1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አፍሪቃውያን ጀርመናውያን በጀርመን እውቅና ለማግኘት የሚያደርጉት ትግል

ረቡዕ፣ ነሐሴ 10 2015

በዘመኑ የተከበረና በጣም የታወቀ ሰው ለመሆን የበቃው ካሜሪናዊው ዲክ ልጆቹ ኤሪካና ዶሪስ የግል ትምሕርት ቤት ነው የሚማሩት። ናዚዎች ስልጣን ሲይዙ ለአፍሪቃውያን ጀርመናውያንን ባወጡት ዘረኛ መመሪያ ምክንያት ልጆቹ ከፍተኛ ትምሕርት መከታተል ተከለከሉ።ጎረቤቶቻቸው ቤተሰቡን መስደብ ጀመሩ።የአዳማኮ አያት የመማር ምኞታቸው ህልም ሆነ።

https://p.dw.com/p/4VD8h
ማዴንጋ እና ኤምሊ ልጆቻቸው ኤሪካና ዶሮትያ
ዲክ ሐምቡርግ የመጀመሪያውን ትዳር መስርተው አንዲት ሴት ልጅ ከወለዱ በኋላ ከሀምቡርግ ወደ ግዳንስክ ከተማ በመሄድ ኤምሊ የተባለች ጀርመናዊት አገቡ። ኤሪካና ዶሪስን ወለዱ ምስል Privatbesitz Reiprich

