ስለ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሕዝብ አስተያየት
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 9 2015በአማራ ክልል የተፈጠረውን ወቅታዊ የፀጥታ መደፍረስን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት በትናትናው እለት አደጋውን ለመቀልበስ ይረዳኛል ያለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አጸድቋል ። ይሁንና ሕጉ በተወካዮች ምክር ቤቱም ብርቱ ሙግት ገጥሞታል ።
ከአሁናዊ የክልሉ ሁኔታ እና ዘላቂ እልባቱ ጋር በተያያዘም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አስፈላጊነት ላይ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡ ነው ። «ህዝብ አንደ ሕዝብ ተነሳ» ጥያቄውም መመለስ ይገባዋል እንጂ አስኳይ ጊዜ አዋጅ አያስፈልግም ሲሉ አስተያየት የሰጡ አሉ ። ሌላኛው አስተያየት ሰጪ ደግሞ፦ «ሕግ እና ስርዓት ማስከበር ሳይቻል ሀገርን ለመታደግ የሚታወጅ አዋጅ ስለሆነ» ሀገርን ለመታደግ አስፈላጊ ነው የሚል አተያየት ሰጥተዋል ።
ሌላ አስተያየት ሰጪ በበኩላቸው «የኢፌዴሪ ሕገመንግሥትን» ጣቅሰው አዋጁ ተገቢ ነውብለዋል ። «በሰላማዊ ሰልፍም ሆነ» በሌሎች መንገዶች ጥያቄዎችን ብጠይቅ መልስ አላገኘሁም ያለ ማኅበረሰብ «ብቸኛው አማራች ሊሆን የሚችለው ነፍጥ አንስቶ ከመንግስት ጋር መዋጋት ነው የሚል ደግሞ ይሄ ሌላ ዕይታ ሊሆን ይችላል» ብለዋል።
ኢሰመኮ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በአማራ ክልል ብቻ እንዲወሰን ለመንግስት ጥሪ አቀረበ
ዘጋቢችን ሥዩም ጌቱ ከተወሰኑ የተለያዩ አስተያየቶች ከሰነዘሩ የማኅበረሰብ አካላት ሐሳባቸውን አጠይቋል፡ ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን የተቃወሙም የደገፉም አሉበት ።
ሥዩም ጌቱ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