1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢራን በእስራኤል ላይ የሰነዘረችው ጥቃት አላማና ግቡ

ሰኞ፣ ሚያዝያ 7 2016

ኢራን ወደ እስራኤል ባሰወነጨፈቻቸው ከ300 በላይ ሚሳይሎችና ድሮኖች ጉዳት ማድስረሷንና ከሁሉም በላይ ግን እስራኤልን ስታሸበር ማደሯን የዓለም መገኛኛ ብዙኃን እስካሁንም እየዘገቡት ነው። እስራኤል በደማስቆ ቆንስላ በከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖቼ ላይ ግድያ በመፈፀሟ ጥቃቱ የአጸፋ እርምጃ ነዉ ስትል አላማዋን እንዳሳክች ኢራን አስታውቃለች።

https://p.dw.com/p/4enDX
ከኢራን የዘነበዉ የሮኬት እና የድሮን ጥቃት
ከኢራን የዘነበዉ የሮኬት እና የድሮን ጥቃትምስል Mohammad Hamad/picture alliance/Anadolu

ኢራን በእስራኤል ላይ የሰነዘረችው ጥቃት አላማና ግቡ

ኢራን በኢስራኤል ላይ የሰነዘረችው  ጥቃት አላማና ግቡ 

ኢራን ባለፈው ቅዳሜ ለዕሁድ ሌሊት ወደ እስራኤል ባሰወነጨፈቻቸው ከ300 በላይ ሚሳይሎችና ድሮኖች ጉዳት ማድስረሷንና  ከሁሉም በላይ ግን እስራኤልን ስታሸበር ማደሯን የዓለም መገኛኛ ብዙኃን እስካሁንም እየዘገቡት ነው። ኢራን ይህን እርምጃ የወሰደችው ኢስራኤል እ.እ ሚያዚያ አንድ ቀን በደማስቆስ የኢራን ቆንስላ ውስጥ በከፍተኛ ወታደርዊ መኮንኖቿ ላይ  ፈጽማዋለች ለምትለው  ግድያ  የአጸፋ እርምጃ እንደሆነ በመግለጽ አላማዋን እንዳሳክች  አስታውቃለች። እስራኤል በበኩሏ የኢራን እርምጃ  በእስራኤል ህልውና ላይ የተቃጣ ጥቃት መሆኑን በመግለጽ የአጸፋ እርምጃ መውሰዷ እንደማይቀር ገልጻለች። ከፍተኛ ጉዳት እንዲያደርሱ የተተኮሱት ሚሳይኖችና ድሮኖች ግን 99 ከመቶ የሚሆኑት በአየር ላይ እንዳሉ እንዲከሽፉ በመደረጉ የኢራን አላማ እንዳልተሳክ የገለጸችው እስራሬል፤ የዓለማቀፉ ማህብረሰብ የበኩሉን እርምጃ በኢራን ላይ እንዲወስድም ጠይቃለች።

የኢራን ጥቃት የፍጠረው አሳሳቢነትና የዓለም መሪዎች ማሳሰቢያ

ዓለምን ቀውስ ውስጥ ካስገባው የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት ሳይወጣ፤ እስራኤል በጋዛ ላይ እየፈጸመችው ባለው ጥቃት ሌላ መጠነ ሰፊ ጦርነት በአካባቢው እንዳይከፈት ስጋት ባየለበት ወቅት  ኢራን የሰነዘረችው ጥቃት ስጋቱን እውን ያደረገው ያህል የእለም መሪዎችን ሲያስጨንቅ ታይቷል።

ፕሬዝዳንት ባይደንና የአውሮፓ መሪዎች  በየግላቸውም በቡድን 7 የባለጸጋዎቹ ስብስባቸውም ኢራንን አጥብቀው አውግዘው፤ ግን ግጭቱ እንዳይሰፋና እንዳይባባስ ሁሉንም አሳስበዋል።የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አስቸኳይ ስብሰባም ለነገ  እንደተጠራ ታውቋል። የመንግስታቱ ድርጅት የጸጥታው ምክርቤት ትናንት በዚሁ ጉዳይ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰብባ፤ ከፍተኛ ክርክር የተደረገ ሲሆን፤  በዋናነት ግን ሁለቱም ወገኖች ግጭትን ከሚያባብሱና ከሚያሰፉ የአጸፋ እርምጃዎች እንዲቆጠቡ ማሳሰቢያዎች ተሰቶበታል። የመንግስታቱ  ድርጅት ዋና ጸሀፊ  አንቶኒዮ ጉቴሬሽ ለምክርቤቱ ባሰሙት ንግግር፤  ሊፈጠር የሚችለውን አውዳሚ ጦርነት ለማስቀረት ሁሉም የበኩሉን እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፤ “ የመካከለኛው ምስራቅ አፋፍ ላይ ነው ያለው። የአካባቢው ህዝብ ሌላ አውድሚ ጦርነት እየመጣበት ነው። ይህን ለማስቀረት ግዜው አሁን ነው” በማለት ሁሉም ወገኖች ሁኔታዎችን ከማባባስ እንዲቆጠቡ አጥብቀው አሳስበዋል።

