1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በግሪክ የተካሄደዉ ምርጫ እና ዉጤቱ

ረቡዕ፣ ግንቦት 16 2015

በግሪክ ባለፈው ዕሁድ የተደረገው ምርጫ በጠቅላይ ሚኒስተር ኪሪያኮ ሚትሶታኪስ የሚመራው የመሀል ቀኙ የአዲሱ ዴሞክርሲ ፓርቲ፤ ከተቃውሚው የግራው ሲሪዛ ፓርቲ በከፍተኛ ልዩነት አሸናፊ ሁኗል። ሆኖም ግን አሽናፊነቱ መንግስት ለመመስረት የሚያስችል አብላጫ የፓርላም ወንበር ያስገኘ ባለመሆኑ ዳግም ምርጫን የሚያስቀር አልሆነም።

https://p.dw.com/p/4Rgzr
Prime Minister Kyriakos Mitsotakis
የግሪክ ምርጫምስል Ayhan Mehmet/AA/picture alliance

ለዳግም ምርጫ ከውዲሁ ጥሪ ቀርቧል

በግሪክ ባለፈው ዕሁድ የተደረገው ምርጫ በጠቅላይ ሚኒስተር ኪሪያኮ ሚትሶታኪስ የሚመራው የመሀል ቀኙ የአዲሱ ዴሞክርሲ ፓርቲ፤ ከተቃውሚው የግራው ሲሪዛ ፓርቲ በከፍተኛ ልዩነት አሸናፊ ሁኗል። ሆኖም ግን አሽናፊነቱ መንግስት ለመመስረት የሚያስችል አብላጫ የፓርላም ወንበር ያስገኘ ባለመሆኑ ዳግም ምርጫን የሚያስቀር አልሆነም።  የሚስተር ሚትሶታኪስና ፓርቲያቸው የስልጣን ዘመን የሚያበቃው በመጭው ሀምሌ ወር ቢሆንም፤ ካንድ ወር በፊት በአገሪቱ በተከሰተው የባቡር አደጋ፣ የስለላ ቅሌትና ከፍተኛ የኑሮ ውድነት ምክኒያት በተቀሰቀሰው ተቃውሞ ይህንን ከመደበኛው ግዜ ሳምንትት ቀደም ብሎ ዕሁድ ለት የተካሂደውን ምርጫ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለመጥራት እንደተገደዱ ታውቋል። አሁንም  ግን ህዝቡ  ያንኑ ላለፈው አራት አመት በስልጣን ላይ የነበረውን ፓርቲና ጠቅላይ ሚኒስተር ሚትሶታኪስን ነው በክፍተኝ ድምጽ የመረጠው።። “ ዛሬ የታየው መሬት አንቀጥቅጥ ፖለቲካ፤ ጠንካራ መንግስት ለመመስረት የምናደርገውን ጥረት እንድናፋጥን የሚያደርገን ፍጹም አብላጫ ሊያገኙ የሚችሉበትን ድጋሜ ምርጫ ለመጥራት መሆኑን  አስታውቀዋል።

Still Griechenland Schlagzeilen vor der Wahl
የግሪክ ምርጫምስል DW

የግሪክ አጠቃላይ ህዝብ ብዛት ከአስራ አንድን ሚሊዮን የማይበልጥ  ሲሆን፤ ከዚህ ውስጥ  9.8 ሚሊዮኑ  ለመምረጥ ተመዝግበዋል ተብሏል። በግሪክ የምርጫ ህግ መሰረት አሸናፊ ሆኖ መንግስት ለመመስረት፤ ከመራጩ ህዝብ 46 ከመቶ ድምጽ ማግኘትና ከ300 የፓርላማ መቀመጫም  ቢያንስ 151 መቀመጫ ማግኘት ያስፈልጋል። ይህ ካልሆነ አንደኛ ወይም ሁለተኛ የሆነው ፓርቲ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር በመጣመር መንግስት ለመመስረት የሚችሉ ቢሆንም ይህ ግን በፓርቲዎቹ ባለው የአይዶሊጂና የፖሊስ ልዩነቶች እንዲሁም የግሪክ ፓርቲዎች በጥምረት የመስራት ባህል ማነስ ምክኒያት ብዙ ግዜ አሰቸጋሪ እንደሆነ ነው የሚነገረው። ከሶስቱ ፓርቲዎች በተጨማሪ ሌሎች ሁለት ፓርቲዎች በፓርላማ ለመግባት የሚያስፈልገውን 3 ከመቶና ከዚያ በላይ ድምጽ ያገኙ ቢሆንም፤ አንዳቸውም ተጣምረው ለምስራት ፈቃደኞች እንዳልሆኑ ነው ሲገልጹ የቆዩት። በዚህ ምክኒያት ጠቅላይ ሚኒስተር ሚትሶታኪስ  ያገኙትን ከፍተኛ ድጋፍና ውጤት  መንግስት ለመመስረት ሳይሆን ዳግም ምርጫ ላማካሄድና  ጠንክራ መንግስት ለመምስረት የሚያስችላቸውን አብላጭ የፓርላማ መቀመጫ ለማግኘት እንደሚጠቀሙበት በመግለጽ ለዳግም ምርጫ ከውዲሁ ጥሪ አቅርበዋል ።

የምራቡ ዓለም ስልጣኔ ምጭ የሆነችው ግሪክ፤ ከቀዳሚዎቹ የኔቶ አባል አገሮች የምትመደብ ስትሆን፤ እ እ ከ1981 ዓም ጀምሮ የአውሮፓ ህብረት፤ ከ2001 ጅመሮ ደግሞ የኢሮ ዞን አገሮች አባልም ናት። ግሪክ ከብዙዎቹ የኢሮ ተጠቃሚ አገሮች ከፍተኛ የእዳ ክምችት ያለባትና  መንግስታዊ መዋቅሯም ጉድለት የሚታይበት ነው በመባል የሚተች ሲሆን፤  በተለይ በ2008 እና 9 የተክስተው የኢሮ ዞን የፋይናንስ ቀውስ ግሪክን በክፍተኝ ዕዳ ውስጥ አስገብቷት እንደነበርና ከኢሮ ዞንም ጭራሽ ልትወጣ አፍፋፍ ላይ ደርሳ እንደነበር የሚታወስ ነው።፡ በዓለማቀፍ የገንዘብ ተቋምት ፣ በአውሮፓ ማእከላዊ ባንክና በሌሎች አበዳሪ አገሮች ድጋፍ እንዲሁም እሷም በወሰደችው መራር የመዋቅር ማሻሻያ እርምጃ ከችግሩ ልታገግምና ልትወጣ እንደቻለች ቢነገርም ፤ እስካአሁንም  በኮቪድና የዩኪሬን ጦርነት ምክኒያት የተፈጠረው የኢኮኖሚ ቀውስና የኑሮ ውድነት ዓገሪቱን  በችግር እንድትቆይ አድርጓታል ነው የሚባለው።፡ያም ሆኖ ግን እ እ እ በ2019 ም ወደ ስልጣን የመጡት ሚትሶታኪስና ፓርቲያቸው አገሪቱን ከገባችበት ችግር በማውጣት በኩል የተሻለ ስራ እንደሰሩና የግሪክን ፖለቲካና ኢኮኖሚ ገጽታ እንዳሻሽሉት ነው የሚነገርላቸው። ግን አሁንም በግሪክ የኑሮ ውድነቱና በችግር ውስጥ ያለው ህዝብም ብዛት በአንጻራዊነት ከፍተኛ እንደሆነ ነው የሚነገረው። ከዚህም በቀር ግሪክ በፕሬስ ነጻነትና የህግ የበላይነት ላይም ከህብረቱ አገሮች ከሚተቹት ውስጥ ናት፡፤ የደህንነት ተቋሙ የጋዜጠኖችንና የተቃዋሚ ፖለቲከኞችን  ስልኮች በመጥለፍም ሲከሰስ ቆይቷል። መንግስታዊ ያልሆነውና በዴሞክራሲ ላይ የሚሰራው Democracy Reporting International ( DRI) የተሰኘው ድርጅት ባልደረባ ወይዘሪት ኒኖ ጼሬቴሊ እንደምትለው የግሪክ ባለስልጣኖች በዚህ የስልክ ጠለፋ ቅሌት ላይ የሚደረገውን ምርመራ እያደናቀፉ ነው።  “የፖለቲክ ባለስልጣኖች በስልክ ጠለፋና ስለላው ወንጀል ላይ የሚያደረገውን ክትትልና ምርመራ እያደናቀፉ በመሆኑ በዚህ ወንጀል ላይ የሚደረገው ምርመራ ግዜ ሊወስድና ውጤቱም ሊዘገይ ይችላል” በማለት በዚህ የስልክ ጠለፋ ወንጀል የመንግስት ዕጅም ሊኖርበት ይችላል የሚሉትን ተጠራጣሪዎች አስተያየት አጠናክራለች።

