የአፍሪቃ ህብረት በICC ላይ ያሳለፈዉ ውሳኔ
ቅዳሜ፣ ጥቅምት 2 2006የኢትዮጵያ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፤ የአፍሪቃ ሕብረት ትናንት በተደረገዉ ልዩ የሚኒስትሮች ሥብሰባ ፤ የዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት፤ በኬንያዉ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ላይ የተጀመረዉ ክስ፤ ፍጹም ተቀባይነት የለዉም ሲል መስማማቱን ገለጹ። አፍሪካ የዓለም አቀፉ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት መሞከሪያ መሆን የለባትም ያሉት የአፍሪቃ ውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች፤ በኬንያታ ላይ የተጀመረዉ የፍርድ ሂደት፤ ኬንያ አሸባሪዎችን ለመዋጋት የጀመረችዉን ስራዋን የሚያደናቅፍ ተግባር ነዉ ሲል፤ የአፍሪቃዉ ሕብረት፤ ማሰቡን፤ የኢትዮጵያዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲና ሙፍቲ ለፈረንሳዩ ዜና ወኪል በስልክ ገልፀዋአል። በዘር ጭፍጨፋ ወንጀል ጉዳይ አፍሪቃዉያን ፤ በአፍሪቃ ሕብረት የተደገፈ ፍርድ ቤት እንዲዳኙ እንጂ በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት ዴንሃግ ድረስ እንዲቀርቡ መገደድ የለባቸዉም ሲል ምክር ቤቱ፤ ሃሳብ ማቅረቡም ተያይዞ ተዘግቧል። የአፍሪቃ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በደረሱበት በዚህ አቋም ላይ ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ጉባኤ የተቀመጡት የአፍሪካ መሪዎችም ይደግፉታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በስፍራው ጉባኤውን ከተከታተለው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ጋ የተደረገውን አጭር ቃለ መጠይቅ ከዚህ በታች ያገኙታል ።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ልደት አበበ