1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በልዩነት ውስጥ አንድነትን የሚጠይቀው የጀርመኑ ፕሬዝዳንት አዲስ መፅሐፍ

ፀሀይ ጫኔ
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 17 2016

የጀርመን ፌዴራል ፕሬዝደንቶች በሥልጣን ላይ እያሉ መጽሐፍ መፃፍ ብዙ ጊዜ የተለመደ ባይሆንም፤ ከሰባት ዓመታት በላይ ጀርመንን በፕሬዚዳንትነት እየመሩ ያሉት ፍራንክ ዋልተር ሽታይንማየር ይህንን አድርገዋል።ሽታይንማየር በቅርቡ ባወጡት «እኛ» በተሰኘው አዲሱ መጽሃፉቸው በብዝሃነት ውስጥ አንድነትን ይፈልጋሉ።

https://p.dw.com/p/4fC0R
Deutschland Bundespräsident Steinmeier in der Türkei
ምስል EPA/ERDEM SAHIN

የጀርመኑ ፕሬዝዳንት በአዲሱ መጽሃፉቸው በልዩነት ውስጥ አንድነትን ጠይቀዋል

የጀርመን ፌዴራል ፕሬዝደንቶች  በሥልጣን ላይ እያሉ መጽሐፍ መፃፍ ብዙ ጊዜ የተለመደ ባይሆንም፤ ከሰባት ዓመታት በላይ ጀርመንን በፕሬዚዳንትነት እየመሩ ያሉት  ፍራንክ ዋልተር ሽታይንማየር ይህንን አድርገዋል።
ፕሬዚዳንቱ እንዳሉት ፤ይህ ውሳኔ በጀርመን ታሪክ ውስጥ በዚህ ዓመት በሚከበሩ ሁለት ዋና ዋና በዓላት ማለትም በጎርጎሪያኑ ግንቦት 23 ፣ የጀርመን ሕገ መንግሥት የታወጀበት 75 ኛ ዓመት  እንዲሁም ህዳር 9 ቀን የበርሊን ግንብ የፈረሰበት 35 አመት የሚከበርበት በመሆኑ ነው። 
ፕሬዚዳንቱ ይህንኑ ጉዳይ ያለፈው የገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ሲያስተላልፉም አንስተውታል።  
«በሚቀጥለው አመት የዲሞክራሲ ስርአታችንን 75ኛ የልደት በአል እናከብራለን። መሰረታዊ ሕጋችን 75 ዓመት የሞላው ሲሆን ከ34 ዓመት ያላነሰ ጊዜም አሁን በተዋሃደችው አገራችን ላይ ተግባራዊ ሆኗል:: ይህ ሁላችንም በዓሉን ለማክበር ምክንያት ይሰጠናል።»

ሽታይንማየር የቀኝ ዘመም  ማንሰራራትን ይሰጋሉ

ፕሬዚዳንቱ የቀኝ ዘመም ፖለቲካ ማንሰራራት ያሳስባቸው ይመስላል።ወሳኝ ክንውኖች  ስንመለከት ፕሬዚዳንቱ ፤ በአንፃራዊነት በመንግስት ጉዳዮች ላይ ሀገር የመወከል ሚና የሚጫወቱ ቢሆንም፤ የሀገሪቱን ሁኔታ ሲያጤኑ ግን፤ ጥሩ የተሰማቸው አይመስልም።
የጀርመኑ ፕሬዚዳንት ዋልተር ሽታይንማየር በጀርመንኛ «WIR»ወደ አማርኛ ሲመለስ “እኛ” በሚል ርዕስ በጻፉት መፅሀፍ በታላቅ ጥርጣሬ ውስጥ ያለች ሀገርን ገልፀዋል።

ሽታይንማየር በቅርቡ ባወጡት  "እኛ" በተሰኘው አዲሱ መጽሃፉቸው በመከፋፈል ውስጥ  ብዝሃነትን ይፈልጋሉ
ሽታይንማየር በቅርቡ ባወጡት "እኛ" በተሰኘው አዲሱ መጽሃፉቸው በመከፋፈል ውስጥ ብዝሃነትን ይፈልጋሉምስል Bernd von Jutrczenka/picture alliance/dpa

