1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሊቢያ ስለሚገኙ ስደተኞች ይዞታ የኮንዴ እና የማክሮ አስተያየት

ሐሙስ፣ ኅዳር 14 2010

ኮንዴ ሁለቱ መሪዎች በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ስደተኞች በአስከፊ ሁኔታ በሚያዙበት በሊቢያ ተይዘው እንዲቆዩ የአውሮጳ ህብረት ሊቢያን መጠየቁ ትክክል አይደለም ሲሉ ተችተዋል። የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑዌል ማክሮ በሊቢያ በስደተኞች ላይ የሚደርሰውን በደል በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸም ወንጀል ብለውታል።

https://p.dw.com/p/2o9Us
Alpha Conde
ምስል Getty Images/AFP/S. Kambou

ሊቢያ ስለሚገኙ ስደተኞች ይዞታ የኮንዴ እና የማክሮ አስተያየት

የጊኒ ፕሬዝዳንት እና የወቅቱ የአፍሪቃ ህብረት ሊቀ መንበር አልፋ ኮንዴ ሊቢያ ውስጥ በሚገኙ አፍሪቃውያን ስደተኞች ላይ የለሚደርሰው ሰቆቃ እና በደል የአውሮጳ ህብረትን ወቀሱ። ትናንት ፓሪስ ውስጥ በጉዳዩ ከፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮ ጋር የተናገገሩት ኮንዴ ሁለቱ መሪዎች በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ስደተኞች በአስከፊ ሁኔታ በሚያዙበት በሊቢያ ተይዘው እንዲቆዩ የአውሮጳ ህብረት ሊቢያን መጠየቁ ትክክል አይደለም ሲሉ ተችተዋል። የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑዌል ማክሮ በሊቢያ በስደተኞች ላይ የየሚደርሰውን በደል በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸም ወንጀል መሆኑን ገልጸው ሀገራቸው ሊቢያ ውስጥ ያለውን ችግር ለመፍታት ከአውሮጳ ህብረት እና ከአባል ሀገራት ጋር ጠንክራ እየሰራች መሆኑን ተናግረዋል። ሃይማኖት ጥሩነህ ከፓሪስ ዘገባ አጠናቅራለች።  
ሃይማኖት ጥሩነህ
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