ማስታወቂያ
ታዳጊዋ በስዕል ችሎታዋም የተካነች ነች፡፡ ለባህላዊና ዘመናዊ ፋሽን የሚውሉ የተለያዩ አልባሳት ዲዛይን የማኖር ክህሎት አላት፡፡ ሶፊያ ከስዕል ችሎታዋም በተጨማሪ በኮምፒዩተር ኮዲንግ ስራ ድረገፅ በማበልጸግ ላይ ስትሆን ይህንንም ኢትዮጵያ የምትታወቅባቸው የባህላዊ መድኃኒቶችን ከነጥቅማቸው ማስተዋወቂያ ለማዋል ታልማለች፡፡ ከባለ ብርሁ ራዕይ ታዳጊ ሶፊያ ጀማል ጋር የአዲስ አበባ የዶቼ ቬለ ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች አዘጋጅ ሱመያ ሳሙኤል ለቃለ ምልልስ ተቀምጣ ነበር፡፡
ዘገባ: ሱመያ ሳሙኤል
ቪዲዮ: ሥዩም ጌቱ