1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መዉሊድ አከባበሩ እና ክርክሩ

ሐሙስ፣ ኅዳር 21 2010

የነብዩ መሐመድ 1492ኛዉ የልደት በዓል (መዉሊድ) ዛሬ በአብዛኛዉ ዓለም በሚገኙ ሙስሊሞች ዘንድ ተክብሮ ዉሏል።በዓሉ ኢትዮጵያ ዉስጥም በተለያዩ መንፈሳዊ እና አለማዊ ድግሶች እና ሥርዓቶች ተከብሯል።

https://p.dw.com/p/2oYRA
Äthiopien Mawlid Feier
ምስል Copyright: DW/Y.G. Egziabhare

(Beri.AA) Wawild in AA - MP3-Stereo

የነብዩ መሐመድ 1492ኛዉ የልደት በዓል (መዉሊድ) ዛሬ በአብዛኛዉ ዓለም በሚገኙ ሙስሊሞች ዘንድ ተክብሮ ዉሏል። በዓሉ ኢትዮጵያ ዉስጥም በተለያዩ መንፈሳዊ እና አለማዊ ድግሶች እና ሥርዓቶች ተከብሯል። በአዲስ አበባዉ ታላቁ አንዋር መስጊድ የነበረዉን የበዓል አከባበር ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ተከታትሎት ነበር።  መዉሊድ ሳዑዲ አረቢያ
የነብዩ መሐመድ የልደት በዓል የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ሕዝብ በሚበዛባቸዉ በአብዛኞቹ ሐገራት ይከበራል። ሙስሊሞች አብላጫ ቁጥር ባይኖራቸዉም ከሩሲያ እስከ ሕንድ፤ ከካናዳ እስከ እስከ ኢጣሊያ ባሉ ሐገራት የሚኖሩ ሙስሊሞችም በዓሉን ያከብሩታል። ይሁንና አብዛኛዉ ሕዝባቸዉ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ የሆነባቸዉ እንደ ሳዑዲ አረቢያ እና ቀጠርን የመሳሰሉ ሐገራት በዓሉን አያከብሩትም። የበዓሉ መከበር የእስልምና ሃይማኖት አባቶች እና ምሑራንን እያወዛገበ ነዉ። የሪያዱ ወኪላችን ሥለሺ ሽብሩ ሳዑዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊንን አስተያየት አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል። 
 

Äthiopien Mawlid Feier
ምስል Copyright: DW/Y.G. Egziabhare

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ስለሺ ሽብሩ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