ማስታወቂያ
አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ (AI)ን ተጠቅማ የፈጠራ ስራዋን በመከወን ላይ የምትገኘው አፍራህ ለምሳሌ ደረጃዎችን መውጣት የሚችል የአካል ጉዳተኛ ወንበር (ዊልቸር)ከመስራት ጀምሮ የሌሎች የበርካታ ፈጠራዎች ባለቤት ናት፡፡ ማየት ለተሳናቸው የሚረዳ ጽሁፍን ወደ ድምጽ መቀየር የሚችል ማንበቢያም ሰርታለች።
አፍራህ በፈጠራዋ በርካታ አገራዊ እና ዓለማቀፋዊ እውቅናዎችን አግኝታለች። “AI for good” በተሰኘው የአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ጉባኤም ለመሳተፍ ወደ ጄኔቫ እና ሌሎች የውጭ ሀገራት ከተሞች ተጉዛለች። የ2024 “AI scholar” ለመባልም በቅታለች፡፡ #ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች #GirlzOffMute
ዘጋቢ፡ ሱመያ ሣሙኤል
ቪዲዮ፡ ሥዩም ጌቱ