1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኪነ ጥበብአፍሪቃ

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች

ረቡዕ፣ ግንቦት 2 2015

አዲስ አበባ ውስጥ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 የወጣቶች ማዕከል የዜማ እና የኔታ ኪነ ጥበብ ቡድን ስር ተሰባስበው ተሰጥዋቸውን እያዳበሩ ከሚገኙ 50 ታዳጊዎች መካከል 40 ገደማ የሚሆኑቱ ሴት ታዳጊዎች ናቸው፡፡

https://p.dw.com/p/4R7hb

ዕድሜያቸው ከ9-18 የሚካተተው ከ5ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የትምህርት ደረጃ ላይ የሚገኙ ታዳጊዎቹ ከትምህርታቸው በማይጋጭ መንገድ በሳምንታት የመጨረሻ ቀናት በዚህ የትያትር ቡድን ተሰባስበው እንደየተስጥዋቸው የተለያዩ የኪነጥበብ ሙያዎችን ይለማመዳሉ፡፡
ግጥም፣ መነባንብ፣ ትወና (ትያትር)፣ ሽለላ እና ሙዚቃ ታዳጊዎቹ በስፋት ከሚለማመዱት ተሰጥዋቸውንም ከሚፈልጉበት የጥበብ ዘርፎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ 
በዚህ የኪነጥበብ ቡድን የሚታደሙት ሴቶች፤ እያሳዩት በሚገኙት ድንቅ ችሎታቸው በተለያዩ አገራዊ መድረኮች ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ፣ ተመልካችንም ያስደምማሉ።
የዶይቼ ቬለ ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች መሰናዶ ከዚህ የኪነጥበብ ቡድን ጋር ቆይታ ባደረገበት ወቅት የትያትር ቡድኑ ኃላፊ እና በትያትር ቡድኑ ውስጥ የነቃ ተሳትፎን ከሚያደርጉ ሴት ታዳጊዎች ጋር አጭር ቆይታ አድርጓል፡፡ #ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች #GirlzOffMute

ዘገባ፡ ሱመያ ሳሙኤል
ቪዲዮ፡ ሥዩም ጌቱ