በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን በታጣቂዎች ይፈፀማል የተባለው ጥቃት
ማክሰኞ፣ ጥር 24 2014ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ታጣቂዎች በተቆጣጠሩአቸው አከባቢዎች መደበኛ ኑሮ መምራት አዳጋች መሆኑን ነዋሪዎች አመለከቱ፡፡ አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡት በዞኑ የገላና ወረዳ ነዋሪዎች በየጊዜው በታጣቂዎች ይፈጸማል ባሉት ግድያ እና የንብረት ውድመት አስከፊ ያሉት ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን አማረዋል፡፡ የአከባቢው ባለስልጣናት በፊናቸው አሁን ላይ በስፍራዎቹ ያሉት የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች በቂ ባለመሆናቸው በየመዋቅራዊ ደረጃው ጥያቄ ቀርቦ ምላሽ እየተጠበቀ ነው ብለዋል፡፡
ስዩም ጌቱ
አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሰ