ይህ ስሜት ከመንግስት ትምህርት ቤቶች ጋር ሲነጻጸር የተሻለ ውጤት ሲያስመዝገቡ በቆዩት የግል ትምህርት ቤት ተማሪዎች ላይ ጭምር የሚታይ ነው። የቅዱስ ዩሐንስ መጥምቅ ደላሳል ካቶሊክ ትምህርት ቤት ተማሪ የሆነችው የአብስራ መላኩ፤ ከእነዚህ ተማሪዎች መካከል አንዷ ናት።
በትምህርቷ ጥሩ ውጤት ስታመዘግብ የቆየችው የአብስራ፤ የ11ኛ ክፍል ተማሪ እያለች ወደ ዩኒቨርስቲ የማለፊያ ነጥብ ያመጡ ተማሪዎች ቁጥር አነስተኛ መሆኑን ስትሰማ ለጉዳዩ እምብዛም ትኩረት አልሰጠችውም ነበር። ለ12ኛ ክፍል ፈተና እየተዘጋጀች ባለችበት በዚህ ዓመት ይፋ የተደረገውን ውጤት ስትስማ ግን የነበራት ስሜት የተለየ ነበር።
“የአሁኑን ውጤት ስሰማ፤ ያለፈው ተማሪ ጭራሽ [ካለፈው ዓመት] በሆነ ነጥብ ቀንሷል። በዚህ በጣም ተደናግጬ ነበር። ‘ባላልፍስ’ የሚል ጭንቀት ውስጥ ከትቶኝ ነበር” ስትል በወቅቱ የነበራትን ስሜት ትገልጻለች። በእርሷ ትምህርት ቤት የሂሳብ መምህር የሆኑት ማርታ ዋቅጅራ፤ የ12ኛ ክፍል ውጤት በጣም ዝቅ እያለ በመምጣቱ በተማሪዎች ዘንድ ጭንቀት መኖሩን ያረጋግጣሉ።
አንዳንድ ወላጆች በጣም ከመጨነቃቸው የተነሳ ወደ ትምህርት ቤት በመምጣት አስጠኚ አስተማሪዎችን እንደሚቀጥሩ መምህሯ ያክላሉ። በተፈታኝ ተማሪዎች ላይ የሚታየውን ይህን ጭንቀት ለመቅረፍ የትምህርት ቤቱ መምህራን “የአጠናን ቴክኒኮችን” ከመንገር ጀምሮ የተለያዩ መንገዶችን የማስተማሪያ መንገዶችን በመጠቀም የማስተማሪያ መንገዶችን እየተጠቀሙ ከወትሮው የተለየ ዝግጅት በማድረግ ላይ እንደሚገኙም ያብራራሉ። #77ከመቶው
ቪዲዮ: ተስፋለም ወልደየስ