በጀርመን አፍሪቃውያን ጀርመናውያን እውቅና ለማግኘት የሚያደርጉት ትግል

አውሮጳና ጀርመን ዝግጅታችን ዛሬ የሚያስተዋውቃችሁ የመጀመሪያው የአፍሪቃውያን ጀርመናውያን ቤተሰብ የጀርመን ሕይወት የሚጀምረው ከዛሬ 130 ዓመት በፊት ነው።ያኔ ለትምህርት ወደ ጀርመን የመጡት አፍሪቃዊ እዚሁ ቤተሰብ መስረተው ያፈሩዋቸው ልጆች ዛሬ እዚሁ ጀርመን አምስተኛው ትውልድ ላይ ደርሰዋል። ይሁንና ቤተሰቡ አሁንም እንደ ሌሎች መሰል ጀርመናውያን በቆዳ ቀለሙ ምክንያት እንደተገለለ ነው። ጀርመን የመጡት የመጀመሪያው የቤተሰብ አባል የልጅ ልጅ ልጅ ልጅ ታሪካቸውን አጋርታለች። 
ናዲን ዎጅሲክ አፍሪቃውያን ጀርመናውያን በተወለዱባት፣ ባደጉባትና በሚኖሩባት በጀርመን ከ19ነ ኛው ክፍለ ዘመን የቅኝ ግዛት ወቅት አንስቶ እስካሁን መብቶቻቸውን ለማስከበር እየታገሉ ነው። ጥቁር ጀርመናውያን በናዚዎች ልዩ ልዩ በደሎች ተፈጽመውባቸዋል፤ የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ካበቃ በኋላም መኖራቸው እንዳይታወቅ ተደርጓል። አሁን ደግሞ በልበ ሙሉነት ያለፈ ታሪካቸውን እየተናገሩ ነው። የማዴንጎ ዲክ ቤተሰብ  ጀርመን ሲኖር ከ130 ዓመታት ተቆጥረዋል። ያም ሆኖ አሁንም እውቅና እንዲሰጣቸው እየታገሉ ነው። 
«ዋናው ጉዳይ ቅድም አያቴና አያቴ ለመብታቸው የሚሟገቱ ሰዎች ነበሩ።ይህም በሆነ መንገድ እንዲጠነክሩ አድርጓል።እርግጥ ነው እኔም እንድበረታ አድርጎኛል ። አሳዛኙ ነገር አሁንም እውቅና ለማግኘት፣ አድናቆት ለማትረፍና ከኅብረተሰቡ ጋር ተዋኅዶ ለመኖር እየሞከርን ነው።» 
ይህን የምትለው የጀርመን አፍሪቃውያንን ታሪክ ቆፍራ በማውጣት ላይ ያለችው የዲክ ቤተሰብ አራተኛው ትውልድ አቤና አዳማኮ ናት።ከወንድሟ ከሮይ ጋር በርሊን ከሚገኘው ከሾነንበርግ ቤተ መዘክር ጋር በመሰረቱት የቅርብ ትብብር የቤተሰቡን ታሪክ በዐውደ ርዕይ ለማቅረብ በቅተዋል። በአሁኑ ጊዜ ቴምፕልሆፍ-ሾነንበርግ ቤተ መዘክር የሚገኝ የጥቁር ጀርመናውያን ታሪክ እየሰፋ በመሄድ ላይ ነው። 
የአቤና አዳማኮ ቤተሰብ ጀርመን ሲኖር አሁን አምስተኛው ትውልድ ላይ ደርሷል። የቤተሰቡ የጀርመን ሕይወት ታሪክ የሚጀምረው በወጣትነቱ ከሀገሩ ካሜሩን ለጫማ ስሪነት የስራ ልምምድ ጀርመን በመጣው በማዴንጋ ዲክ ታሪክ ነው። አዳማኮ የቅድመ አያቷን አመጣጥ እንዲህ ትተርካለች። 
«ቅም አያቴ በ1891 ነጻ ሰው ሆኖ በቅኝ ትገዛ ከነበረችው ከካሜሩን መጀመሪያ ሀምበርግ መጣ ።አመጣጡ ምን መማር እንደሚችል ተመልክቶ፣ ከተማረ በኋላ ወደ ሀገሩ ለመመለስ ይመስለኛል። ሆኖም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ወደ ሀገሩ ለመመለስ ቢፈልግም የሚፈቀድለት ለጀርመን ፕሮፓጋንዳ የሚሰራ ከሆነ ብቻ መሄድ እንደሚፈቀድለት ቢነገረውም፣ ይህን ለማድረግ ግን ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል።»
ጥቁሮች በጀርመን እንደ ልዩ ፍጡር በሚቆጠሩበት በቅኝ ግዛት ዘመን ያኔ አስተማሪው ማዴንጋ ዲክን ለትርዒት እንደሚታይ እቃ መስኮት አጠገብ ነበር የሚያስቀምጡት። ዲክስ ከጊዜ በኋላ ልምምዱን አቋርጦ በንግድ ተሰማራ። ዲክ ሐምቡርግ የመጀመሪያውን ትዳር መስርተው አንዲት ሴት ልጅ ከወለዱ በኋላ ከሀምቡርግ ወደ ግዳንስክ ከተማ በመሄድ ኤምሊ የተባለች ጀርመናዊት አገባ። በዚያም የቅኝ ግዛት እቃዎች የሚሸጡበት ሱቅም ከፍቶም ነበር።«በተለይም ትምባሆ ሲጋራና የመሳሰሉትን መሸጥ ጀመረ።ይህ ደግሞ ከፍ ያለ ቦታ ከሚሰጠው የጀርመን ማኅበረሰብ ጋር እንዲቀላቀል ረዳው በጣም ተቀባይነት የነበረውና የሚደነቅም ነበር። ይህም የጀርመን ዜግነት በማግኘት የመጀመሪያው ካሜሩናዊ ለመሆን አብቅቶታል።»

የዲክ ቤተሰብ አራተኛው ትውልድ አቤና አዳማኮና ወንድሟ ከሮይ  በርሊን ከሚገኘው ከሾነንበርግ ቤተ መዘክር ጋር በመሰረቱት የቅርብ ትብብር የቤተሰቡን ታሪክ በዐውደ ርዕይ ለማቅረብ በቅተዋል።
የጀርመን አፍሪቃውያንን ታሪክ ቆፍራ በማውጣት ላይ ያለችው የዲክ ቤተሰብ አራተኛው ትውልድ አቤና አዳማኮ ናት።ከወንድሟ ከሮይ ጋር በርሊን ከሚገኘው ከሾነንበርግ ቤተ መዘክር ጋር በመሰረቱት የቅርብ ትብብር የቤተሰቡን ታሪክ በዐውደ ርዕይ ለማቅረብ በቅተዋል።ምስል Nadine Wojcik/DW