በኢራን ጉዳይ ላይ የመከረዉ የፀጥታዉ ምክር ቤት
በኢራን ጉዳይ ላይ የመከረዉ የፀጥታዉ ምክር ቤት ምስል Fatih Aktas/Anadolu/picture alliance

የኢራንና እስራኤል ተወካዮች በመንግስታቱ ድርጅት የጸጥታው ምክርቤት

በስብሰባው የእስራኤል ተወካይ ሚስተር ጊላድ ኤርዳን፤ ኤራን የሰንዘረችው ጥቃት እስራኤል ቀርቶ  አለም የሚይወግዘው መሆኑን በመግለጽ እስራኤል እራሷን የመካልከል እርምጃዋን እንደምትቀጥል ዓስታወዋል። የኢራኑ ተወካይ ሚስተር አሚር ሰይድ ኢርቫኒ በበኩላቸው ኢስራኤል ፈጸመዋለች ያሉትን የደማስቆሱን ግድያ የጸጥታጣው ምክርቤት ባለማውገዙና ሀላፊነቱን ባለመወጣቱ፤ ኢራን እራሷን ከመከላከል ውጭ ሌላ አማራጭ የሌላት መሆኑን  በመግለጽ በእስራኤል ላይ የተወሰደው እርምጃ እራስን የመካላከል እርምጃ መሆኑን አስገንዝበዋል “ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ኢሳላማዊት ሪፑብሊክ ኢራን በአለማቀፍ ህግ መሰረት እራሷን የመካልከል መብቷን ከማስከበር ውጭ ሌላ አማራች የላትም” በማለት ጥቃቱ እራስን ለመካልከል ተገደው የገቡበት  እንደሆነ ገልጸዋል።
በዚሁ ስብሰባ የአሚሪካ ቻይናና ሩሲያ ተወካዮች አስተያየቶችም ተስተጋብተዋል። የአሜርካው ተወካይ ኢራንን  ያወገዙ ሲሆን፤ የሩሲያው ተወካይ ግን  የጸጥታጣውን ምክርቤት ባለፈው ግዜ የኢራን ወታደሮች በደማስቆስ ሲገደሉ ድምጹን ሳያሰማ አሁን መጯጩሁ አድርባየነትና መርሀ አልባነት ነው ሲሉ ምክርቤቱን ወርፈዋል። ባጠቃላይ ግን ሁሉም፤ ሁለቱም ወገኖች ከተጨማሪ የሀይል እርምጃ እንዲታቀቡ በበማሳሰብ የእካባቢው ችግር ምንጩ ግን የፍስልስጤም ጥያቄና በጋዛ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ መሆኑን በበስብሰብው በሰፊው ተወስቷል።

የኢራንን ጥቃት ተከትሎ እስራኤልን በመደገፍ በበርሊን አደባባይ የተካሄደ ሰልፍ
የኢራንን ጥቃት ተከትሎ እስራኤልን በመደገፍ በበርሊን አደባባይ የተካሄደ ሰልፍ ምስል DW

 

ጥቃቱ ለሁለቱም  ሊያስገኝ የሚችለው ፖለቲካዊና ወታደራዊ ፋይዳ

የቅዳሜውን እርምጃ ኢራን ወታደርዊ ብቃቷን ያሳየችበትና ለእራኤልና አጋሮቿ  የማስጠንቀቂያ መልክት ያስተላለፈችበት ነው የሚሉ ያሉ ሲሆን፤ ኢስራኤል ከሞላ ጎደል  ሁሉንም ሚሳይሎች ማክሸፍ መቻሏ ወታደራዊ አቅሟን አስመክሮላታል የሚሉና በጋዛ ምክኒያት ክወዳጆቿ ጋር የገባችበትን መቃቃርም ያለዘበላት ነው የሚሉም አሉ።  የቻታሀም ሀውስ ተመራመሪ የሆኑት ሚስተር ያሲ ሜኬልበርግ ይህንን ህሳብ ያጠንክራሉ፤ “ እንደሚመስለኝ በዚህ ሁኒታ እስራኤል ለግዜው የአጸፋ እርምጃ ከመውሰድ ልትታቀብ ትችላለች፤ምክኒያቱም ትናንት የታየው በጋዛ እያካሄደች ባለው ጦርነት ምክንያት ቅሬታ የነበራቸው አሜሪካና የአውሮፓ አገሮች  ከኢስራኤል ጎን ሲቆሙ ነው” በማለት  ይህ ለኢስራኤል ትልቅ የዲኢፕሎአማሲ ድል በመሆኑ እስራኤል ለግዜው የአጻፋ እርምጃ ክመውሰድ ልትቆጠብ እንደምትችል ያልቸውን ዕመንት ገልጸዋል።

 

ገበያው ንጉሤ

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