1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን በታጣቂዎች ይፈፀማል የተባለው ጥቃት

ማክሰኞ፣ ጥር 24 2014

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ታጣቂዎች በተቆጣጠሩአቸው አከባቢዎች መደበኛ ኑሮ መምራት አዳጋች መሆኑን ነዋሪዎች አመለከቱ፡፡ አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡት በዞኑ የገላና ወረዳ ነዋሪዎች በየጊዜው በታጣቂዎች ይፈጸማል ባሉት ግድያ እና የንብረት ውድመት አስከፊ ያሉት ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን አማረዋል፡፡

https://p.dw.com/p/46NQJ
Äthiopien | Wahlen | Oromia

በስፍራዉ ላይ ያሉ የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ለጥበቃዉ በቂ አይደሉም

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ታጣቂዎች በተቆጣጠሩአቸው አከባቢዎች መደበኛ ኑሮ መምራት አዳጋች መሆኑን ነዋሪዎች አመለከቱ፡፡ አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡት በዞኑ የገላና ወረዳ ነዋሪዎች በየጊዜው በታጣቂዎች ይፈጸማል ባሉት ግድያ እና የንብረት ውድመት አስከፊ ያሉት ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን አማረዋል፡፡ የአከባቢው ባለስልጣናት በፊናቸው አሁን ላይ በስፍራዎቹ ያሉት የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች በቂ ባለመሆናቸው በየመዋቅራዊ ደረጃው ጥያቄ ቀርቦ ምላሽ እየተጠበቀ ነው ብለዋል፡፡

ስዩም ጌቱ

አዜብ ታደሰ 

ኂሩት መለሰ