ትራምፕ ለ 20 ደቂቃ እስር ላይ ነበሩ
ዓርብ፣ ነሐሴ 19 2015ማስታወቂያ
የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ምፕ የ 2020 ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤትን ለመቀልበስ አሲረዋል በሚል ክስ በአትላንታ ጆርጂያ በሚገኘው እስር ለጥቂት ደቂቃዎች ተይዘዉ በዋስ ተለቀቁ። የዶናልድ ትራምፕ 4ኛ ክስ ምን ለየት ያደርገዋል? ትራምፕ ትናንት ሃሙስ ለ 20 ደቂቃዎች ከቆዩበት እስር የተለቀቁት የ 200 ሺህ ዶላር የገንዘብ ዋስ ከፍለዉ ነዉ። ትራምፕ በእስር ቤት በቆዩባቸዉ ደቂቃዎች በሃገሪቱ የእስር ቤት ደንብ፤ ለፖሊስ የጣት አሻራ ሰጥተዋል፤ ፎቶግራፍም ተነስተዋል። ትራምፕ ከጆርጅያዉ ከእስር ቤቱ ቆይታ በኋላ ”ሐሰተኛ ፍትህ” ሲሉ ነዉ የተናገሩት። ይህ “የምርጫ ጣልቃ ገብነት ነው” “ሃቀኝነት የጎደለው ነው ብለን የምናስበውን ምርጫ” የመቃወም ሙሉ መብት አለን ሲሉም ትራምፕ አክለዋል። የዶናልድ ትራምፕ ክስ
ትራምፕ በአምስት ወራቶች ዉስጥ በተለያዩ ወንጀሎች ተጠርጥረዉ በቁጥጥር ሲዉሉ የትናንትናዉ ለአራተኛ ጊዜ መሆኑ ነዉ። ትራምፕ ለመጀመርያ ጊዜ ፎቶግራፍ እንዲነሱ በተደረገበት የእስር ቆይታቸዉ በርካታ ደጋፊዎቻቸዉ ከእስር ቤቱ ፊት ለፊት ሁኔታዉን ለመከታተል ተሰብስበዉ ቆመዉ ታይተዋል። ትራምፕ እስር ቤት የተነሱት ፎቶ በዓለም ዙርያ ማህበራዊ ሚዲያዎች ትኩረትን ስቦ ነዉ የዋለዉ።
አዜብ ታደሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