1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ተጀምሯል

ቅዳሜ፣ የካቲት 9 2016

በመክፈቻ ሥነ ሥትዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የሕብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሕማት ሽብርተኝነት፣ ኢ- ሕገ መንግሥታዊ የመንግሥት ለውጦች እና ግጭቶች አሁንም የአሕጉሩ አሳሳቢ የፀጥታ ችግሮች ሆነው መቀጠላቸውን ገልፀዋል።

https://p.dw.com/p/4cWjS
Äthiopien | AU Gipfel in Addis Ababa
ምስል Solomon Muchie/DW

የአፍሪቃ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ አዲስ አበባ ውስጥ ተጀመረ

የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ ተጀምሯል

37ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ የካቲት 9 ቀን 2016 ዓ . ም ተጀምሯል።

በመክፈቻ ሥነ ሥትዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የሕብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሕማት ሽብርተኝነት፣ ኢ- ሕገ መንግሥታዊ የመንግሥት ለውጦች እና ግጭቶች አሁንም የአሕጉሩ አሳሳቢ የፀጥታ ችግሮች ሆነው መቀጠላቸውን ገልፀዋል።

በአሕጉሩ የትብብር እና የአፍሪካ አንድነት ስሜት እየተዳከመ ስለመሆኑም በንግግራቸው አንስተዋል።

የፍልስጤም ጉዳይ ጎልቶ የተደመጠበት የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ ሕብረቱ ከፍልስጤም ጎን እንደሚቆም ተገልጿል፣ ደቡብ አፍሪካ እስራኤልን በአለም አቀፍ ፍርድ ቤት መክሰሷም አድናቆት ተችሮታል።

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር በበኩላቸው አፍሪካውያን በልውጠት ላይ ባለው የዓለም ሥርዓት ላይ ምን አይነት ሚና ሊወጡ ይገባል የሚለው ጥያቄ ምላሽ እንደሚያሻው ገልፀዋል።

ሞሪታኒያ ሕብረቱን ስትመራ ከቆየችው ኮሞሮስ የሊቀ መንበርነት ሥፍራውን ተረክባለች።

የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እየተካሄደ
በመክፈቻ ሥነ ሥትዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የሕብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሕማት ሽብርተኝነት፣ ኢ- ሕገ መንግሥታዊ የመንግሥት ለውጦች እና ግጭቶች አሁንም የአሕጉሩ አሳሳቢ የፀጥታ ችግሮች ሆነው መቀጠላቸውን ገልፀዋል።ምስል Solomon Muchie/DW

የመሪዎቹ መወያያ አጀንዳዎች ምንድን ናቸው ?

100 ሚሊዮን አፍሪካዊያን ሕፃናት እና ታዳጊዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸው ቀደም ብሎ በተጀመረው በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች መደበኛ ጉባኤ የተገለፀበት አፍሪካ ሕብረቱ በዚሁ ምክንያት ለአሸባሪዎች ምልመላ ፣ ለሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር፣ ለጉልበት ብዝበዛ እና ለአደንዛዥ ዕፅ ተጋላጭ የሚሆኑ ሕፃናትን እና ታዳጊዎችን ወደ ትምህርት የመመለስን አጀንዳ ቀዳሚ አድርጎ ተወያይቷል። 

የሕብረቱ የዚህ ዓመት ዐቢይ የውይይት አጀንዳ ትምህርት ይሁን እንጂ እየተባባሰ የሚገኘው የአሕጉሩ የሰላምና ደህንነት እጦት፣ የሱዳን ግጭት ፣ የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ውጥረት 

የምእራብ አፍሪካ ሀገራት የመንግሥታት ግልበጣዎች አሳሳቢነት ይወያዩባቸዋል ተብለው የተያዙ ጉዳዮች ናቸው።

በጉባኤው ላይ እነማን ተገኙ ?

በአሜሪካ አፍሪካ ፣ በቻይና አፍሪካ ፣ በሩሲያ አፍሪካ፣ በሳውዲ አፍሪካ፣ በጣልያን አፍሪካ እና በሌሎችም ሀገሮች አፍሪካ ተብለው በሚዘጋጁ ጉባኤዎች ላይ እየተጠመዱ ያሉት የአህጉሪቱ መሪዎች በሕብረቱ በኩል ከፍልስጤም ጎን እንደሚቆሙ እና እስራኤልን ተጠያቂ ለማድረግ የተጀመረውን የደቡብ አፍሪካ እርምጃ አድንቀው ዛሬ በሕብረት እውቅና ሰጥተዋል።