 በዚህ ሁሉ ቀውስና ተቃውሞ መሀል  አሁንም ጠቅላይ ሚኒትሩና ፓርቲያቸው አሸናፊ የሆኑበት ዋናው ምክኒያት ግን፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚትሶታኪስና መንግስታቸው ከነችግርቻቸውም ቢሆን   ግሪክን ሉኡላዊነተኗንና ከፈታተነውና ክብሯን ዝቅ ካድረገው የፋይናንስ ቀውስና የኢኮኖሚ ድቀት እንድታገግም ማድረግ በመቻላቸው ነው ይባላልም። በጣሊያን ሚላን ቦኮኒ ዩንቨርስቲ ተመርማሪ የሆኑት ሚስተር ዳኒየል ክሮስ የግሪክን ያለፉትን አመታት የስራ አፈጻጸም ከሚያወድሱት አንዱ ናቸው። “ በመስረቱ ግሪክ ያለፉትን ሁለት ቀውሶች የኮቪድንና የህይል ቀውሶችን በተሻለ ሁኔታ ከተቁቁሙት  የህብረቱ አገሮች አንዷ ለመሆን ችላለች። ጠንካራ የፊስካል ፖሊስ በማውጣትና በመተግበር ጥሩ ውጤት አስገኝታለች በማለትም ያሁኑ የምርጫ ውጤት የዚህ ፍሬ ሊሆን እንደሚችል ግምታቸውን ገልጸዋል።

ያም ሆኖ ግን ከነባሩ  ሁኒታና በመንግስት ላይ ከታየውና ይሰማ ከነበረው ተቃውሞ አንጻር የተገኘው  ውጤት ከተጠበቀው ውጭ እንደሆነ ነው በብዙዎች የሚነገረው። ተወዳዳሪዎቹ ፓርቲዎች በተለይም ዋናዎቹ፤ ማለት አዲሱ ዴሞክራሲ፤ የግራዎቹ ሲሪዛና መሀል ግራው ሶችሊስቱ  ፓርቲዎች በምረጡኝ ዘመቻወቻቸው ያተኮሩባቸውን አጅንዳዎች በዋናነት በኢኮኖሚ እድገትና በኑሮ ውድነት ላይ ያተኮሩ እንድነበሩ ምርጫውን ይከታተል የነበረው ጋዜጠኛ ጊዮርጎስ ክሪስቴዴስ ያስረዳል። “ የወግ አጥባቂ የመሀል ቀኝ ፓርቲ ያተኮረው  በኢኮኖሚው፣ ደህንነትና ስደተኖችን በመከላከል ላይ እንደሚሰራና የተጀመሩ ጥሩ ስራዎችን እንደሚያስቀጥል ነበር። ዋናዎቹ  ተቃዋሚዎቹ ሲርዛና ሶሻሊስቱ ደግሞ ከሁሉም በላይ በህግ የበላይነት መከበር ላይና  በስልክ ጠለፋ ወንጀሉ ላይ በማተኮር ለውጥ እንደሚያስፈልግ በመግለጽ ነበር ብሏል።

ህዝብ ተመሮና ለውጥ ጠይቆ ከወጣ በኋላ ምርጫ ሲደረግ፤ ያው ጥያቄ ሲነሳበት የነበረው ፓርቲ የሚመረጥበት ምክኒያት ግልጽ ባይሆንም፤ ምናልባትም አሁን ላለው ችግር  ጠንካራ መንግስት የሚያስፈግ በመሆኑንና  ጠቅላይ ሚኒስተር ሚትሶታኪስ  ጠናክራ መንግስት እንዲኖራቸው ዕድል ለመስጠት ነው የሚሉ የፖለቲክ ተንታኖች አሉ። በሌላ በኩል ደግሞ ተቃዋሚዎቹ ፓርቲዎች የተሻለ አማራጭ ይዘው ባለመቅረባቸውና ቃል የገቧቸውን ተግባራዊ ማድረግ መቻላቸውን ህዝቡ ስለሚጠራጠር ነው በማለት የሚከራክረሩም አሉ።፡ ባንጻሩ አዲሱ ዴሞክራሲ ፓርቲ ለበዙ ግዜ በስልጣን ላይ መቆየቱ ፓርቲውን እንዲገነግንና ሙስናንና አድሉዊነትንም እንዲስፋፉ ኢያደርግ ይችላል  በማለት ስጋታቸውን የሚገልጹም ጥቂቶች አይደሉም።