እንደ የቀኝ ዘመም ፖለቲካ እና ሕዝበኝነት፣ የብዙ ሰዎች ተስፋ መቁረጥ፣ በዴሞክራሲ ላይ ጥርጣሬ፣ ከስደት ጋር የተያያዙ ያልተፈቱ ጉዳዮች፣  የመንግሥት ድጎማ እና የአየር ንብረት ለውጥን በመዋጋት ረገድ ሽታይንማየር ብርቱ ሀሳብ የገባቸው ይመስላል። 
ፕሬዚዳንቱ በመፅሃፋቸው ጀርመን «ሁልጊዜ ያልተጠበቀ ነገር መጠበቅ ያለባት ሀገር ሆናለች» ሲሉ አስፍረዋል። እንደ ፕሬዚዳንቱ ፤የሰዎችን ህይወት ሽባ አድርጎ የነበረውን የኮሮና ተዋህሲ  መከሰት ወይም በክረምት ወቅት ለማሞቂያ የሚሆን ጋዝ ያሳጣውን የዩክሬን  ጦርነት ሰዎች መሠረታዊ በሆኑ ነገሮች ላይ ያላቸውን እምነት አሳጥተዋል።የጀርመን ፕሬዚደንት የአፍሪቃ ኅብረት ጉብኝት
ፕሬዚዳንቱ ከዚህ ቀደምም  በአንድ ንግግራቸው ተመሳሳይ ሀሳብ አንስተዋል። «ይህ ዓመት በሀገራችንም ብዙ ያልተፈቱ ጉዳዮችን ትቷል። አንዳንድ ሰዎች መንግስትን እና ፖለቲከኞችን በጥርጣሬ ሲመለከቱ አንዳንዶቹ ደግሞ ስለወደፊቱ ይጨነቃሉ። ሁላችንም ሰላም የሰፈነበት ዓለም እንናፍቃለን።እኔም ተመሳሳይ ስሜት ይሰማኛል። እና በፍጹም ይህንን መተው እንደሌለብን እምነቴ ነው።»

ፕሬዝደንት ድልድይ ሰሪ አይደለምን?

ሽታይንማየር ትንንሽ ከተሞችን እና ማህበረሰቦችን ጨምሮ ሃሳባቸው የሚለይ ሰዎችን ጨምር ለማነጋገር ያለመታከት በመላ ሀገሪቱ ተዘዋውረዋል።  ለዚህም ይመስላል ፕሬዚዳንቱ በሰዎችች መካከል አንድ የሚያደርገውን "እኛ"ን ለመፈለግ ሙከራ ያደረጉት።
ያም ሆኖ፤ በአንድ በኩል በማህበራዊ ቀውሶች እና ወቅታዊ የፖለቲካ ውዝግቦች ላይ በመጽሃፉቸው እንዳደረጉት ግልፅ አቋም መያዝ  ወይስ፤ እንደ ርዕሰ ብሄርነታቸው  ከወቅታዊ ሁኔታዎች ባሻገር በሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች መካከል ድልድዮችን ለመስራት መሞከር አለባቸው?የሚሉ ሁለት መሰረታዊ ጥያቄዎች በፕሬዚዳንቱ ላይ እየተነሱ ነው።

የጀርመን ፕሬዚዳንት ዋልተር ሽታየንማየር ከብሪታኒያ የንጉሳዉያን ቤተሰቦች ጋር
የጀርመን ፕሬዚዳንት ዋልተር ሽታየንማየር ከብሪታኒያ የንጉሳዉያን ቤተሰቦች ጋር ምስል picture-alliance/dpa

