ማስታወቂያ
በዚህ መሰሉ ሀሳብ ላይ በነፃነት የሚናገሩ ወጣት ሴቶችን ማግኘት አስቸጋሪ የነበረ ቢሆንም በድሬደዋ የሚኖሩት ፂሆን እና ጓደኞቿ ፍቃደኛ ሆነው ዝምታቸውን ሰብረዋል። ወጣቶቹ አንዲት ሴት የወንድ ጓደኛ ልትይዝ የሚገባት "እድሜዋ ሃያ እና ከዚያ በላይ ሲሆናት ነው" ሲሉ ተመሳሳይ የሆነ የጋራ እሳቤያቸውን አካፍለውናል። ወጣቶቹ ለሰጡት ምላሽ በምክንያትነት ያነሱት" እድሜው ሴቷም ሆነ ወንዱ ክፉና ደጉን መለየት እና ማመዛዘን የሚችሉበት መሆኑን ነው"።
እድሜያቸው ከሀያ በታች ሆኖ የወንድ ጓደኛ የሚይዙ ወይም ከተቃራኒ ፃታ ጋር ግንኙነት የሚጀምሩ መኖራቸውን የጠቀሱት ዝምታ ሰባሪዎቹ በአቻ ተፅዕኖ ወደ መሰል ሁኔታ እንደሚገባ እና የጓደኛ ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ይናገራሉ። ከዚህም ሌላ ከልጆቻቸው ጋር ግልፅ ውይይት የሚያደርጉ ጥቂት ወላጆች ቢኖሩም በአብዛኛው የተለመደ አለመሆኑን ያነሱት ወጣቶቹ ወላጆች ለአቅመ አዳምና ሄዋን ከደረሱ ልጆቻቸው ጋር በቅርበት መወያያት ጠቃሚ ነው ብለዋል ።
#ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች #GirlzOffMute
ዘገባ: ሊዲያ መለስ
ቪዲዮ: መሳይ ተክሉ