በአውሮፓ ህብረት በኩል   በተለይ በዩክሬን ጦርነት ላይ እይተወሰደ ባለው አቋም፤ የጠቅላይ ሚኒስተር ሚትሶካቲስ መንግስት የተለየ ሀሳብ እንደሌለው ነው የሚታወቀው፡፤ ግሪክ ከደቡብና ምስራቅ በኩል ወደ አውሮፓ ለሚገቡ ስደተኖች መዳረሻ በመሆኗ የተለየ ጫና እንዳለብት ግልጽ ሲሆን ፤ የአውሮፓ ህብረት በስደተኖች ላይ ወጥና የጋራ ፖሊሲ የሌለው መሆኑ ከሚያስመርራቸው አገሮች አንዷ ናት።የጠቅላይ ሚኒስተር ሚትሶታኪስ  መንግስትም በተለይ ከቱርክ ጋር ባለው ደንበር የአጥር ግምብ በመገንባት ጭምር ስደተኖችን ለመክላከል የሚያደርገውን ጥረት እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፤ድምጽ “ አውሮፓዊ የሆነ አጠቃላይ  የስደተኖች የጋራ ፖሊስ ሊኖረን ይገባል። በደምበራችን አጥር መገንበታችንን  ግን እንቀጥላለን” በማለት ከሳቸው በፊት እንደነበረው መንግስት ደንበሩ ክፍት ሆኖ ስደተኛ በነጻ የሚገባበት እንደማይሆን ግልጽ አድርገዋል ።

Griechenland, Athen | Parlamentswahlen | Alexis Tsipras nach der Stimmabgabe
የግሪክ ምርጫምስል Michael Varaklas/AP/picture alliance

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጎረቤታቸውና የነቶ አባል ከሆነችው ቱርክ ጋር ያላቸውን ግንኑነትም በጥንቃቄ ግን በወዳጅነት መንፈስ እንደሚያስቀጥሉት ገልጸዋል፡፤ ግሪክና ቱርክ ካላቸው የቆየ ታሪካዊ  አለመግባባት በተጨማሪ  በተለይ በቆጵሮስና በደንበር ጭምር አለመግባባት ያላቸው መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፤ በቀጣይ በቱርክም ከተካሂደው ምርጫ አንጻር ግንኑንታቸው ምን ሊመስል እንደሚችል ተጠይቀውው ሲመልሱ ፤ “ ምንም ይሁን ማን ከተመረጠው የቱርክ መንግስት ጋር  ከዚህ ቀደም በተደረሱት ስምምነቶች መሰረት ጥሩ ወዳጅነት ለመገንባት እሞክራለሁ። ያንድ አገር የውጭ ፖሊሲ በአንድ ምርጫ ውጤትና የመሪ መለወጥ ምክኒያት ወዲያውኑ ይለወጣል ብየም አላስብም በማላት የአገራቸውን ለኡላዊትና ጥቅም ለማስጠጠብቅ የሚያስችላቸውን አቅም ከመገንባት ወደኋላ እንደማይሉ አስታውቀዋል።

በዘንድሮው የግሪክ ምርጫ ሌላው አዲሱ ነገር የግሪክ የዲያስፖራ አባላት በሚኖሩባቸው አገሮች እንዲመርጡ መደረጉ ነው።፡ በዚህም መሰረት በ35 አገሮችና በ99 የምርጫ ጣቢይዎች 22 ሺ 855 ዲያስፖርዎች ለምርጫ መመዝገባቸው ታውቋል። ዳግም ምርጫው በሚቀጥለው ወር መጨረሻ ወይም በሀምሌ ወር መጀመሪያ የሚደረግ ሲሆን፤ ውጤቱም የጠቅላይ ሚኒስተር ሚትሶታኪስን  አዲስ ዴሞክርሲ ፓርቲ በብችኝኘት የአገሪቱ  ገዥ  እንደሚያደርግ ከወዲሁ በሰፊው እየተነገረ ነው። ይህ ግሪክን  በብቸኘት የሚያስተዳደር ይሆናል የተባላው ፓርቲና መሪው ሚስተር ሚትሶታኪስ እንደሚጠበቀው ያገሪቱን ኢኮኖሚና መንግስታዊ መዋቅሩን በማሻሻል በግሪክ አይነተኛ ለወጥ የሚያመጡ ይሆን! ወይንስ አንድንዶች እንደሚፈሩት ያንድ ፓርቲ ተጽኖ የሰፈነበትና የነበሩትን ችግሮች የሚያስቀጥል ይሆ? ወደፊት የሚታይ ይሆናል።

 

ገበያው ንጉሴ

አዜብ ታደሰ