ዛሬ አዲስ አበባ ላይ በተጀመረው 37 ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ የብራዚሉ ፕሬዝዳንት ሉላ ዳሲልቫ፣

የፓላስታይን ጠቅላይ ሚኒስትር ፣ የአረብ ሊግ ሊቀመንበር 

ተገኝተው ንግግር ያደረጉ ሲሆን ብራዚል ከአፍሪካ ጋር ያላትን ግንኙነት በላቀ ሁኔታ ለማሳደግ እንደምትጥር ተገልጿል፣ 

በጉባኤው ንግግር እንደሚያደርጉ አስቀድሞ ተገልጾ የነበሩት የተባበሩት መንግሥታ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ በጉባኤው አልተገኙም።

የፖን አፍሪካኒዝም ስሜት መቀዛቀዝ

የፖለቲካ አለመረጋጋት ፣ ድርቅና ድህነት ብሎም የፀጥታ ችግር አሁንም አፍሪካን አላራምድ ያለ ችግር መሆኑን የገለፁት የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ፣ ኢ - ሕገ መንግሥታዊ የመንግሥት ለውጦች መበራከት መሪዎቹ ያን የመመከት አቅም መልስ እንደሚያስፈልገው ጠቋሚ መሆኑን ገልፀዋል። በአሕጉሩ የትብብር፣  የአፍሪካ አንድነት እና የፓን አፍሪካን ስሜት እየተዳከመ ስለመምጣቱም መታዘባቸውን ገልፀዋል።

የሕብረቱ ጉባኤ አስተናጋጅ የሆነችው ኢትዮጵያ የውስጥ የትጥቅ ግጭት አሁንም ያልተለያት ሲሆን ሶማሊያ የሉዓላዊ ግዛቴ አካል ከምትላት ሶማሊላንድ ጋር  የመግባቢያ ስምምንነት መፈራረሟን ተከትሎ ከሶማሊያ ጋር ውጥረት ውስጥ ገብታለች። ዛሬ በመሪዎቹ ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አፍሪካዊያን በዓለም ሥርዓተ ትድድር ላይ ሊኖራቸው የሚገባው ሚና መልስ የሚያሻው መሆኑን ገልፀዋል።

የቀድሞ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት አባል ሃገራት መሪዎች
የሕብረቱ ጉባኤ አስተናጋጅ የሆነችው ኢትዮጵያ የውስጥ የትጥቅ ግጭት አሁንም ያልተለያት ሲሆን ሶማሊያ የሉዓላዊ ግዛቴ አካል ከምትላት ሶማሊላንድ ጋር  የመግባቢያ ስምምንነት መፈራረሟን ተከትሎ ከሶማሊያ ጋር ውጥረት ውስጥ ገብታለች።ምስል Solomon Muchie/DW

የአፍሪካ ሕብረት ችግር ፈቺነት - የተንታኞች ምልከታ

የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ በኢትዮጵያ እየተካሄደ መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት አሕጉራዊ ድርጅቱ በኢትዮጵያ ያለውን ግጭት ለማስቆም በቂ ጥረት እያደረገ ነውን? በሚል ከዶይቼ ቬለ ጥያቄ ቀርቦላቸው ምላሽ የሰጡት በዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ ዩኒቨርሲቲ አፍሪካ የታሪክ ፕሮፌሰር ፕሮፌሰር ማቻሪያ ሙኔን ጉዳዩ በሕብረቱ ጥንካሬ ላይ የሚወሰን መሆኑ ገልፀው ሕብረቱ የአባል ሀገራቱን ችግሮች በመፍታት ረገድ ችግር ያለበት መሆኑን ገልፀዋል።

ከዚህ በፊት ስለ አፍሪካ ሕብረት ጥንካሬ እና ኃላፊነት ትንታኔ የሰጡ ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የዓለም አቀፍ ሕግ እና ዲፕሎማሲ ተንታኝ ሕብረቱ እዚህ ግባ የሚባል ሥራ ከመስራት ይልቅ የተለጠጠ ዕቅድ በመያዝ የማሳካት አቅሙን የማያሳይ መሆኑን ጠቅሰው ነበር።

የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ ግጭቶች እየጨመሩ ነው። የሕብረቱ የመሪዎች ውይይት ነገም ይቀጥላል። ለመሰረታዊ የሰላምና ድህንነት ጉዳዮች መፍትሔ በማስቀመጥ ስብሰባው ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

የሕብረቱን ሊቀመንበር በየዓመቱ የሚመርጠው የአፍሪካ ሕብረት ሞሪታኒያ የዚህ ዓመት ሊቀመንበርነትቱን እንድትይዝ አድርጓል።

ሰለሞን ሙጬ

ታምራት ዲንሳ