ፕሬዚዳንቱ የጀርመንን ስሕተቶች እና ያለፉ የተሳሳቱ ውሳኔዎችን በመጽሃፋቸው ብዙም አልዳሰሱም። 
ለመሆኑ፣ ሽታይንማየር እንደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ሀገሪቱ ለረጅም ጊዜ ራሷን ወደ ያልተጨበጠ የደኅንነት ስሜት ውስጥ እንድትገባስ ትልቅ ሚና አልተጫወቱምን? ከጎርጎሪያኑ 2005 እስከ 2009 ዓ/ም ፣ ከዚያም ከ2013 እስከ 2017 የቀድሞ የሶሻል ዴሞክራት ፓርቲ  ፖለቲከኛ እና የጀርመን ከፍተኛ ዲፕሎማት ነበሩ። በጎርጎሪያኑ 2014 ዓለም አቀፍ ህግን በመጣስ ሩሲያ ክሬሚያን ስትይዝም በዚያ ሀላፊነት ላይ ነበሩ። የፕሬዝዳንት ሽታይንማየር የኢትዮጵያ ጉብኝት

ከሞስኮ ጓደኝነት ወደ ከሰላ ትችት

ሽታይንማየር ብዙ የጀርመን ፖለቲከኞች በጎርጎሪያኑ የካቲት 2022 ዓ/ም በዩክሬን ጦርነት እስኪቀሰቀስ ድረስ ከሞስኮ ጋር ሲነጋገሩ መቆየታቸውን ይገልፃሉ።አሁን ግን “ጦርነቱ የሞስኮን ኢ-ፍትሃዊ አገዛዝ እየዳከመ ነው። የሩሲያ ማህበረሰብ በታሪካዊ ሚዛን ተጠያቂ እያደረገ ነው” ሲሉ ፅፈዋል። 
ነገር ግን  በወቅቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በነበሩበት ወቅትስ እነዚያ ምልክቶች ቀደም ብለው አልነበሩምን? በማለት ፕሬዚዳንቱን የሚጠይቁ አሉ።

ስለ ጀርመን ማህበረሰብ አቃፊነት እና ብዝሃነት

በጀርመን ውስጥ ያሉ አብዛኛዎቹ ሰዎች በመጽሐፉ ውስጥ ከተገለጹ ነገሮች ጋር ይስማማሉ ፣ ለምሳሌ ፣ ስለ ጀርመን ማህበረሰብ አቃፊነት ባሰፈሩት ፅሁፍ፤ ከሌሎች ሀገሮች እና ባህሎች የመጡ ሰዎች ያለማቋረጥ ይቀላቀሉታል።ብለዋል።
"ወደ እሱ የፈለሱ፣ በውስጡ ያሉ፣ አዲስ ዜግነት በመምረጥ ጀርመን የሆኑ" ሁሉ  እንደማንኛውም ዜጋ እኩል  ናቸው። ብለዋል።
በሌላ ጫፍ ላሉት ቀኝ ዘመሞች ግን እነዚህ ሀሳቦች ውድቅ ናቸው።."ስቴይንማየር ስለ ቀኝ ክንፍ ህዝበኞች ሲናገሩ፡- “አንዳንዶቹ እንዲህ አይነቱን አንድአይነትነት በግዳጅ ለመፍጠር እና ህጉን የማይመጥኑ ጀርመናውያንን በግዳጅ ለመፍጠር ይፈልጋሉ።አብዛኞቹ ዜጎች እንዲህ ያለውን ኢ-ህገመንግስታዊ ቅዠቶች ይቃወማሉ።ብለዋል።

የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ትችት እና ባህል 

ነገር ግን የፕሬዚዳንቱን የ"እኛ" ጽንሰ-ሀሳብ የማደግፉ እና ውይይቶቻቸውን በራሳቸው የዲጂታል መድረኮች የሚያካሂዱ ሰዎች ጥቂቶች አይደሉም። 
ሽታይንማየር እነዚህን ችግሮች በመገንዘብ «መነገር የሚችሉ ነገሮች መነገር በሌለባቸው  ነገሮች ተገፍተው ድንበር ተሻግረው ሩቅ ተጉዘዋል። ጭካኔ በፖለቲካ ቋንቋ ውስጥ ሥር ሰዶ እንደ ድል አድራጊ እና ደፋር ያስቆጥራል። በተቃራኒው ለእያንዳንዱ ግልፅ ቃላት ጥቃት በማድረስ፤ በግልፅ ሀሳብህን መናገር እንደማትችል ብዙዎች ያረጋግጡልሃል።»በማለት በመፅሀፋቸው አስፍረዋል።.
የሽታይንማየር ዓላማ  ዝምያለውን ሰፊ የህብረተሰብ ክፍል/ Silent Majority/ከዚህ ቡድን በተፃራሪ ማሰባሰብ እና በስልጣን ላይ ባሉ ፖለቲከኞች እምነት እንዲኖራቸው ማበረታታት ነው።
ሽታይንማየር በመፅሃፋቸው «ጀርመን በተለወጠ ሁኔታ ውስጥ መሆኗ ተጠያቂዎቹ ክፉ ፖለቲከኞች ብቻ እንዳልሆኑ መገንዘብ ያስፈልጋል። የትኛውም የጀርመን ፖለቲከኛ ዓለም ወደ እኛ  ፊቱን እንዲመልስ ማዘዝ አይችልም» በማለት ይህንኑ የህብረተሰብ ክፍል ተማፅነዋል። 

የ68 ዓመቱ አንጋፋ ፖለቲከኛ ዋልተር ሽታየንማየር በጎርጎሪያኑ ሚያዚያ  2017 ዓ/ም ደግሞ የጀርመን 12ኛ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመርጠዋል። በየካቲት 2022 ዓ/ም ለሁለተኛ ጊዜ ተመርጠው ሀገራቸውን በፕሬዚዳንትነት በማገልገል ላይ ይገኛሉ
የ68 ዓመቱ አንጋፋ ፖለቲከኛ ዋልተር ሽታየንማየር በጎርጎሪያኑ ሚያዚያ 2017 ዓ/ም ደግሞ የጀርመን 12ኛ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመርጠዋል። በየካቲት 2022 ዓ/ም ለሁለተኛ ጊዜ ተመርጠው ሀገራቸውን በፕሬዚዳንትነት በማገልገል ላይ ይገኛሉምስል Wolfgang Kumm/dpa/picture alliance

የጀርመን ፕሬዚዳንት ሚና

የጀርመን ፕሬዝዳንት ስልጣን የተገደበ ሊሆን ይችላል፣ነገር ግን ሽታይንማየር የቢሮ ስራ እንዳደከማቸው  በመጽሃፋቸው ይታያል።
ለአገሪቱ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ያላቸው ሀሳብ  አንድ ነገር ቢሆንም፤መፅሀፋቸው የጎደለው  በዓለም ላይ ካሉት ሀብታም ሀገሮች አንዷ የሆነችውን እና ሕገ መንግሥታዊ ስርዓት ያላትን ጀርመንን በትክክል መገምገም ነው። ምክንያቱም፤ እንደ እነዚህ ያሉ ውጣ ውረዶች እዚህ ሀገር ብቻ የሚታዩ አይደሉም። በመፀሀፋቸው እንደሚታየው፤ የቀድሞ ኃያል ፖለቲከኛ ሽታየንማየር፤ እነዚህን አስቸጋሪ ጊዜያት ለመቅረጽ ብዙ ሚና መጫወት ባለመቻላቸው የተወሰነ ብስጭት የተሰማቸው ይመስላል።ነገር ግን በዙሪያቸው ያለው ዓለም ምንም ያህል የተመሰቃቀለ ቢመስልም፤  ሚናው በተገደበ ስልጣናቸውም ቢሆን፤ሀገር የመወከል ተግባር የእሳቸው ሥራ  ነው።ጀርመን አዲስ ፕሬዚዳንት መረጠች

የ68 ዓመቱ አንጋፋ ፖለቲከኛ ዋልተር ሽታየንማየር ለበርካታ ዓመታት የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን፤ በጎርጎሪያኑ ሚያዚያ  2017 ዓ/ም ደግሞ የጀርመን 12ኛ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመርጠዋል። በየካቲት 2022 ዓ/ም ለሁለተኛ ጊዜ ተመርጠው ሀገራቸውን በፕሬዚዳንትነት በማገልገል ላይ ይገኛሉ። 


ፀሀይ ጫኔ
አዜብ ታደሰ