በሰላም ስምምነቱ ላይ ጥላ ያጠላዉ ጾታዊ ጥቃት
ዓርብ፣ ነሐሴ 19 2015የመቀለ ከተማ ነዋሪ የሆኑት እና የወሲብ ጥቃት የተፈፀመባቸዉን ሴቶች የሚያማክሩት የማኅበራዊ ጉዳይ ሠራተኛዋ ብርሃን ገብረ ክርስቶስ ስለሰበሰቧቸዉ መረጃዎች ሲናገሩ በሃዘን እና በሰለለ ድምፅ ነዉ። "በትግራይ ክልል ለሁለት ዓመታት በተካሄደው የእርስ በርስ ጦርነት በርካታ ሴቶችና ልጃገረዶች በጭካኔ ተደፍረዋል፤ ያሉበት ሁኔታ በጣም አሳሳቢ ነው" ሲሉ ብርሃን ገልፀዋል።ጾታዊ ጥቃት እና ማህበራዊ ችግር ያብቃ ፤ የትግራይ ሴቶች
«የትግራይ ሴቶች በጾታ ጥቃት ምክንያት እየደረሰባቸው ያለው ሁኔታ በጣም አሳሳቢ ነው ። የጥቃቱ ሰለቦቹ በአሁኑ ወቅት ብዙ ፈታኝ ሁኔታዎች እየተጋፈጡ ነዉ። በቂ የሕክምና ርዳታ አለማግኘታቸው ደግሞ ቀደም ሲል የደረሰባቸውን ከባድ ሥነ ልቦናዊ ቀውስ ከማባባስ ውጪ የፈየደላቸዉ ነገር የለም። በሁሉ ቦታ ሆስፒታል ባለመኖሩ አሁንም በቂ ሕክምና የለም። በሕይወት የተረፉት ሰዎች ከሁለት ሦስት ዓመታት በኋላ መድሃኒት ለማግኘት ወደ ትግራይ ክልል ዋና ከተማዋ መቀሌ ሆስፒታል በመምጣታቸዉ ሆስፒታሉ በጣም ተጨናንቆዋል።" በጦርነት ወቅት ለጥቃት የሚዳረገው የሴቶች ሕይወት
ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም በኢትዮጵያ መንግስት እና በትግራይ ህዝብ ነጻ አውጭ ግንባር (ህወሓት) መካከል ከተፈፀመዉ የሰላም ስምምነት በኋላ እንኳን አስገድዶ መድፈር እንደ የጦር መሣሪያ ሆኖ እንደሚውል ሁለት በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኙ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ሰሞኑን ይፋ ባደረጉት ዘገባ አሳዉቀዋል።
የርዳታ ድርጅቶች የሰብዓዊ መብት ጉዳይ ሀኪሞች እና የአፍሪቃ ቀንድ የሕግና ተጠያቂነት ቢሮ ጸሐፍቶች ይፋ ባደረጉት መሰረት፤ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸመውን የወሲብ ጥቃት በተመለከት በትግራይ ክልል ከሚገኙ የጤና ተቋማት በተመረጡ 304 የህክምና መዝገቦች ላይ የተመሰረተ መረጃ መሆኑ ተመልክቷል። መረጃዉን ይፋ ያደረጉት ጸሐፍት እንደገለፁት የህክምና መዝገቦችን መሰረት በማድረግ በግጭት ሰዓት የተፈፀመ ወሲብ ጥቃት በተደራጀ መልኩ ሲሰነድ እና ይፋ ሲሆን ይጅ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ነዉ።ፅናት፤ የጾታዊ ጥቃት ሰለባዋ አዳጊ ወጣት
በርካታ የተደፈሩ ሴቶች ወደ ሆስፒታል እየመጡ ነዉ ስትል የማኅበራዊ ጉዳይ ባለሞያዋ ብርሃን ገብረ ክርስቶስ የተናገረችዉን የመቀሌ ከተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ዳይሬክተር ፊልሞን መስፍን፤ ለዶቼ ቬለ አረጋግጠዋል። ፊልሞን ወደ ሆስፒታሉ እየመጡ ያሉት ሴቶች እጅግ በርካታ መሆናቸዉን እና ከሰላም ስምምነቱ በፊት በአስገድዶ መደፈር ጥቃት ሰለባ የሆኑ መሆኑንም አክለዋል። በጦርነቱ ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸው የሚደገፉበት የእርዳታ ስምምነት
