳለፈችው ነገር ምንም ፍርድ ቢሰጥ ደስተኛ እንደማያደርጋቸው ይናገራሉ።«ፖሊሶቹ ለመያዝ መተው አመለጣቸው ከቤት ከዛ ተመልሶ 6 ሰአት ላይ ነው የገደላት ። የኢትዮጵያን ሕግ ታውቂዋለሽ ከልጃችን ህይወት አንፃር ካሳለፈችው ነገር አንጻር ማሾፍ መቀለድ ነው የሚሆነው ። እየተደጋገመ የመጣው በሕጉ ክፍተት ስለሆነ ይሄን ያህል ልባችንን የሚሞላ ፍትህ ይመጣል ብለን አንገምትም» ብለዋል ።
በተደጋጋሚ በአሰቃቂ ሁኔታ እየተፈጸመ ያለው የሴት ልጅ ጥቃትን ማስቆም ለምን አልተቻለም ስንል የሕግ ባለሙያዋን ሀና ላሌን ጠይቀን ነበር ።
«ሙሉ ለሙሉ በሕጉ ክፍተት ብቻ ሳይሆን በአፈፃጸም ክፍተቱ ተጨማሪ ነው በርግጥ ክፍተቶች ሊኖሩ ይችላሉ ከሱም በላይ አሁን ላይ ግን እያየን ያለነው ያፈጻፀም ችግር ነው ሕጉ በሚፈቅደው መንገድ ውሳኔውን እየሰጡ ባለመሆናቸው ሌሎች ሰዎች እንዲፈፅሙ እያነሳሳ ነው የሚል ሀሳብ አለኝ» ብላለች።
የሴት ልጅ ጥቃት ፈርጀ ብዙ እና የተለያየ ነው። ታዲያ ሙሉ ለሙሉ የሚፈጸመው ጥቃት ማስቆም ባይቻል እንኳን መቀነስ የሚቻልበት መንገድ ይኖር ይሆን? ለሕግ ባለሙያ ሃና ያቀረብኩት ሌላኛው ጥያቄ ነበር።
«በአፈፃፀም ላይ ስርአቱን የጠበቀ እና ትክክለኛ ፍርድ ቢሰጡ ሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች ይቀንሳሉ ብዬ አስባለው ። ከዚህ በተጨማሪ ኅብረተሰቡ እንደዚህ አይነት ጥቃቶች እንዳይፈፀሙ ድምጽ መሆን አለበት ኅብረተሰቡን ማስተማር እና እንዲነቃ መደረግ አለበት»
ጥቃቱ እየተባባሰየቀጠለው እና ወንጀሉ ሊቆም ያልቻለው በህጉ ክፍተት ስላለው ብቻ ሳይሆን የህጉን የምንተገብርበት ወይም ተግባራዊነት የምናደርግበት መንገድ ከሚጠበቅበት አንጻር እኩል ስላልሆነ ነው ያሉት የፍትህ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት እና ኮሚኒኬሽን ዳሬክተሮች ዳሬክተር አቶ አወል ሱልጣን ናቸው ሴት ልጅ ላይ ጥቃት የሚያፈርስ ሰው ላይ እስከ 25 አመት ፅኑ እስራት እንደሚያስቀጣም ይናገራሉ «በጣም ትልልቅ ቅጣት ከሚያስቀጡ ወንጀሎች መሀከል አስገድዶ መድፈር እና ጥጾታን መሰረት ያደረጉ ወንጀሎች አንድ ነው። እስከ 25 አመት ሊያስቀጣ የሚችል የወንጀል አይነት ነው ። በኢትዩጵያ ትልቅ ቦታ ተሰቶት የተሰራ የህግ ማእቀፍ ነው ያለው በኢትዩጵያ ህጉ እያንዳንዱን በytoce ላይ የሚደርስን ጥቃት ግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ የተሰራ የህግ ማእቀፍ ነው ። ስለዚ ሴቶች ላይ ቅጣቱ ሊባረከት የቻለውና ወንጀሉ ሊቆም ያልቻለው። የህጉ ክፍተት ስላለሳይሆን ህጉን የምንተገብርበት መንገድ ተግባራዊነቱን የምንተገብርበት መንገድ ከሚጠበቅበት አንጻር እኩል ስላልሆነ ነው ።»
አቶ አወል ማህበረሰቡ የሴት ልጅ ጥቃትን የኔ ጥቃት ነው ብሎ ማሰብ አለት ይላሉ
«በሴቶች ላይ የሚፈጠር ማንኛውም ጉዳይ የኔ ጉዳይ ነው የወንዱም የትልቁም የትንሹም ጉዳይ ነው እህቴ እስካልተደፈረች ልጄ እስካልተደፈረች አያገባኝም የሚል አመለካከት ከማህበረሰብ ውስጥ ወጥቶ እንዲጋለጥ ማድረግ የምንችልበት ሁኔታ ከተፈጠረ ሰዎች እንደዚ አይነት ጉዳዩችን ከመፈጸም እየተቆጠቡ ይመጣሉ ። የወጣው ህግ አፈፃፀሙ ላይ የተወሰኑ ክፍተቶች አሉበት እነዚህ ክፍተቶች በጥናት የሚለዩ ሆነው ግን ህዝቡም የሀይማኖት አባቶችም ቤተሰብም እንዲሁም ትምህርት ቤትም ሁሉም የሚወስደው የራሱ ሚና ይኖራል ብዬ አስባለው »
ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመርያዋ ሴት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ሆነው ሲሾሙ የሴቶች ጥቃት ፈጽሞ ባይቆምም ይቀንሳል ብለው ተስፋ ያደረጉ ብዙዎች ነበሩ። ኢትዮጵያ የሚኒስትሮች ምክር ቤቷን 50 በመቶ በሴት ሚኒስትሮች ስትሞላ በዚህ በኩል የተሻለ ለውጥ ይመጣል የሚል ተስፋ የጣለው ጥቂት አልነበረም። ሆኖም ግን በሕጉ ላይም ሆነ በአፈጻጸሙ ላይ ለውጥ ሳይደረግ 50 በመቶዉን የሚሸፍኑት የምክር ቤት አባላት ሥራ ከጀመሩ ዓመት አለፋቸው። በሚያሳዝን ሁኔታ ዛሬም ግን በሴቶች ላይ የሚፈጸመው ዘርፈ ብዙ ጥቃት እስከ ሕይወት ማጥፋት ዘልቆ እንደቀጠለ ለመሆኑ ሰሞኑን በለጋ ዕድሜዋ የተቀጠፈችው «አዳናዊት» ጉዳይ ማሳያ ነው።
ማህሌት ፋሲል
ነጋሽ መሀመድ