 በዘመኑ የተከበረና በጣም ታዋቂ ሰው ለመሆን የበቃው ዲክ በሁለተኛው ትዳሩ ያፈራቸው ኤሪካና ዶሪስ የግል ትምሕርት ቤት ነበር የሚማሩት። ከዛ በኋላ ናዚዎች ስልጣን ሲይዙ   ለአፍሪቃውያን ጀርመናውያንን ባወጡት ዘረኛ  መመሪያ ምክንያት ልጆቹ ከፍተኛ ትምሕርት መከታተል ተከለከሉ።ጎረቤቶቻቸው ቤተሰቡን መስደብ ጀመሩ፤ ልጆቹም ከሌሎች ጓደኞቻቸው ጋር መገናኘት ተከልክለው ነበር። ሐኪም የመሆን ምኞት የነበራቸው የአዳማኮ አያት ምኞታቸው ህልም ሆኖ ቀርቷል።የቅም አያቷ የማንዴንጋ ዲክ ንብረትም ተወርሶ ያበበውን ንግዳቸውን አጡ። ቀሪው ቤተሰብ ይህን ከባድ ወቅት ማለፍ ቢችልም ዲክ ግን ያለ እድሜያቸው በልብ ድካም ሕይወታቸው አለፈ። ትልቋ ልጃቸው ኤሪካ በሂሳብ ባለሞያነት ተቀጥራ ነገር ግን ሰው በማያያት ክፍል ውስጥ ነበር የምትሰራው ።ታናሽ እህቷ ዶሪስ ግን ከባድ ጊዜ ነበር ያሳለፈችው ለተወሰኑ ሳምንታት ግዳንስክ ውስጥ አንድ መርከብ ላይ በግዳጅ ስራ እንድትሰራ ተደርጋ ነበር። በግዳጅ ከመምከንም ለጥቂት ነበር የተረፈችው። ከዲክ ቤተሰብ ታሪክ አዳማኮንና ሌሎች ጀርመናውያን የቅድመ አያቷታሪክ ያስደንቀናል ትላለች ።ትውልደ አፍሪቃውያን ስለ ጀርመን ምርጫ 
«እኔንም ሆነ የጀርመን ማኅበረሰብን በጣም የሚያስገርመው ነገር ቢኖር ቅድመ አያቴ በ1990 ዎቹ መጀመሪያ ላይ ካሜሩናዊ ማግባቷ ነበር።ይህ በእርጥም ጠንካራና ኃይል ያላት ሴቶች እንደሆነች የሚያሳይ ነው።የቤተሰቡ አባል በሙሉ የጀርመን ዜግነታቸውን ሲነጠቁ የእርስዋ ግን አልተነካም ነበር። ካሜሩናዊ ካገባች በኋላ ግን የጀርመን ዜግነቷን አጣች።የዲክ ቤተሰብ በናዚዎች ፓስፖርታቸውን ከተቀሙ በኋላ በይፋ ሀገር አልባ ሆነው እዚሁ ጀርመን መኖራቸውን ቀጠሉ።ቤተሰቡ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የተቀማው ዜግነት በኋላ ተመልሶለታል። »
አዳማኮ እንዳለችው ያኔ ግን ቅድም አያቷ ሞተው ነበር። አያቷና እናቷ ግን ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ ነው ዜግነታቸው የተመሰላቸው።  የአዳማኮ አያት ኤሪካ ደግሞ በወቅቱ እጅግ ታዋቂ የነበረውን የፊልም ተዋናይ ሉዊስ ብሩዲን አገባች ። አንድ ልጅ ወልደው ወደ በርሊን ሄዱ። የፊልም ተዋናዩ ብሮዲም ካሜሩናዊ ነው። በቋሚነት ከሚሰሩ ጥቂት ጥቁር የፊልም ተዋናዮች አንዱ ነበር። ከ60 በላይ የሚሆኑ ፊልሞች ላይ ሰርቷል። ግን ጎላ ያለ ገጸባህርይ ተሰጥቶት አያውቅም።ሦስቱ ላይ ብቻ የመሪና የተናጋሪ ገፀ ባህርይ ተላብሶ ይጫወት ነበር። አቤና አዶማኮ ቅድም አያቷን በፊልም ነው የምታውቃቸው።

