ማስታወቂያ
እ.ጎ.አ. ጥቅምት 29 ቀን 2020 በጾታ እኩልነት ፣ ድህነትን ማጥፋት እና ማህበራዊ ደህንነት ላይ የሚሰራው የናሚቢያ ሚኒስቴር (MGEPESW) ይፋ ያደረገው ጥናት እንደሚያሳየው በሀገሪቱ ካሉ ልጃገረዶች 18.4% ያህሉ ያለ እድሜያቸው ይዳራሉ። ወንዶች ደግሞ 4.1 % ያህል ናቸው። ጥናቱ እንደሚጠቁመውም በአገሪቱ ውስጥ ያሉ በርካታ ታዳጊ ሴቶች ለመጀመሪያ ጊዜ ከ12 እስከ 17 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ይፈጽማሉ። በልጅነት ከተዳሩ ልጃገረዶች በእድሜ ትንሽ የሚባሉት በ11 ዓመታቸው የተዳሩ ናቸው። ድህነት፣ ባህልና የትምህርት እድል አለማግኘት ብዙውን ጊዜ የልጅ ጋብቻ እንዲፈፀም ዋና ምክንያቶች ናቸው። #77ከመቶው