7ኛው ዙር የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ዘመቻ በኢትዮጵያ
ሰኞ፣ ኅዳር 9 2017ክትባቱ ዛሬ በባሕርዳር ከተማ ድልችቦ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲጅመር የተገኙት በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሚኒስትሯ የክትባት አማካሪ አቶ ዮሐንስ ላቀው እንዳሉት በዚህ 7ኛ ዙር በተባለው የክትባት ዘመቻ 7 ሚሊዮን 500 ሺህ እድሜያቸው ክ9 እስክ 14 ዓመት የሆነ ታዲጊ ሴት ህፃናት ክትባቱን ይወስዳሉ፡፡
በአማራ ክልል 1.6 ሚሊዮን ህፃናት የማህፀን በር ክትባት ይወስዳሉ
የአማራ ክልል ጤና ቢሮ የእናቶችና ህፃናት ክትትል ዳይሬክተር አቶ መልሰው ጫንያለው በበበኩላቸው በአማራ ክልል 1 ሚሊዮን 600 ሺህ ወጣት ሴቶች ክትባቱን ያገኛሉ ብለዋል፡፡ እንደኃላፊው ከ2011 ዓም ጅመሮ ለ7ኛ ጊዜ የሚስጠው ክትባት ከ9 ዓመት እስከ 14 ዓመት ክልል የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ወጣተ ሴቶች ናቸው፡፡ በዚህ ዓመት ክትባቱን የሚወስዱ ሴቶች ቁጠር ከፍተኛ መሆኑን አመልክተው፣ ይህም በአማራ ክልል ብቻ ተካታቢዎች 1.6 ሚሊዮን ናቸው ብለዋል፡፡ ይህ ቁጥር ባለፉት 6 ዓመታት የተከተቡትን እንደሚስተካከልም አቶ መልሰው ተናግረዋል፡፡በባሕርዳር ከተማ ድል ችቦ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ክትባቱን ካገኙ ተማሪዎች መካክል ተማሪ ዳናዊት ደረጀን ስለክትባቱ አስፈላጊነት ተናግራለች፡፡የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት በኢትዮጵያ
አስቀድሞ መጠንቀቅ ያስፈልጋል አስፈላጊነት
“መጀመሪያ ጥንቃቄ አስፈላጊ ነው፣ ከዚያ ባለፈ ደግሞ የመጣውን እድል መጠቀም ጊዜ ሊስጠው አይገባም” ብላለች፡፡ አርሴማ ጥላሁን የተባለች ሌላ የዚሁ ትምህርት ቤት ተማሪም ጓደኞቿ እድሉን እንዲጠቀሙበት መልዕክት አስተላልፋለች፡፡ ክትባቱ የጎላ የህመም ስሜት እንደሌለው ያመለከተችው አርሴማ የትምህርት ቤት ጓደኞቿም ሆኑ የሰፈር አብሮአደጎቿ እንዲከተቡ አደራ ብላለች፡፡
ኅብረተሰቡ ክትባትን ሊለምደው ይገባል
የአማራ ክልል ሐይማኖት ተቋማት ምክር ቤት አስተባባሪ አቶ ፋሲል ታዬ ህብረተስቡ ህፃናት ክትባቱን እንዲወስዱ በማድረግ ከሞት እንዲታደጋቸው ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ባልዳበረበት ጊዜ በሽታዎች ህብረተስቡን በከፍተኛ ሁኔታ ይጎዱ እንደነበር አመልክተዋል፡፡በመሆኑም ወላጆች ህፃናቱ እንዲከተቡ ማድረግ ተገቢ መሆኑን አቶ ፋሲል ገልጠዋል፡፡ ህብረተሰቡም ክትባትን ልምዱ ሊያደርገው እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡
የማህፀን በር ካንሰር በኢትዮጵያ በየዓመቱ የ8000 እናቶችንና ወጣት ሴቶችን ህይወተ እንደሚቀጥፍ የጤና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ 5 ቀናት በመላ አገሪቱ እንደሚሰጥ የጤና ባለሙያዎቹ ገልጠዋል፡፡
ዓለምነው መኮንን
ኂሩት መለሰ
ታምራት ዲንሳ