ማስታወቂያ
በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ የረመዳን ፆም ወቅት ማጠናቀቂያ ላይ ከሚከበረው የኢድ አልፈጥር በኃላ ያሉ ስድስት ተጨማሪ የፆም ቀናት በኃላ በሀረሪ ክልል ማህበረሰብ ዘንድ በሚከበረው የሸዋል ኢድ በተለየ መልኩ በባህላዊ አልባሳት የተዋቡ የሀረሪ ወጣት ሴቶች ለበዓሉ ድምቀት ሆነው ያመሻሉ።
በጥንታዊቷ ሀረር ከተማ በሚገኘው የጀጎል ግንብ በሚካሄደው የበዓሉ የምሽት ድግስ ከተለመዱ ኩነቶች አንዱ መተጫጨት መሆኑን ወጣቶቹ ለዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች ዝግጅታችን ገልፀዋል። ምንም እንኳን እነሱ መሰል ታሪክ ባይኖራቸውም የቆየ እና የሚቀበሉት ባህል መሆኑንም አጫውተውናል።በጉጉት የሚጠብቁት የሸዋል ዒድ በዓል ደርሶ ደምቆ ለመታደም ዝግጅት እንደሚያደርጉም ወጣቶቹ ነግረውናል። የሀረሪ ወጣቶች ይህ ባህላቸው ይበልጥ እንዲያድግ እና ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ የበኩላቸውን እንደሚወጡም ጠቁመዋል። #ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች #GirlzOffMute
ዘገባ: ሊዲያ መለስ
ቪዲዮ: መሳይ ተክሉ