« የጥቃቱ ሰለቦቹ ወደ ጤና ተቋማት ለመምጣት የሚስችላቸዉ ምንም አይነት መንገድ አልነበራቸዉም። ሁሉም ከሰላም ስምምነቱ በፊት ጥቃት የደረሰባቸዉ ናቸዉ። አሁን ግን ብዙ የጥቃቱን ሰለቦች እየተቀበልን ነዉ። ምክንያቱም ከቅርብ ወራት ወዲህ የጾታ ጥቃት ግንዛቤን ለማሳደግ ብዙ በመሠራቱ፤ ብዙ የተደፈሩ ሴቶች ወደ ሆስፒታል እየመጡ ነዉ። ሆስፒታል ከመጡት መካከል አንዳንዶቹ ወልደዋል፤ አንዳንዶቻቸው ፅንሱ እንዲወርድላቸዉ የሚጠይቁ ነፍሰ ጡሮች ናቸዉ። አንዳንዶቹ ደግሞ በኤች አይ ቪ ኤድስ ተሐዋሲ የተጠቁ ናቸው። »የአስገድዶ መድፈር ወንጀል በኢትዮጵያ
በግዕዝ ስያሜዉ 'መቃኒት' ወይም 'የስቃይ መሣርያ' የሚል ስያሜን የያዘዉ እና በትግራይ ሴቶች ላይ የተፈፀመዉን የፆታ ጥቃት የሚተርከዉ አዲስ መጽሐፍ ከቀናቶች በፊት ለአንባብያን የቀረበ ሲሆን፤ የታሪኩ ጸሐፍት አንዷ የሆኑት የማኅበራዊ ጉዳይ ሠራተኛዋ ብርሃን ገብረ ክርስቶስ፤ እንደተናገሩት በጦርነቱ ወቅት በትግራይ የተፈፀሙ ፆታዊ ጥቃቶች ደግመዉ እንዳይረሱ፣ ለተፈፀመው በደል ፍትህ እንዲረጋገጥ አልመው መጽሐፉን ማዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።ፍትህ ለጾታዊ ጥቃት ሰለባዎች
በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል በነበረዉ ግጭት 600,000 ሰዎች መሞታቸዉ እና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዓለም ላይ ግጭት ከሚካሄድባቸዉ አካባቢዎች ከፍተኛ የሟቾች ቁጥር የተመዘገበት በትግራይ እንደሆነ ተመልክቷል። የርዳታ ድርጅቶች የሰብአዊ መብት ጉዳይ ሀኪሞች እና የአፍሪቃ ቀንድ የሕግና ተጠያቂነት ቢሮ ጸሐፍት፤ የሰሜን ኢትዮጵያዉ ጦርነት ከሁለት ዓመታት በኋላ በሰላም ስምምነት በይፋ ቢያበቃም፣ ከኢትዮጵያ እና ከኤርትራ መንግስታት ጋር ጥምረት ያላቸው ወታደራዊ ኃይሎች ማሳቃየት ማዋረድ እና አስገድዶ መድፈርን ጨምሮ ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ስለመፈፀማቸዉ ከፍተኛ ጥርጣሬ መኖሩን የምርመራ መረጃን አስደግፎ ዘግቧል።የብዙ ሴቶችን ሕይወት ያጨለመው ጾታዊ ጥቃት
ይህን ጽሑፍ ካቀረቡት መካከል በዋሽንግተን ዲሲ -ጆርጅታውን ዩኒቨርስቲ የሕክምና ኮሌጅ መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር ራኒት ሚሾሪ እንደተናገሩት፤ በርግጥም የሕክምና መዝገቦችን መርምረን በሕይወት የተረፉትን ሰዎች ራሳችን ቃለ-መጠይቅ ባለማድረጋችን በእርግጠኝነት ማወቅ እና ጉዳዩን ማጣራት ግን አልቻልንም ብለዋል። ይሁን ይላሉ በመቀጠል የጆርጅ ታዉን ኮሌጅ መምህሯ ራኒት፤ በሁሉም መረጃዎች በወንጀሉ የልዩ ወታደራዊ ቡድኖች እና ኃይላት የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መንግሥታት ወታደሮች እንዲሁም የፋኖ ሚሊሺዎች እና ጥቂት የትግራይ ኃይሎች በወንጀሉ አሉበት ብለዋል።አምነስቲ፤ በኢትዮጵያ ወሲባዊ ጥቃት ለደረሰባቸዉ ፍትህ
"እስካሁን ያየናቸው የሕክምና መረጃ መዝገብት እንደሚያሳዩት የጾታ ጥቃት የደረሰባቸዉ ሴቶች ከባድ አካላዊም ሆነ ሥነ-ልቦናዊ ጉዳት ለአጭርም ጊዜም ሆነ በዘላቂነት ተጋፍጠዋል። ለምሳሌ የመንፈስ ጭንቀት እንዲሁም የመራቢያ አካላት የተለያዩ ጉዳቶችና የጤና እክሎች ይገኙበታል።"
አዜብ ታደሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