ዶሮትያ ሬልፒሽ ከጓደኞቿ ጋር
ኤሪካና ዶሪስ የግል ትምሕርት ቤት ነበር የሚማሩት። ከዛ በኋላ ናዚዎች ስልጣን ሲይዙ   ለአፍሪቃውያን ጀርመናውያንን ባወጡት ዘረኛ  መመሪያ ምክንያት ልጆቹ ከፍተኛ ትምሕርት መከታተል ተከለከሉ።ምስል Privatbesitz Reiprich

ብሮዲ በወቅቱ ለቅኝ ግዛት ፕሮ ፖጋንዳ ተብለው በሚሰሩ ፊልሞች ላይ ነበር የሚተውነው። ከ1933 እስከ 1945 በዘለቀው የናዚ ጀርመን አገዛዝ ይህን ከማድረግ ውጭ ሌላ አማራጭ አልነበረውም። እምቢ ካለ ከሙያው ይታገዳል ፤ወይም በሰዎች ማጎሪያ ጣቢያዎች ይታሰራል ትላለች የልጅ ልጁ አዶማኮ።ሁለቱን ልጆቻቸውም ከናዚ ዎች በደል ተርፈዋል። ከኤሪካና ከሉዊስ የተወለደችው ቤሪል ሶስተናዋ ትውልድ የአቤና አዳማኮ እናት ናት። የቤሪል እናት ከናዚ በቀደመው በቫይመር ሪፐብሊክ የተለያዩና ተጋሽ ማኅበረሰብ ውስጥ ነው የኖረችው። በሌላ በኩል ቤሪል ያደገችው ደግሞ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በተፈጠረው ክፍተት ውስጥ ነበር ። ከጦርነቱ በኋላ በተፈጠረው ክፍተት ራሷን እንዳትታይ ያደረገችው ቤሪል ጋናዊ አፍቅራ አገባች። የቤተሰቡን ታሪክ የምትነግረንን አቤናንና ሮይን ወለደች። አራተኛው ትውልድ ናቸው። አቤና እንደምትለው እናታቸው በተቻለ መጠን ራሳቸውን ደብቀው እንዲኖሩ ይጥሩ ነበር። አቤና አዳማኮ በልጅነቷ ጭምት የነበረች ቢሆንም ዛሬ ድምጽዋ ከፍ ብሎ ይሰማል። አዳማኮ ጀርመን የሚኖሩ ጥቁሮች እውቅና እንዲሰጣቸው ከሚንቀሳቀሰው ድርጅት መስራቾች አንዷናት። ድርጅቱ ራሳችንን የምናጠናክርበት እውቅና እንዲሰጠን የምንጠይቅበት ቦታ ሆኖልናል ትላለች። ጥቁሩ ማኅበረሰብም በአግባቡ ያልተሰነደውን ታሪኩንም በትምሕርት ቤት የሚሰጠውን  ታሪኩን ራሱ መጻፍ አለበትም ስትል ታሳስባለች። ከዩናይትድ ስቴትስ ወይም ከብሪታኒያ ጋር ሲነጻጸር ሁኔታው እጅግ ጨቅላ ነው ትላለች አዳማኮ ። በርካታ አፍሪቃውያን አሜሪካውያን በባርነት ተግዘው አሜሪካን የገቡ ዘር ማንዘሮቻቸውን ማንነት ከታሪክ ሰነድ ማግኘት ችለዋል።ታሪካቸው በኦስካር ተሸላሚው የስቲቭን ሽፒልበርግ ፊልም THE COULOR PURPLE ወይም የስቲቭ ማክዊንስ ! 12 YEARS OF SLAVE  ፊልም ተሰርቶላቸዋል። ጀርመን ግን እነዚህ የሉም። የናዚ አገዛዝ ሰላባ ለሆኑት ኤሪካ ዲክና ሉዊስ ብሮዲ በበርሊን መታሰቢያ አላቸው። የአዶማኮ አያት ኤሪካ የተሰጣቸውን  እውቅና ሳያዩ ነው ያረፉት። በ1999 በጎርጎሮሳዊው አቆጣጠር ነው የሞቱት። ለአፍሪቃውያን ጀርመናውያን መብቶች መከበር የምትታገለው አቤና አዶማኮ በእስካሁኑ እንቅስቃሴ ከዚህ በፊት ያልነበረ ለውጥ አይተናል የምትለው አዶማኮ ዓላማችንን ለማሳካት ወደፊት  ለብዙ ዓመታት መስራት ይኖርብናል ብላለች። የአፍሪቃውያን ወጣቶች ሕይወት በጀርመን
«በኔ እምነት ከ30 ዓመታት በላይ የመብት ትግል በኋላ ጥቁር ጀርመናውያን ወይም በጀርመን የሚገኙ ጥቁሮች እንደሌሎች ሊቆጠሩ አይችሉም።እየተደመጡ ነው።እንደ አፍሪቃዊ ጀርመናዊ ማኅበረሰብ እየታየን እየታወቅን ነው።ይህ በጣም አስፈላጊ ነው። ምክንያቱም ከዛ በፊት ግን አልታየንም ነበር።አሁን እየተደመጥንምነው። በምንጠየቅበት ጊዜ ሁሉ አንዳች ተጽእኖ ይኖረናል። ሆኖም ስራችን አላበቃም። እንደሚመስለኝ ሌላ 30 ፣40 ዓመት ሊቀጥል ይችላል። አናውቅም ፤ ሆኖም ባይደግፉንም ለኔ ትልቁ ነገር ከአሁን በኋላ ከኛ ውጭ ምንም ነገር ማድረግ አይችሉም፤እኛንም ሊረሱን አይችሉም።»
አሁን አዶማኮ የአንዲት ሴት ልጅ እናት ናት። አንቶንዮ አዶማኮ የአፍሪቃውያን ጀርመናውያን ቤተሰብ አምስተኛዋ ትውልድ ናት።  የ24 ዓመቷ አንቶንዮ ለንደን ውስጥ የምትሰራ አርቲስት ናት። የቤተሰቧን ታሪክም በፎቶግራፍ ስራዎቿ ታወጣለች። አዶማኮ ልጇን ከልጅነቷ አንስቶ አየፍሪቃውን ዳያስፖራዎች ስብሰባዎች ላይ ትወስዳታለች።አንቶንዮ በእድሜ ስትገፋ ግን ሌሎቹ ጥቁሮች በእለት ተእለት ህይወታቸውን እንደሚገልጹት እሷ ምንም ሲሰማት አላይም ትላለች እናቷ። ግዳንስክ የተወለዱት የአዶማኮ አያት ኤሪካ ያረፉት በርሊን ነው። የወላጆቻቸውን አገር ግን አላዩም አቤና አዶማኮ ግን ጋና ያሉትን የአባቷን ቤተሰቦች በየጊዜው ትጎበኛለች። በዚያ ቆይታዋም የአፍሪቃዊ ጀርመናዊ ኃይሏን ታጠናክራለች። 

