ከእንግዲህ የልብ ህሙማንን በአገር ዉስጥ ማከም ይቻላል10 የካቲት 2001ማክሰኞ፣ የካቲት 10 2001የዛሬ 30ዓመት አንድ የልብ ህመምተኛ ህፃን ከባህር ማዶ አሻግሮ ማሳከም ብርቅ ነበር። ዛሬ ግን አንድ ህፃን ብቻ ሳይሆን በቀን ከአምስት የሚልቁ ህመምተኞችን አስተኝቶ ደረጃዉን የጠበቀ ህክምና መስጠት የሚያስችለዉ የልብ ህሙማን ሊረዱበት የሚችሉበት ሃኪም ቤት አገር ዉስጥ ተገንብቶ ስራዉን ጀመረ።https://p.dw.com/p/GwAq...ልብ ቀጥ ካለ...ምስል APማስታወቂያ ይህ ብስራት የተማዉ ባለፈዉ ሳምንት ነዉ። ሃኪም ቤቱ በበጎ አድራጊዎች ርብርብ ተገንብቶ ስራ መጀመሩ በስራዉ ለተሳተፉ ታታሪዎች ብቻ ሳይሆን ዜናዉን ለሚሰሙት ሁሉ አመርቂነቱ አያነጋግርም። የሃኪም ቤቱ አገልግሎት እንዳጀማመሩ ለህፃናት ብቻ ሳይሆን አዋቂዎችንም ያካትታል። በቀጣይም የምርምር ማዕከል የሚገነባ ሲሆን ባለሙያዎችን ማሰልጠንኑም በተጓዳኝ ይከወናል።