ማስታወቂያ
የኬንያ ፖሊስ ባለፈው ሚያዚያ ምስራቃዊ ኬንያ የሚገኝ ሻካሆላ ደን ውስጥ በብዛት በጅምላ የተቀበሩ ሰዎች አግኝቷል። ከዚያን ጊዜ አንስቶ የሟቾች ቁጥር ከፍ ብሎ 201 ደርሷል። ሟቾች ራሱን «ጉድ ኒውስ ኢንተርናሽናል ቸርች » ብሎ የሚጠራ ቡድን አባላት ሲሆኑ የአለም ፍፃሜ ከመምጣቱ በፊት ሰማይ ቤት ለመግባት በሚል ተርበው ሞተዋል። የኬንያ ባለስልጣናት ለዚህ የቡድኑ መሪ ፓውል ማኬንዚን ተጠያቂ ያደርጋሉ።
ከዚህ ሞት ጋር ተያይዞ በመላው አፍሪቃ ያሉ የብልጽግና ሰባኪዎች በሌላው ህዝብ ዘንድ ጥያቄ ውስጥ ገብተዋል። እነዚህ ሰዎች ልዩ መንፈሳዊ ኃይል እንዳላቸው ሰዎችን እያሳመኑ በምትኩ ውለታ እንዲዋልላቸው ይጠይቃሉ። ነገር ግን ይህ በተከታዮቻቸው እና በቤተሰቦቻቸው ላይ አስከፊ መዘዝ ሊያስከትል ይችላል። #77ከመቶው