የናዚ አገዛዝ ሰላባ ለሆኑት ኤሪካ ዲክና ሉዊስ ብሮዲ በበርሊን የተቀመጠላቸው መታሰቢያ
የናዚ አገዛዝ ሰላባ ለሆኑት ኤሪካ ዲክና ሉዊስ ብሮዲ በበርሊን መታሰቢያ አላቸው። የአዶማኮ አያት ኤሪካ የተሰጣቸውን  እውቅና ሳያዩ ነው ያረፉት። በ1999 በጎርጎሮሳዊው አቆጣጠር ነው የሞቱት። ምስል Fabian Sommer/dpa/picture alliance
ኤምሊ ዲክ ከልጆቿ ከኤሪካና ዶሮትያ እንዲሁም ጋር ከልጅ ልጆቿ ከቤሪል ማርዮን እና አናና ራይፕሪሽ
ቤሪል ጋናዊ አፍቅራ አገባች። የቤተሰቡን ታሪክ የምትነግረንን አቤናንና ሮይን ወለደች። አራተኛው ትውልድ ናቸው። አቤና እንደምትለው እናታቸው በተቻለ መጠን ራሳቸውን ደብቀው እንዲኖሩ ይጥሩ ነበር። አቤና አዳማኮ በልጅነቷ ጭምት የነበረች ቢሆንም ዛሬ ድምጽዋ ከፍ ብሎ ይሰማል። ምስል Privatbesitz Adomako

ኂሩት መለሰ 

አዜብ ታደሰ 

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ዘገባና ትንታኔ

ዘገባና ትንታኔ